Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

አማርኛ አሪሰ ሙንጂዳህ.pdf


Advertisement
  • word cloud

አማርኛ አሪሰ ሙንጂዳህ.pdf
  • Extraction Summary

ነ » ማለትም በዚህ ዓለም የሚከናወነውን ሁሉ የወሰነ ነው በንግስናውም ከእርሱ ጋር አጋር የለውም ምከንያቱም በዚህ ዓለም ላለው ሁሉ እውነተና ባለቤት እርሱ ብቻ ነው አሏህ ሁሉንም ነገር ብዛት ያውቃል አሏህ ያሻውን የሚያደርግቧ ነው ማለትም ሥፓፖ እርሱን የሚመስል በጭራሽ የለም አሏህ በዚህ እያ ሩ ይናገራል ንግግሩም የሚጀመርና የሚጨረስ ያልሆነ ፊደል ድምፅና ቋንቋም አይደለም ነገር ግን የተውሂድ ጉዳዮችን ስብስብ ያጠቃለለ ነው አሸይኸ አልአኒይ እንዲህ አሉ «አንደ ድምፅና ፊደል እንዲሁም መቅደምና መዘግየትን ከመሰሉ ከፍጡር ባህሪያት የተጥራራ ንግግር ለአሏህ ተገቢ ነው ኪፋየቱጣሊቢንን ተመልከት።

  • Cosine Similarity

ሣሇይቫ ሠ የዓቂደቱል ሙርሺዳህ መትን ራኖሠ ዴን በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው አሏህ እኛንም ሆነ አንተን ወደ ቀና መንገድ ይምራን ሀያሉና ታላቁ ፈጣሪያችን አሏህ በንግስናው ብቸኛ መሆኑን በተጠያቂዎች ሁሉ ማወቁ ግዴታ መሆኑን እወቅ ዓለምን በጠቅላላ ላይኛውንና ታችኛውን ከፍል ዓርሽና ኩርስይን ሰማያትንና መሬትን ውስጣቸውና መካከላቸው ያለውን ሁሉ ፈጠረ ሁሉም ፍጥረታቶች በችሎታው ቁጥጥር ሥር ናቸው ቅንጣትም ብትሆን ካለ እርሱ ትእዛዝ አትንቀሳቀስም ከእርሱ ጋር ፍጡርን የሚያስተዳድር የለም በንግስናውም አጋር የለውም ሕያው እንዲሁም በእራሱ የተብቃቃ ማንቀላፋትም ሆነ እንቅልፍም አይወስደውም የተደበቀውንም ሆነ የሚታየውንም የሚያውቅ ነው በምድርም ሆነ በሰማይ ምንም አይሰወርበትም በየብስና በባህር ውስጥ ያለውን ያውቃል አንዲትም ቅጠል ብትሆን አትወድቅም እርሱ ሳያውቃት አንዲትም ፍሬ ብትሆን ጨለማ መሬት ላይ አርጥብም ሆነ ደረቅ አይኖርም ለውሐል ማህፉዝ ውስጥ ቢኖር እንጂ ሁሉንም ነገር በእውቀቱ አካሏል የሁሉንም ነገር ብዛት ያውቃል ያሻውን የሚያደርግ በሚፈልገው ነገር ላይ ችሎታ አለው ንግስናም አለው እንዲሁም በራስ መብቃቃት የማይበገር ሀይልም አለው እንዲሁም ዘላለማዊነት ፍርድም አለው አንዲሁም ውሳኔ መልካም ስሞችም አሉት የወሰነውን የሚመልስ የለም የሰጠውንም የሚከለከል የለም በፍጥረቱ የፈለገውን ያደርጋል ፍጥረቱ ላይ በሚፈልገው ይፈርዳል ምንዳም አይጠብቅም ቅጣትም አይፈራም በእርሱ ላይ ግዴታም ሆነ ፍርድ የለበትም ፀጋዎች ሁሉ ከእርሱ ችሮታ ነው ቅጣቶቹ ሁሉ ከእርሱ ፍትህ ነው በሚሰራው አይጠየቅም እነሱ ግን ይጠየቃሉ ከፍጥረታት በፊት የነበረ ነው ከእርሱ በፊትም ሆነ ከአርሱ በኋላ የሚባል የለውም ላይም ሆነ ታች ቀኝም ሆነ ግራ ፊትም ሆነ ጀርባ የለውም የዓለም አጠቃላይም ሆነ ከፊሉም አይደለም መቼ ነበር አይባልም የት ነበርም ሆነ እንዴት ነበር አይባልም ቦታ ሳይኖር ነበር ፍጥረታቶችንም ከወነ ዘመንንም አበጀ በዘመን አይታጠርም በቦታም አይወሰንም አንድ ጉዳይ ከሌላ ጉዳይ አይጠምደውም ሐሳብ አይደርስበትም ልቦናም አያካልለውም በጭንቅላት ውስጥም አይወሰንም በነፍስም ውስጥ አይመሰልም በሐሳብም አይሳልም በልቦናም እንዴት ተብሎ አይታሰብም ሐሳብም ሆነ ቅት አይደርስበትም እርሱን የሚመስል በጭራሽ የለም «እርሱ ሰሚም ተመልካቸም ነውኔ ሄራ ሄሬኅ ሬቫ ሠ አርሪሳለቱል ሙንጂዳህ የዓቂደቱል ሙርሺዳህ የቃላት ፍቺ መግቢያ ራ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ምስጋና ለአሏህ ይገባው ሶላትና ሰላም በአይነታቸን በሙሐመድ እና በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም መልካምና ንጹህ በሆኑት በሰሀቦቻቸው ላይ ይስፈን በመቀጠልም ዓሊሙ ሼኸ ፈኸሩዲን ኢብኑ ዓሳኪር። አሏህ እኛንም ሆነ አንተን ሐቅን ለማወቅና ትከከለኛን ነገር እንድንገጥም ወደ ቀና መንገድ ይምራን ሀያሱና ታላቁ ፈጣሪያችን አሏህ በንግስናው ማለትም በስልጣኑ አጋር የሌለው ብቸኛ መሆኑን በተጠያቂዎች ሁሉ ማወቁ እና ማመኑ ግዴታ መሆኑን እወቅ ለዚህ ዓለም ከአሏህ በስተቀር ሌላ ጌታና ፈጣሪ የለውም ካለ እርሱ በስተቀር ሊገዙት የሚገባው ሌላ የለም ተጠያቂ ሲባል ለአካለመጠን የደረሰ አብድ ያልሆነና የእስልምና መሠረታዊ ጥሪ የደረሰው ማለትም ካለ አሏህ በስተቀር ሌላ ፈጣሪ እንደሌለና ሙሐመድ የአሏህ መልእከተኛ መሆናቸው የደረሰው ሰው ነው ዓለምን በጠቅላላ ማለትም ካለመኖር ወደ መኖር የገባ ማንኛውም ነገርን የፈጠረው አሏህ ነው ይህ ሲባል የዓለም ላይኛውን ከፍል እሱም ሰማያትና ከነሱ በላይ ያሉትን እንደ ጀነት ያሱ እና ታቸኛውን ከፍል እሱም ምድሮችና ከነሱ በታች ያሉትን አንደ ጀሃነም ያሉ ዓለማትን ማለትም ዓርሽና ኩርስይን ሰባቱ ሰማያትንና መሬትን ውስጣቸውና መካከላቸው ያለውን ሁሉ ፈጠረ ዓርሽ የጀነት ጣሪያ ነው ከፍጥረታቶች ሁሉ በግዝፈት ትልቁ ሲሆን አራት እግር ያለው ትልቅ ዙፋን ነው ኩርሲይ ደግሞ ከዓርሽ በታች የሆነ ትልቅ አካል ሲሆን ከሰማያትና ከመሬት የተለቀ ከዓርሽ ያነሰ ነው ሰማያትና መሬት ውስጥ ሲባል እንደ መላኢካዎች ሰዎችና አጋንንቶችና ሌሉችን ሲያካትት በመካከላቸው ያለ ሲባል ደግሞ ፀሐይ ጨረቃ ከዋከብቶችንና ሌሎችንም ያካትታል ይህ ደግሞ የባሮችን አካልና ስራዎቻቸውን እንዲሁም ሼኸ ጀማሉዲን አልአኒይ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ «አሏህ በእውኑ በባህሪውና በድርጊቱ አምሳያ የለውም ለእርሱ አጋር የለውም ኪፋየቱጣሊቢን በተሰኘ መፅሐፋቸው ጠቅሰውታል ንግግራቸውን ልቦናዊ ሽውታቸውን። ነ » ማለትም በዚህ ዓለም ለማንኛውም ነገር ካለ አሏህ በስተቀር ሌላ ፈጣሪ የለም የዚህች ዓለም መኖር ለአሏህ መኖር ማስረጃ ነች ምከንቱም በጭንቅላታችን ስናስበው አንድ ድርጊት ያለ አድራጊ ሊኖር አይችልምና ነው ሁሉም ፍጥረታቶች አካላቶችም ሆኑ ባህሪያት በቸሎታው ቁጥጥር ሥር ናቸው ማለትም የተገኙት በችሎታው ነው እነሱም በቁጥጥሩ ሥር ናቸው እንደፈለገው ማድረግ ይችላል ከዓለም ውስጥ ብናኝም ብትሆን ካለ እርሱ ትእዛዝ እና መሻት አትንቀሳቀስም ብናኝ ስንል የፀሐይ ብርሃን በመስኮት ሲገባ የሚታይ ነገር ነው ከእርሱ ጋር የፍጡርን ጉዳዮች በማስተዳደር አጋር ሆኖ የሚያስተዳድር የለም የሁሉም ፍጡር አስተዳዳሪ እርሱ ነው ማለትም በዚህ ዓለም የሚከናወነውን ሁሉ የወሰነ ነው በንግስናውም ከእርሱ ጋር አጋር የለውም ምከንያቱም በዚህ ዓለም ላለው ሁሉ እውነተና ባለቤት እርሱ ብቻ ነው አሏህ ሕያው ነው አይሞትም ሕይወቱ የኛን ሕይወት አይመስልም በመንፈስ በስጋና በደም አይደለም እንዲሁም በእራሱ የተብቃቃ ማለትም ከእርሱ ሌላ የሆኑ ሁሉ ከእርሱ ሲከጅሉ እርሱ ግን ከሌላ ፈላጊ አይደለም ማንቀላፋትም ማለትም እንጉልቻም ሆነ እንቅልፍም አይወስደውም ምከንያቱም በፈጣሪ የማያመች ሊኖር የማይችል ጎዶሎነትን ስላዘሉ ነው አሏህ የተደበቀውንም ማለትም ከፍጥረታቶች የተደበቀና የተሰወረውን የሚያውቅ ነው ፍጥረታቶች ግን ከአሏህ እውቀት የሻላቸውን ያህል እንጂ ሁሉንም አያካልሉም አሏህ የተሰወረውንም ሆነ የሚታየውንም ማለትም ፍጥረታቶች የሚያዩትንም የሚያውቅ ነው በምድርም እንዲሁ ከስሯ ሼኸ ጀማሉዲን አልአኒይ ለዚህ ማስረጃ « ሁ » የሚለውን አያ አስፍረው አንዲህ አሉ ይህች አያ ባሮችና ድርጊቶቻቸው በጎም ሆነ መጥፎ ለሀያሉ ጌታችን ፍጥረታት እንደሆኑ አስፍራለች ለቀደሪዮችም ምላሽ ሰጠች ኪፋየቱጣሊቢን መፅሐፍን ገፅ ተመልከት የሉትንም ሆነ በሰማይ እንዲሁ ከሱ በላይ ያሉት ምንም አይሰወርበትም የተጥራራው ጌታችን ሁሉንም ነገር ባጠቃላይም ሆነ በዝርዝር ያውቃል አሏህ አካሎችንና ባህሪያቶችን ባሪያዎችንና ስራዎቻቸውን ውጫዊ ገጽታቸውንና ውስጣቸውንም ያውቃል እንዲሁም እንደ እፅዋትና እንስሶች ያሉትን በየብስና በባህር ውስጥ ደግሞ እንደ ልዑል ያለውን ያውቃል አንዲትም ቅጠል ብትሆን አትወድቅም እርሱ ሳያውቃት አንዲትም ፍሬ ብትሆን ጨለማ መሬት ላይባ ማለትም በምድር ውስጣዊ ከፍል አይኖርም አሏህ ቢያውቀው እንጂ እርጥብም ሆነ ደረቅ አይኖርም እርሱ ሳያውቀው አንድም ሰው አይወለድም አንድም ጠብታ ከሰማይ አይወርድም አሏህ ሳያውቀው ይህ ሁሉ ደግሞ አይኖርም ለውሐል ማህፉዝ ውስጥ ተጽፎ ቢኖር እንጂ ለውሐል ማህፉዝ ከሰባተኛው ሰማይ በላይ የሚገኝ ግኡዝ አካል ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረውንና ወደ ፊት እስከ የውመል ቂያማ የሚሆነውን የተጻፈበት ነው አሏህ ሁሉንም ነገር በእውቀቱ አካሏል የተቀደሰው ጌታችን ከዚህ በፊት የተከሰተውን አሁን የሚሆነውንና ወደፊት የሚከሰተውንም መጀመሪያ በሌለው ፍጡር ባልሆነው አምሳያ በሌለው በማይቀያየረው በማይጨምረውና በማይቀንሰው እውቀቱ ያውቃል ለአሏህ አንድን ነገር ሳያውቀው ቀርቶ እለሱ አዲስ አውቀት አይከሰትበትም መርሳትም ቢሆን አይከሰትበትም የሁሉንም ነገር ብዛት ያውቃል የተቀደሰው ፈጣሪ መጀመሪያ በሌለው እውቀቱ የሁሉንም ነገር ብዛት ያውቃል እርሱ የፍጥረታትን ትንፋሽ ብዛት ያውቃል እንዲሁም የዝናብ ጠብታዎች የአሸዋ ጠጠሮችንና የሌሎችንም ብዛት ያውቃል አሏህ ያሻውን የሚያደርግቧ ነው ማለትም እንዲገን የፈለገውን መገኘቱን በፈለገው ወቅትና መገኘቱን በፈለገው ባህሪ የማስገኘት ችሎታ አለው በሚፈልገው ነገር ላይ ችሎታ አለው እንዲገኝ የፈለገውን ነገር መፍጠር አይሳነውም ማንም የሚከለከለውም የለም የአሏህ መልእከተኛው እንዲህ አሉ ። ሠ ሠ ነፊ ማለትም «አሏህ ያሻው ይሆናል ያላሻው ደግሞ አይሆንም ማንኛውም ነገር ኸይርም ሆነ ሸር አሏህ መኖሩን የሻው ከሆነ ካለመኖር ወደ መኖር ይሻገራል ነገር ግን ኸይሩ በአሏህ ውዴታና ትእዛዝ ሲሆን ሸሩ ግን በአሏህ ውዴታና ትእዛዝ አይደለም ማንኛውም ነገር አሏህ መኖሩን ያልፈለገው ከሆነ በማንም ዱዓእ ይሁን ሰደቃ ካለመኖር ወደ መኖር አይሻገርም ከኃጢያት አንርቅም በእርሱ ጥበቃ ቢሆን እንጂ በጎን ነገር መስራት አንቸልም በእርሱ እገዛ ካልሆነ በስተቀር የተጥራራው ጌታችን የማይጠፋና ማንም የማይቀናቀነው ንግስናም አለው እንዲሁም በራስ መብቃቃት ከፍጥረቱ ምንም አይፈልግም እነሱ ግን ከእርሱ ይከጅላሉ ከነሱ ለራሱ ምንም ጥቅም አያስገኝም ከራሱም አደጋን በነሱ አይከለከልም የማይበገር ሀይልም አለው እርሱ የማይሸነፍ ሃያል ነው እንዲሁም ዘላለማዊነት አለው አይጠፋም አይሞትም አይባከንም ፍርድም አለው ማለትም ገደብ የሴለው ማዘዝና መከልከል አንዲሁም ውሳኔ አለው ማለትም መፍጠር የእርሱ ነው ይኸውም አንድን ነገር ካለመኖር ወደ መኖር ማምጣት ነው እንደ አርራህማንና አርረሂም ያሱ ምሉአነትን የሚያመላከቱና ለእርሱ ተገቢ የሆኑ መልካም ስሞችም አሉት ከጎዶሉ ባህሪያት ሁሉ የጠራ ነው ለዚህም ነው እርሱን ኣህ ወይም ሩህ ወይም ዓቅል ብሎ መጥራት የማይፈቀደው የወሰነውን የሚመልስ የለም ማንም ቢሆን እርሱ የወሰነውን የሚመልስ የለም የሰጠውንም የሚከለከል የለም ማንም ቢሆን እርሱ የለገሰውን ሲሳይ የሚከለከል የለም አሏህ በፍጥረቱ የፈለገውን ያደርጋል የሚያደርገውም በምርጫው እንጂ ሳይወድ በግድ አይደለም አሏህ ፍጥረቱ ላይ በሚፈልገው ይፈርዳል የፈለገውን መልካም ሲያደርግ የፈለገውን አስቀያሚ ያደርጋል የፈለገውን ግዴታ ሲያደርግ የፈለገውን ሐራም ያደርጋል ከፍጥረቱ ምንዳም ሆነ ጥቅም አይጠብቅም ከነሱ ቅጣትም ሆነ ጉዳት አይፈራም የተቀደሰው ጌታችን በእርሱ ላይ ግዴታም ሆነ ሐቅ የለበትም ምከንያቱም ምንም ግዴታ የለበትም እንዲሁም በእርሱ ፍርድ የለበትም አቡዳውድ ሱነናቸው ውስጥ የአደብ ከፍል ላይ ሲነጋ ስለሚባለው በተጠቀሰበት ምእራፍ ላይ ዘግበውታል የሼኸ አኒይን መፅሐፍ ኪፋየቱጣሊቢን ገ ተመልከት ምክንያቱም በእርሱ የሚፈርድ የለም እርሱን የሚያዝም ሆነ የሚከለከል ስለሴለ ነው አሏህ አንድን ሰው የሚቸረው ፀጋዎች ሁሉ ከእርሱ ችሮታ ነው እንጂ ግዴታ አይደለም በአንድ ሰው የሚያወርደው ቅጣቶቹ ሁሉ ከእርሱ ፍትህ ነው እንጂ በደል አይደለም አሏህ ምንዳ የሰጠው ችሮት ሲሆን የቀጣው ደግሞ ከፍትሃዊነቱ ነው « ሬ ሀ» ማለትም ፈጣሪህ ባሮቹን በዳይ አይደለም የተቀደሰው ፈጣሪ በባሪያዎቹ ላይ በሚሰራው አይጠየቅም ምከንያቱም እነሱም ሆኑ ንብረቶቻቸው የአሏህ ስለሆኑ እንደፈለገ ማድረግ ይችላል እነሱ ግን ይጠየቃሉ ባለቤት ለሆኑለት ድርጊትም ሒሳብ ይደረጋሉ አሏህ ከፍጥረታት በፊት የነበረ ነው የአሏህ መልእከተኛ አንዲህ አሉ ህቃ ኳሥ ዕጁ ኦህ «አሏህ ከእርሱ ሴላ ምንም ነገር ሳይኖር ነበር ማለትም ከአለማት ምንም ነገር ሳይኖር አሏህ ጥንት ነበር ከእርሱ ጋር ውሃም ሆነ አየር ጊዜም ሆነ ቦታ መሬትም ሆነ ሰማይ ዓርሽም ሆነ ኩርሲይ ብርሃንም ሆነ ጨለማ ሰውም ሆነ አጋንንት መላኢካዎችም ቢሆን አልነበሩም እንዲሁም ለእርሱ ጅማሬ ስለሌለው ለባህሪያቶቹም ጅማሬ የላቸውም ለዚህም ነው ጥንት ያለነበረ ባህሪ አይከሰትበትም ምከንያቱም በአንድ ነገር ላይ የሁኔታዎች መቀያየር የግኝትነቱ ትልቅ ምልከት ነው እንዲሁም ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላ የሚባል የለውም ማለትም የእርሱን መኖር አለመኖር አልቀደመውም ስለዚህ በመኖር እንዲወሰን ያደረገው የለም ከእርሱ በስተቀር ያሉ ዓለማቶች ግን ግኝቶች ናቸው መኖራቸውን አለመኖር ቀድሞታል ለዚህም ነው ካለመኖር ይልቅ በመኖር እንዲወሰኑ የሚያደርጋቸው ያስፈለጋቸው እንዲሁም ከእርሱ በኋላ የሚባል የለውም ስለዚህ መጥፋት አይከተለውም በእርሱም አያመችም የተቀደሰው አሏህ በስድስቱ አቅጣጫዎች አይወሰንም ስለዚህ ላይም ሆነ ታች ቀኝም ቡኻሪይ በሰሂሃቸው የፍጥረታት ጅምር ከፍል ጩቭ ኦ» ስለሚለው አንቀፅ የወረደውን በሚመለከት ምእራፍ ዘግበውታል በይሃቅይ ደግሞ ሱነኑል ኩብራ ላይ ዘግበውታል ሆነ ግራ ፊትም ሆነ ጀርባ የለውም ምከንያቱም አቅጣጫዎች የዚህ ዓለም ከፍል ናቸው አሏህ ደግሞ ከዓለማቶች ምንም አይከጅልም የተጥራራው ጌታችን የዓለም አጠቃላይም ሆነ ከፊሉም አይደለም ማለተም ዓለም በጠቅላላ አሏህ አይደለም እንዲሁም የዓለም ከፊል አካልም አይደለም በእርሱ ውስጥ የሚሆን ነገር የሚባል የለም እርሱ ደግሞ በሌላ ነገር ውስጥ በፍፁም አይሆንም ምከንያቱም መባዛትን መበራከትን መከፋፈለንና መገማመስን ስለሚያስከትል ነው ይህ ደግሞ በአካላቶች የተወሰኑ ባህሪያት ናቸው አሏህ ደግሞ አካል አይደለም እርሱ እንደ ቅንጣት ከጥቂት ከፍልፋዮች የተገነባ ትንሽ አካልም ሆነ እንደ ዓርሽ ከብዙ ከፍልፋዮች የተገነባ ግዙፍ አካልም አይደለም እንዲሁም እንደ ዛፍ ድንጋና ሰው ያለ የሚዳሰስ ግዑዝ አካልም ሆነ እንደ ብርሃን ነፍስ አየር አጋንንትና መላኢካዎች የማይዳሰስ ረቂቅ አካልም አይደለም ምክንያቱም ፍጥረታቶቹን በፍፁም ስለማይመስል ነው አሏህ መቼ ነበር አይባልም ምከንያቱም ለመኖሩ ጅማሬ የለውምና እንዲሁም አሏህ የት ነበርም ሆነ እንዴት ነበር አይባልም የት ነበር የማይባለው ቦታ ስለሌለው ነው መሬትም ሆነ ሰማይ ላይ ዓርሽም ላይ ሆነ በታች የትም ቦታ ሆነ ሁሉም ቦታ አልሰፈረም ይልቁንስ የተጥራራው አሏህ ያለ ቦታ ያለ ነው የአሏህ መልእከተኛ እንዲህ ብለዋል ኃ ፊዕቃ ነጩ ዕቃህ ኳሥ » ጩህ ሥ ኢማም አቡ ጃዕፈር አጥጠሃዊይ በ ሒ የተወለዱት የአህሉሱና ወልጀማዓ እምነት ማብራሪያ ነው በማለት ባዘጋጁት የዓቂዳ መፅሀፋቸው ላይ እንዲህ አሉ «እንደተቀሩት ግኝቶች ስድስቱ አቅጣጫዎች አያካልሉትም ሼኸ አኒይ አሏህ ከአካልነት የሴለ ነገር ከመሆንና አንድ ነገር ውስጥ ከመሆን የተጥራራና የተቀደሰ መሆኑን ጠቅሰዋል ኪፋየቱጣሊቢንን ገፅ ተመልከት ኢማም ዓሊይ አሏህ ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ ጌታችን ውስን የመሰለው የሚመለከውን ፈጣሪ የማያውቅ ነው አቡ ኑዓይም ሂልየቱል አውሊያእ በተሰኘው መፅሐፋቸው ዘግበውታል ኢማም አቡ ጀዕፈር አጥጠሃዊይ ደግም እንዲህ በለዋል «አሏህ ከወሰኖች ከጫፎች ከጎኖች ከትላልቅ የሰውነት ክፍሎችና ከትናንሽ የሰውነት ከፍሎች የተጥራራ ነው ኢማም ዓሊይ አሏህ ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ «የተጥራራው አሏህ ዓርሽን የፈጠረው ችሎታውን ሊያሳይ እንጂ ቦታ አድርጎ ሊይዘው አይደለም ኢማም አቡመንሱር አልበግዳዲይ አልፈርቅ በይነል ፊረቅ በተሰኘው መፅሐፋቸው ገፅ ዘግበውታል ሼኽ አብዱልገኒይ አናብሉሲይ ደግሞ እንዲህ አሉ አሏህ ሰማያትንና መሬትን የሞላ ነው ብሎ የሚያምን ወይም ዓርሽ ላይ የተቀመጠ አካል ነው ብሎ የሚያምን ከሆነ ሙስሊም ነኝ ብሎ ቢያስብም ካፊር ነው ፈትሁርረባኒ በተሰኘ መፅሐፍ ገፅ ጠቅሰውታል «አንተ ነህ አዝዛሂር ከአንተ በላይ ምንም ነገር የለም አንተው ነህ አልባጢን ከአንተ በታች ምንም ነገር የለም እንዲሁም አሏህን እንዴት ነው አይባልም ምከንያቱም እንዴት የሚባለው እንደ ግኝትነት መቀየር መለወጥ ምስል መልክከ ርዝመት እጥረት ቀለም እንቅስቃሴ እርጋታና መቀመጥን ለመሳሰሱ ለፍጥረታት ባህሪያቶች ነው የተጥራራውና የተቀደሰው ፈጣሪያችን ካፊሮች ከሚሉት የላቀና የጠራ ነው የዚህ መትን ባለቤት እነዚህን የመሰሉ ቃላቶችን ለአሏህ እንዳንጠቀም ከከለከሉ በኋላ የእውነት ባለቤቶች እምነትን በማስጨበጥ እንዲህ አሉ አሏህ ጥንት ቦታ ሳይኖር ነበር ማለትም ቦታ የሚባል አልነበረም ከዛ በኋላ ፍጥረታቶችንም ከወነ ማለትም ዓለማትን ከፈጠረም በኋላ ያለ ቦታ ነው ያለው ምከንያቱም አሏህ ከአንድ ሁኔታ ወደ ሌላ ሁኔታ መቀያየር አያመችበትምና የተቀደሰው አሏህ ዘመንንም አበጀ በዘመን አይታጠርም ስለዚህ ዘመን አያልፍበትም ከጉድለት የተጥራራው አሏህ በቦታም አይወሰንም ምከንያቱም ባዶ ቦታ የሚይዝ አካል ስላልሆነ ነው አሏህ እንደ ብርሃንና አየር አንድን ከፍል ወይም መስጂድን ወይም ካዕባን ወይም ህዋን የመሰለ ቦታን የሚሞላ አይደለምዬ ከዚህ በመነሳት ማንኛውም በቁርኣን ወይም በሐዲስ የሰፈረ ላይ ላዩ ሲታይ ለአሏህ ቦታ እንዳለው አድርጎ የሚያስመስል ከሆነ ታእዊል ማድረጉ ግዴታ ይሆናል ማለትም በውጫዊ ትርጉሙ ሳይሆን አሏህ ከቦታ የተጥራራ መሆኑን ከ ሙስሊም በሰሒሓቸው የዚክርና የዱዓእ ከፍል ውስጥ እንቅልፍ ጊዜ መተኛ ላይ ሲያርፉ ስለሚባለው በተመለከተ ምእራፍ ዘግበውታል በይሃቂይ ይህን ሐዲስ ከጠቀሱ በኋላ እንዲህ አሉ «ከእርሱ በላይ ምንም ነገር ከሌለ ከእርሱም በታች ምንም ነገር ከሌለ ቦታ ላይ አይደለም ማለት ነው አልአስማእ ወስሲፋት በተሰኘው መፅሐፍ ገፅ ጠቅሰውታል ኢማም አቡ ጃዕፈር አጥጠሓዊይ በዓቂዳ መፅሐፋቸው እንዲህ አሉ «አሏህን ከሰው ባህሪ በሆነ አንድ ባህሪ የገለፀ ከእስልምና ይወጣል አቡ ሱለይማን አልኸጣቢ ደግሞ እንዲህ አሉ በእኛም ሆነ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ የሚሆንብን ፈጣሪያችን የምስልም ሆነ የቅርፅ ባለቤት እንዳልሆነ ማወቅ ነው ምክንያቱም ምስል እንዴታን ያስከትላል እንዴታ ደግሞ ለአሏህም ሆነ ለባህሪያቱም ተገቢ አይደለም ይህንንም በይሃቂይ በአስማእ ወስሲፋት ገፅ ዘግበውታል ኢማም ዓሊይ አሏህ ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ አሏህ ቦታ ሳይኖር ነበር አሁን ደግሞ እርሱ እንደነበረው ያለ ነው አቡ መንሱር አልበግዳዲይ አልፈርቅ በይነል ፊረቅ በተሰኘው መጽሐፋቸው ገፅ ዘግበውታል ከሚያመላከቱ ሙሕከማት የቁርኣን አያዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ይፈሰራል የተቀደሰው ፈጣሪያችን ጉዳዮችን ሲፈፅም አንድ ጉዳይ ከሌላ ጉዳይ አይጠምደውምእ ምከንያቱም አንድን ነገር የሚያደርገው ማለተም ካለመኖር ወደ መኖር የሚያመጣው ጅማሬ በሌለው ችሎታውና ፍላጎቱ መሳሪያ መጠቀም ሳያስፈልገው እንዲሁም በሰውነት ከፍል አካሎች ሳይታገዝ ወይም ከምንም ነገር ጋር ንከኪ ሳይኖረው ምንም ችግር ሳይደርስበት ነው የተጥራራው ጌታችን ሐሳብ አይደርስበትም ምከንያቱም ሐሳብ የሚያጠነጥነው አንድ ሰው በለመደው በስሜት ህዋሱ በሚያውቀው እንደ መጠን ቅርፅ ቀለምና ቦታ ያለውን ነገር ስለሆነ ነው አሏህ ደግሞ በዚህ አይገለፅም ልቦናም አያካልለውም ማለትም በልቦናዎች አይታጠርም በጭንቅላት ውስጥም አይወሰንምጋ ስለዚህ ጭንቅላቶች ሊመስሉት አይቸሉም በነፍስም ውስጥ አይመሰለም ምከንያቱም የተጥራራው ፈጣሪያችን አምሳያ የለውምና በሐሳብም አይሳልም ምከንያቱም ምስል የለውምና በልቦናም እንዴት ተብሎ አይታሰብም ምከንያቱም እንዴት የሚያስብል የለውምና ሐሳብም ሆነ ቅዥት አይደርስበትም ማለትም የአሏህን አውነታ አይደርሱበትም ምክንያቱም የአሏህን እውነታ ካለ አርሱ በስተቀር ሌላ የሚያውቅ ማንም የለምና ለዚህም ነው ሰለፎች ስለ አሏህ እውን ማሰላሰል የከለከሉት ኢማም የሆኑት ዙኑን አልሚስሪይ እንዲህ አሉ ህ ሄዴ ፊህ ሬቭጆ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Advertisement
Bottom banner

Download options | Convert to Pdf | Reading List | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact