Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
በጉባኤ የሚነገር የጸና የቀና የጎላ የተረዳ ሃይማኖት ት በተዋህዶ ከበረ ነው። ከዚህ እንዲህ ማለቱ በሥጋዊ ነገር አይከራከርም ሲል ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጽሐፍን ገልጦ አነበበ ይላል ያነበበው ቃልም ይህ በኢሳይያስ ትንቢት ተጽፎ ያለውን ቃል ነውና ትርጓሜው ተመሳሳይ ነው።
ኢትዮጵያን ግራኝ አህመድ በወረራት ጊዜ ዐፄ ልብነ ድንግል ከፖርቹጊዝ መንግሥት እርዳታ ጠይቀው እርሳቸው ከሞቱ በኋላ በፖርቹጊዞች እርዳታ ግራኝ ድል ሆኖ ኢትዮጵያ ሙሉ ነጻነቷን አግኝታ መንግሥቷን በትክክል ማቋቋሟ የታወቀ ነው በዚህ ጊዜ ከኢትዮጵያ ተልኮ ፖርቹጊዞችን ለእርዳታ ያመጣው ቤርሙዲዝ ደ ከኢትዮጵያ ግዛት ገሚሱ ለፖርቹጊዝ መንግሥት ይሰጥ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም ከእንግዲህ ወዲያ አቡን ከእስክንድርያ መምጣቱ ቀርቶ ከሮም ይምጣ እኔም ለኢትዮጵያ አንደኛ መጀመሪያ ሮማዊ ጻጻስ ልሁን ብሎ ዐፄ ገላውዴዎስን ጠየቀ ዐፄ ገላውዴዎስም ሊቃውንቱን ሰብስበው ምን እናድርግ ብለው ጠየቁ የኢትዮጵያ ሊቃውንትም ፍርድ በቃ ይስጡን እንከራከርና ሮማውያን ቢረቱን እንልቀቅላቸው ብንረታቸው ይልቀቁልን አሏቸው ንጉውም ፈቅደው ጉባዔ ተደረገ ለኢትዮጵያ ሊቃውንት አፈ ጉባኤ ዝክሪና ጳውሊ ኾኑ ዝክሪና ጳውሊም በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጠገብ የሚገኝ የደብረ ጽሙና ገዱም ሊቃውንት ናቸው ኢትዮጵያውያን ሮማውያንን ሀገራችሁ ወዴት ነው ሃይማኖታችሁ ምንድን ነው ሲሉ ጠየቋቸው ሮማውያን ሲመልሱ ሀገራችን ሮም ነው ሃይማኖታችንም ኹለት ባሕርይ ኹለት ጠባይዕ አንዱ የመለኮቱ አንዱ የትስብእቱ እንላለን ኹለተኛም ወልድ ከአብ ያንሳል መንፈስ ቅዱስም ከወልድ ያንሳል እንላለን አሏቸው ኢትዮጵያውያን ሲመልሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ የሚል ምን አለ እስኪ አስረዱን አሏቸው ሮማውያን ሲመልሱ እርሱው ራሱ ወልድ ደቀመዛሙርቱ ሕልፈተ ዓለም የሚሆነው መቼ ነው ብለው ቢጠይቁት መላእክትም ቢሆኑ ወልድም ቢሆን ከአብ በቀር ያችን ዕለት ያችን ሰዓት የሚያውቃት የለም ብሏል ስለዚህ አብ መለኮት ስለሆነ ያውቃል ወልድ መንፈስ ቅዱስ ግን መለኮት ስላልሆኑ አያውቁም እንላለን እናንተ ይህን ነገር ምን ትሉታላችሁ አሉ አባ ዝክሪ ሲመልስ ሦስቱን አካላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን አንድ አምላክ የምንላቸው አብን ልብ ወልድን ቃል መንፈስ ቅዱስን እስትንፋስ ብለን በአብ ልብነት ያስባሉ ያውቃሉ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ እስትንስነት ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ ለየራሳቸው ልብ ቃል እስትንፋስ የላቸውም በማለት ነው ልብ ቃል እስትንፋስ ያለው አንድ ሰው በልቡ አስቦት አውቆት ለመናገር ጊዜው ባለመድረሱ ሰዓት እየጠበቀለት ሰውሮ የያዘውን ነገር ጊዜው ባለመድረሱ ምክንያት በቃሉ ሳይናገረው ቢቆይ ቢጠየቅም ዛሬ አልናገረውም ቢል አያውቅም እንደማይባል ወልድም ያችን ዕለት ያችን ሰዓት የምትገለጽበት ጊዜው እስኪደርስ በልቤ በአብ ሰውሬ አቆያታለሁ እንጅ ዛሬ በቃልነቴ አውጥቼ አልናገራትም ማለቱ ነው እንጅ የማያውቃት ሆኖ አይደለም እንዲህስ ባይሆን የከዊን ስማቸውና ግብራቸው ተፋልሶ አብ ቃል ወልድ ልብ በተባሉ ነበረ አለው በዚህ ጊዜ ሮማውያን መልስ አጥተው ዝም አሉ ኹለተኛ ጥያቄ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሮማዊ ተነሥቶ መለኮት ሥጋ አልሆነም ሥጋም መለኮት አልሆነም ሥጋ ለመለኮት እንደ ብረት ልብስ እንደ ጥሩር ኾነው መለኮትና ሥጋ እንደ ኀዳሪና ማኅደር ኾነው መለኮት የመለኮትን ሥራ ትስብእትም የትስብእትን ሥራ ሲሰሩ ኖረው በዕርገቱ ጊዜ የለበሰውን ሥጋ አውልቆ በሦስተኛው ሰማይ አኑሮት በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ተቀመጠ የዚህም ምሳሌው አንድ ንጉሥ ለጦርነት ወደ ሰልፍ ሲገባ የጦርነት ልብስ ይለብሳል ሲዋጋ ውሎ ድል ካደረገ በኋላ የለበሰውን የጦር ልብስ አውልቆ ከግምጃ ቤት ሰቅሎ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ላይ እንደሚቀመጠው ያለ ነው እንጅ ትስብእቱን ከመለኮቱ ጋራ በአባቱ ቀኝ አያስቀምጠውም አለ አባ ዝክሪ ሲመልስ ነፍስ ርቀቷን ሳትለቅ ሥጋ ግዙፍ ውሱን መኾኑን ሳይለቅ ተዋሕደው አንድ ሰው እንዲኾኑ መለኮት ምልዐቱን ስፍሐቱን ርቀቱን ሳይለቅ ትስብእትም ግዙፍነቱን ውሱንነቱን ሳይለቅ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ኾኗል እንጅ እንደ ልብስና እንደ ገላ አይደለም አለ ሮማዊ መለኮት ከደረሰበት ኹሉ ይህ መዋቲ ትስብእት ደረሰ ትላለህን አለ አባ ዝክሪ ሲመልስ እኔስ መለኮት እና ትስብእት በተዋህዶ አንድ ስለሆኑ መለኮት በሥጋ ውሱን ግዙፍ ኾነ ትስብእትም በመለኮት ምሉዕ ስፉሕ ረቂቅ ኾነ እላለሁ ትስብእት ከመለኮት ተለይቶ በሦስተኛው ሰማይ እንዳልቀረ በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ እንደተቀመጠም ሲያስረዳ አሜሃ ትሬእይዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው እንዘ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ብሏል በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም እንዲመጣ ሲያስረዳም ወአመ ይመጽእ ወልደ እጓለ እመሕያው በስብሐተ አቡሁ ወኩሎሙ መላእክቲሁ ምስሌሁ ብሏል ይህ ንባብ በቅዱስ ወንጌል መጻፉን ታምናለህ ትክዳለህ። አለው ሮማዊ መልስ አጥቶ ዝም አለ ሦስተኛ ጥያቄ ሮማዊ እኔ ክርስቶስን ፍጡር እለዋለሁ አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ ክርስቶስን ፍጡር የሚል ንባብ ከምን ታገኛለህ አለው ሮማዊ አምላክ ከኾነ ከሣምራዊት ውኃ እስኪለምን ድረስ ለምን ተጠማ ከላይ ያለው ሐኖስ ከታች ያለው ውቅያኖስ በመኃል እጁ ሲሆን አምላክ ይጠማልን አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ ፍጡር ከኾነ የእግዚአብሔርንስ ስጦታ አውቀሽ ቢኾን ይህ ውኃ አጠጭኝ ብሎ የሚለምንሽ ማን እንደሆነ ተገንዝበሽ አንች የሕይወት ውኃን አጠጣኝ ብለሽ በለመንሺው ነበረ እርሱም በሰጠሽ ነበረ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ኹሉ ዳግመኛ ይጠማል እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ዳግመኛ ይህ እኔ የምሰጠው ውኃ ለዘላለም ሕይወት ሊኾነው ከውስጡ ሲመነጭ ይኖራል እንጅ ዳግመኛ አይጠማም ለምን አላት አለው ዐራተኛ ጥያቄ ሮማዊ አምላክ ከኾነ አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት ብሎ ለምን ጠየቀ የተቀበረበትን ባላወቀውም ነበረን ኹለቱ ዕውራንስ የዳዊት ልጅ ይቅር በለን ባሉት ጊዜ ምን ትሻላችሁ ብሎ ለምን ጠየቃቸው የሚሹትን ባላወቀውም ነበረን አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ እግዚአብሔር አዳምን አይቴ ሀሎከ ብሎ ጠየቀው ይላል ዘፍ ደታ ሙሴንም ምንት ውስተ እዴከ ብሎ ጠየቀው ይላል ዘፀ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ መጠየቁ አዳም ያለበትን ቦታ አጥቶት ሙሴም በእጁ ምን እንደያዘ አላውቀው ብሎ ይኾን አይደለም ይህም ይህን የመሰለ ጥያቄ ነው በዚያውስ ላይ ፍጡር ከኾነ አልዓዛር አልዓዛር ነዓ ፃዕ አፍአ እመቃብር ብሎ ሊያስነሣው እንደምን ቻለ በደረቅ ግንባርስ ላይ ዐይን ሊፈጥር እንደምን ቻለ አለው ሮማዊ ይህን የመሳሰለስ ቅዱሳንም ልዩ ልዩ የኾኑ ብዙ ተአምራት ያደርጋሉ አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ ቅዱሳን ልዩ ልዩ ተአምራት ቢያደርጉ የርሱን ስም ጠርተው በስሙ ለኢየሱስ ናዝራዊ ተንሥእ ወሑር እያሉ ነው ግብ ሐዋ ርተ ጆ እርሱ ግን እኤዝዘከ ፃዕ እምኔሁ እያለ በገዛ ሥልጣኑ ነውና ቅዱሳን ከሚያደርጉት ተአምራት ጋራ ሊነጻጸር አይገባውም አለ በዚህ ጊዜ ሮማዊ መልስ አጥቶ ዝም አለ ዐምስተኛ ጥያቄ ስሙን ልዮን የሚሉት አንድ ሮማዊ ተነሥቶ ወልደ አብ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ሥጋ ማርያምን በለበሰ ጊዜ ሰይፍ በሰገባው እንዲከተትና እንዲቀመጥ አደረበት እንጅ አልተዋሐደውም በሰላሳ ዘመኑ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በራሱ ላይ ሲቀመጥ መለኮቱ ከትስብእቱ ተዋሐዶ የጸጋ አምላክ ኾነ መዋቲ ትስብእትም የማይሞት ኾነ ከሰላሳ ዘመን በፊት የጸጋ አምላክ ስላልኾነ አምላካዊ ሥራ አልሠራም ከተጠመቀ በኋላ ግን የጸጋ አምላክ ስለኾነ ውኃውን ወይን አደረገ ብዙ የአምላክነት ሥራ ሠራ አለ እንደዚኸውም በንግድ ምልክት መጥቶ እስክንድርያዊ መስሎ በኢትዮጵያ የሚኖር አንድ ሰው ተነሥቶ እንዲህ ሲል ተናገረ እናንተ ኢትዮጵያውያን ቃል ሥጋ በለበሰ ጊዜ በማኅጸነ ማርያም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ የባሕርይ አምላክ ኾነ ትላላችሁ በማኅጸን መንፈስ ቅዱስን ሲቀበል ያየው የለም ሮማውያን ግን እስከ ሰላሳ ዘመን በሰብአዊ ግብር ኖሮ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ ሰው ሁሉ እያየው በራሱ ላይ ስለተቀመጠበት የጸጋ አምላክ ኾኖ የአምላክነት ሥራ ሠራ ይላሉና ከእስክንድርያ ሃይማኖት የሮማ ሃይማኖት ትሻላለች አለ አባ ጳውሊ ሲመልስ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ሲያበሥራት መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል የአብም ኃይሉ ይጋርድሻል ካንች የሚወለደውም ቅዱስ ነው የልዑል የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ብሎ ሦስቱም አካላት በማኅጸነ ማርያም እንደ አደሩ ተናግሯል ማደራቸውም አብ ለአጽንዖ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ ወልድ ለለቢሰ ሥጋ ነው እንጅ ሦስቱ ኹሉ ለለቢሰ ሥጋ ያደሩ አይምሰልህ በዚህ ጊዜ መለኮት ርቀቱን ለቆ ሳይገዝፍ ሳይለወጥ ትስብእትም ግዘፍነቱን ለቆ ሳይረቅ ሳይለወጥ እንደ ነፍስና እንደ ሥጋ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ኾነ ወልድ ለለቢሰ ሥጋ ማለት ይህ ነው አብ ለአጽንዖ ማለትም ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ምሉዕ ስፉሕ ረቂቅ መለኮትን እመቤታችን በጠባብ ማኅጸን እንድትችለው አጸናት ማለት ነው መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ ማለትም ትስብእትን ከአዳም መርገም አንጽቶ ቀድሶ ለተዋሕዶተ መለኮት የበቃ አደረገው ማለት ነው ይህን በማኅጸን በረቂቅ ምሥጢር የሠሩትን አምላካዊ ሥራ በዮርዳኖስ ወልድ ባጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ሲጠመቅ በመታየት አብ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ የሚል ድምጽ በማሰማት መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀምጦ አብ ልጀ ይህ ነው ብሎ የመሰከረለት ወልድ ይህ ነው ብሎ በጣት ጠቅሶ እንደ ማሳየት በመመስከሩ ገልጸውለታል እንጅ እስከዚያ ድረስ ሰላሳ ዘመን መንፈስ ቅዱስ ተለይቶት ኖሮ በዮርዳኖስ አደረበት ማለት አይደለም አለ ያ ሮማዊ መልስ አጥቶ ዝም አለ በዚህ ጊዜ ንጉውሁ ገላውዴዎስ አባ ዝክሪንና አባ ጳውሊን እኔ የክርስቶስ ባሪያ ሃይማኖቴ እንደ ሃይማኖታችሁ ኦርቶዶክስ እስክንድርያዊ ነው ይህነንም እናንተ ታውቁልኛላችሁ ነገር ግን እኛ የሕክምናና የተግባረ እድ ትምህርት የለንም ሮማውያን ብዙ ጥበብ ያውቃሉና ይህን ጥበባቸውን እስኪያስተምሩን ድረስ በሀገራችን እንዲቆዩ ፈቃዳችሁ ይኹን ሲል ለመናቸው አባ ዝክሪ የተባለው መነኩሴ ተነሥቶ እናንተ የኢትዮጵያ ሰዎች እሊህ ሮማውያን በሀገራችን ይቀመጡ ካላችሁ ወደፊት በኢትዮጵያ ላይ የሚደርስባትን ነገር ልንገራችሁ እኒህ ሰዎች ከእህቶቻችን ከልጆቻችን ይወልዳሉ እኒያ ልጆች በድብቅ ያባቶቻቸውን የካቶሊካውያንን ትምህርት ይማራሉ እኛ ወገኖቻችን መስለውን ቅስና ዲቁና ስንሾማቸው የመምህርነት ማዕርግ ስንሰጣቸው ውስጥ ውስጡን የኹለት ባሕርይን ባህል እያስተማሩ ሃይማኖታችንን ይለውጧታል ይህም የተናገርኩት ነገር አይቀርም አምስት ነገሥታት ካለፉ በኋላ ስድስተኛ ንጉሥ ከወደ ዐረማውያን ሀገር መጥቶ ይነግሣል በርሱ ጊዜ ይፈጸማል ሲል ትንቢት ተናገረ ከዚህ በኋላ ከዐፄ ገላውዴዎስ ዐፄ ፋሲል ከዐፄ ፋሲል ዐፄ ሚናስ ከዐፄ ሚናስ ዐፄ ሠርጸ ድንግል ከዐፄ ሠርጸ ድንግል ዐፄ ያዕቆብ ከዐፄ ያዕቆብ ዐፄ ሱስንዮስ ዐፄ ሱስንዮስ ከዐረማውያን ሀገር መጥተው ነገሠ በስድስተኛው ንጉሥ በዐፄ ሱስንዮስ ጊዜ የአባ ዝክሪ ትንቢት ተፈጸመ ጃ የቅብዐት እና የተዋሕዶ ልዩነት ክፍል የኢትዮጵያ ሊቃውንት ከሚሲዮናውያኑ ጋር ባደረጉት ክርክር ሚሲዮናውያኑ ለጊዜው የተሸነፉ መስለው ከክርክሩ ራሳቸውን አሸሹ ከዐጹ ገላውዴዎስ ሞት በኋላ በተሾሙት በወንድማቸው በዐጹ ሚናስ ዘመነ መንግሥትም እንዲሁ ክርክር አድርገዋል በእነዚህ ዘመናት ሁሉ እምነታቸውን በድብቅ ያስተምሩ ነበርና ንጉው የሚሲዮኖችን ፓትርያርክ ኦቢያዶን አስጠርተው ድጋሜ የካቶሊክን እምነት እንዳያስተምር አስጠነቀቁት እጸድቅ ብየ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች እንደሚባለው ሆኖ ኦብያዶ በዚህ የተነሣ የንጉሁን ሥም ማጥፋት እና ከእስላሞች ጋር በምሥጢር እየተገናኘ ንጉሠን ለማስገደል እንዲሁም የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ለማስያዝ ወጥመዱን ያጠምድ ጀመረ ይህ ክፉ ሥራው ስለታወቀ ከጓደኞቹ ጋር ተይዞ በግዞት ተቀመጡ ሆኖም ግን ከዚህ አምልጠው በኢትዮጵያ ዙሪያ ከሰፈሩት ጠላቶቻችን ከቱርኮች ጋራ ተቀላቀሉ ሚሲዮኖቹ ግን የካቶሊክ እምነትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ቆርጠው ተነሥተዋልና ብዙ አማራጮችን ተጠቅመዋል ከዐጹ ሚናስ ሞት በኋላ በዐጹ ዘድንግል ዘመነ መንግሥት በጀ ዓም በአባ ጴጥሮስ ፖኤዝ የሚመሩ ላቲኖች ወደ ሀገራችን ገቡ የፖርቹጋል መንግሥት ባደረገው ውለታ ምክንያት በሀገራችን እንዲቀመጡ ስለተፈቀደላቸው በሀገራችን ተቀምጠው በተለያዩ አጋጣሚዎች ሁሉ እምነታቸውን በድብቅ ማስፋፋት ጀመሩ በዚህ መልኩ ከቀጠሉ በኋላ በይፋ ደረታቸውን ነፍተው ልባቸውን ሞልተው በኩራት እምነታቸውን ማስፋፋት የጀመሩት ግን በዐጹ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት ነበር ፈሊጥ አዋቂው ጴጥሮስ ፖኤዝ የሀገራችንን ቋንቋ ግእዝን ተምሮ ይሰብክ እና ይቀድስ እንደነበር ይነገራል ከንጉው ዘንድም እየሄደ የካቶሊክ እምነትን ቢቀበሉ የፖርቹጋል መንግሥት የጦር መሣሪያን ያስታጥቅዎታል እያለ ይሰብካቸው ነበር ንጉውም በዚህ ተታልለው ለካቶሊኮች የቤተክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ሰጧቸው በኋላም በ ዓም በጴጥሮስ ፓኤዝ እጅ ከነቤተሰቦቻቸው በሮማ ካቶሊክ ሥርዓት ተጠምቀው ካቶሊክነታቸውን በይፋ አረጋገጡ የጴጥሮስ ፓኤዝን ሞት ተከትሎ በሮማው ጳጳስ እጅ ጵጵስና የተሾመው የእስፔኑ ተወላጅ አልፎንሱ ሜንዴዝ በየካቲት ዓም የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ተብሎ ተሰይሞ ወደ ሀገራችን ሰኔ ቀን ቿኗ ዓም ገባ ከዚህ የካቶሊክ ፓትርያርክ ጋር አንድ ረዳት ኤጺስ ቆጾስ እና ጆ ቀሳውስት አብረውት ተልከው ወደ ሀገራችን ገብተዋል ንጉሥ ሱስንዮስ የካቲት ቀን ዓም የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ካቶሊክ እንዲሆን እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በሮም ሥር እንድትተዳደር ዐዋጅ ዐወጁ ከዚህ በኋላ ንጉሁ ከአልፎንሱ ሜንዴዝ ጋር ተባብረው የሚከተሉትን ህጎች አወጡ ወ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች እንደገና እንዲጠመቁ ወ ካህናቱም እንደገና እንዲካኑ ወ አብያተ ክርስቲያናትም እንደገና በሮማውያን እንዲባረኩ ወ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ቅዱሳት ሥዕላት ቀርተው በሮማውያን ሥርዓት የተቀረጹ ምስሎች እንዲቆሙ ወ የሮማውያን የቀን መቁጠሪያ በኢትዮጵያ እንዲሠራበት ወ የአርብና የረቡዕ መጾም ቀርቶ ቅዳሜ እንዲጾምና የቅዳሜ ሰንበትነት እንዲሻር ይህንን ህግ የማይጠብቅ ሁሉ የአካል ቅጣት እንደሚወሰድበት ንጉው ዐዋጅ እንዲያውጁ አልፎንሱ ሜንዴዝ ስለነገራቸው ንጉውም በዚሁ ተስማምተው ዐዋጁን ዐውጀዋል በዚህም የተነሣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጳጳስ የሆኑት አቡነ ስምኦን ለሃይማኖታቸው ተቆርቋሪ የሆኑትን ካህናት መኳንንት እና ምእመናን ሰብስበው ከንጉሠ ጋር ጦርነት ከፈቱ የንጉሠሁን ተከታዮች ለመቀነስም አቡነ ስምኦን ንጉው የአባቶቻችንን ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለውጠዋልና እርሳቸውን የሚከተል እንደ አርዮስ የተወገዘ ይሁንን ብለው የንጉውን ተከታዮች በማውገዝ ድጋፋቸውን አጠናከሩ ሆኖም ግን ድሉ ለንጉሠ ሆነና ጳጳሱም በዚሁ ጦርነት ተገደሉ በዚህም የተነሣ በካቶሊካውያኑ ዘንድ ንዴትን ፈጠረ እና የተዋሕዶ እምነትን በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ ስቃይ አጸኑባቸው ይህንን በክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እና መከራ የሰሙ የጎጃም ቤጌ ምድር የትግራይና የላስታ ሰዎች ሰማእትነት እንዳያመልጠን እያሉ ወደ ሱስንዮስ ዐደባባይ ስለመጡ ብዙ ክርስቲያኖች ተገድለዋል ይህ ጦርነትም ለሰባት ዓመታት ያህል ከተካሄደ በኋላ ንጉሁ ታመሙና አንደበታቸው ተዘጋ ልጃቸው ፋሲልም ወደ ገዳማትና አድባራት በመሄድ አባቴ የክርስቲያኖችን ደም በማፍሰሱ እግዚአብሔር ተቆጥቶበት አንደበቱ ተዘግቷልና ጸልዩለት የምትፈልጉትን ሁሉ አደርጋለሁ አለ በዚህ የፋሲል ልመና የማኅበረ ሥላሴው አምደ ሥላሴ የተባሉ ባሕታዊ የገዳማቸውን መነኮሳት አስከትለው በመሄድ ለሦስት ሱባኤ ያህል በጸሎት በምህላ ቆይተው ጸበል አጠመቋቸው ንጉሁም አንደበታቸው ተከፈተ መናገር ቻሉ በዚህ ጊዜ ለልጃቸው የእስክንድርያ ሃይማኖት ትመለስ የሮም ሃይማኖት ትርከስ ፋሲል ይንገሥ ብለህ ዐዋጅ ተናገርን ብለው ነገሩት እርሱም ዐዋጁን ዐወጀ ህዝቡም ተደሰተ አድባራትና ገዳማትም የደስታ ደወላቸውን ደወሉ በአልፎንሱ ምክንያት የተሰደዱት በየዋሻው በየበረሃው የገቡ መምህራን መነኮሳት ሁሉ መጽሐፎቻቸውን እና ጽላቶችን እየያዙ ወደየቦታቸው ተመለሱ በካቶሊካውያኑ ተታልለው ሃይማኖታቸውን የለወጡትንም ንስሐ እንዲገቡ እያደረጉ ወደ ቤተክርስቲያን መለሷቸው ከዚህ በኋላ ንጉው ሞቱና ልጃቸው ፋሲል ነገሠ ህዝቡ ይበልጥ ደስ አለው አልፎንሱ ግን እስካሁን ድረስ ከሀገራችን አልወጣም ነበር ዐዴ ፋሲል መንግሥቱን ካደላደለ በኋላ የተዋሕዶ ሊቃውንት ከአልፎንሱ ሜንዴዝ ጋር በጎንደር ጉባኤ ተደርጎ ተከራከሩ በዚህም ጉባኤ በዕጨጌ በትረ ጊዮርጊስ መሪነት የተከራከሩት የተዋሕዶ ሊቃውንት አሸነፉ የመጀመሪያ ጠያቂው አልፎንሱ ሜንዴዝ ። ጥያቄ አንተ በራስህ አንቅተህ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ቃል ሥጋ በኾነ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አደረበት መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ የጸጋ ልጅ ኾነ እያልህ ታስተምራለን። የዛሬዎችም በመጽሐፋቸው «ወልደ አብ ገጽ ሀ» አጣ ደሐየ ተቸገረ ዜገ ሲሉ «ይህ የጸጋ ልጅነት የሌለው ባእድ ሥጋ እምቅድመ ዓለም የባሕርይ ልጅነት ካለው መለኮት ጋራ ቢዋሐድ የቃልን ገንዘብ ተቀብሎ ወልደ አብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ልጅነት አገኘ ይህ ልጅነት ያለው ቃል ልጅነት ከሌለው ሥጋ ጋራ ቢዋሐድ በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ ኾነ» ብለዋል ቀጥለውም ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን ሲገልጹ ወልደ አብ ገጽ ጃ ላይ « መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ ቢወለድ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክ የባሕርይ ልጅ ኾነ» በማለት ጽፈዋል። በተጨማሪም ወልደ አብ ገጽ ላይ ፉወልድስ በሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን ከአብ ተቀብሎ ባይወለድ ወልድ በሰውነቱ እንደ አብ ባልገዛም አብም ለወልድ በሰውነቱ አገዛዙን ክብሩን በመላ በሰፋ ባልሰጠውም ነበር» በማለት አብን ሰጭ ወልድን ደግሞ ተቀባይ መንፈስ ቅዱስን ስጦታ ሲያደርጉ ይታያሉ ስለዚህ ነው እንግዲህ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስን ጠቀመው ረባው ማለታቸው መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ባይወለድ ኖሮ ወልድ እንደ አብ እንደ መንፈስ ቅዱስ መግዛት ማዘዝ አይችልም ነበር ማለታቸው ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገዋል ማለታቸው ነውና ከመጀመሪያዎቹ የቅባት ክፍል ጋር አንድነት አላቸው ወልደ አብ ገጽ ቋ ላይ ደግሞ ለመለኮት የማይቀፀል ቃል እንዲህ ብለው ቀፀሉ «ፉበዚህም በባሕርይ ልጅነቱ እኛ ብቻ ተጠቅመንበት አልቀረንም እርሱም ተጠቀመበት እንጂ» ይላሉ። በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ይላሉ። ልዩነታችን ቅብዐቶች የጌታ ልደት በዓል ኹል ጊዜ ታኅሣሥ ቀን መከበር አለበት ይላሉ። የቅብዐት እና የተዋሕዶ ልዩነት ክፍል የዶግማ ልዩነቶቻችን ልዩነት ቅብዐቶች ወልድን ፍጡር ይሉታል እኛ ግን ፈጣሪ ነው እንለዋለን። ፍጡር ደግሞ ማክበር አይችልምና መንፈስ ቅዱስ አክብሮ አምላክ አደረገው ማለታቸው ነው እንደ አብ እንደ መንፈስ ቅዱስ የገዛ ያዘዘ አምላክ የኾነ በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ነው በማለት ቅብዐትን ለቃልም ለመለኮትም ይቀጽላሉ። የቅብዐት እና የተዋሕዶ ልዩነት የዶግማ ልዩነቶቻችን ልዩነት ቅብዐቶች ለቅዱሳን እና ለመስቀል ስግደት አይገባም ይላሉ እኛ ግን ይገባል እንላለን። የቅብዐት እና የተዋሕዶ ልዩነት ክፍል የዶግማ ልዩነቶቻችን ልዩነት ቅብዐቶች ወንጌል በአሚን ብቻ ታድናለች ይላሉ እኛ ግን አሚን ያለምግባር ብቻውን አያድንም እንላለን። ቅብዐቶች ወልደ አብ ገጽ ላይ ። የቅብዐት እና የተዋሕዶ ልዩነት የዶግማ ልዩነቶቻችን ልዩነት እነርሱ ፈበቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ» እኛ ደግሞ ፈበተዋሕዶ ከበረ» እንላለን። እኛ የተዋሕዶ ልጆች በተዋሕዶተ ቃል ሥጋ ክቡር አምላክ ሆኗልና በተዋሕዶ ከበረ እንላለን ይህንንም ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ በድርሳኑ ድርሳን ቁጥር ላይ እንዲህ ይላል «አብን በልብነት መንፈስ ቅዱስን በእስትንፋስነት ገንዘብ ለማድረግ ሥጋ ቃልን ተዋሐደ» ስለዚህ ሥጋ የአብን ልብነት የመንፈስ ቅዱስን እስትንፋስነት ገንዘቡ ያደረገው ቃል ስለተዋሐደው እንጅ መንፈስ ቅዱስ በቅብዐትነት ስላከበረው አይደለም ማለት ስለዚህ ነው ቅዱስ ቄርሎስ በሃይማኖተ አበው ስምዐት ላይ «ወካዕበ ይቤ እስመ ክርስቶስ ኢተቀብዐ በእንተ መፍቅድ ዘቦቱ አላ ለሊሁ ቀባዒ ውእቱ ወዐርገ ኀበ ሥልጣነ መለኮቱ እንዘ ሰብእ ውእቱ ወለሊሁ እግዚአብሔር አምላክ ተብህለ በእንቲአሁ ከመ ውእቱ ተለዐለ ፈድፋደ በእንተ ትህትና ወሕጸጽ እንተ ዘትስብእት ወንዴት ወለሊሁ ጸገዎ ስመ ዘላዕለ ኩሉ ዝንቱ ዘኮነ በህላዌ ከመ አምላክ ከመ ያልዕለነ ለነሂ ዓዲ ኀበ ሀሎ ዝኩ ዳግመኛ ክርስቶስስ ክብር መሻት ኖሮበት አልከበረም እርሱ ራሱ አክባሪ ነው እንጅ ሰው ቢኾንም በባህርይ ክብሩ ከበረ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር አምላክ ነው ሥጋ ትሁት ሕጹጽ ነዳይ ስለሆነ ተለዐለ ተብሎ ተነገረለት ከሁሉ በላይ የሆነ ስምንም እሱ ራሱ ሰጠው ተባለ ይህም የሆነ በባህርይ ተዋሕዶ ነው አምላክ እንደሆነ እኛንም እሱ ወደ አለበት ያቀርበን ዘንድ» ይላል። እኛ ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ» የምንል የተዋሕዶ ልጆች ግን በክብር መለያየት የለባቸውምና ቃል ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ በኾነ በራሱ ክብር የተዋሐደውን ሥጋ አከበረው እንላለን። አካላዊ ቃል ፈጥሮ የተዋሐደውን ሥጋ ማክበር የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው ይላሉ። ፉወልድ ቅብዕ ማለትና መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ማለት በተዋሕዶ የባሕርይ አምላክ ኾነ ማለትና በቅብዐት የባሕርይ ልጅ ኾነ ማለት መገናኘት የማይቻላቸው ልዩ ልዩ ነገሮች መኾናቸውን ሊረዱ አልቻሉም» መድሎተ አሚን ገጽ ላይ ሪእንዲያውም በጠቅላላው ዛሬ በኢትዮጵያ ኹሉም ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኹለት ልደት በተዋሕዶ ከበረ የሚል ነው እንጂ ከዚህ ወጥቶ አንድ አካል ኹለት ባሕርይ በቅብዐት የጸጋ ልጅ በቅብዐት የባሕርይ ልጅ የሚል አይገኝም» በአጠቃላይ «አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ብሎ ማመን የሚከተሉትን ስህተቶች ያመጣል። ኛ የአካላት ግብር ስም ኹለት ጊዜ እንደተሰጣቸው ያሳያል ዘመን ሳይቆጠር ቀድሞ «አብ ቀባዒ ወልድ ቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቀባዒ» ድኅረ ዓለም ወልድ በሥጋ ማርያም በተገለጠ ጊዜ ደግሞ «አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ» ሆኑ ማለት ነው ይህ ደግሞ የግብር መቀዳደምን እና መለዋወጥን ያሳያል ኛ ዮሐንስ አፈወርቅ በድርሳኑ ምእራፍ ቁጥር ላይ ። እዚህ ጽሑፍ ላይ በዋናነት ሦስት መሠረታዊ ስህተቶችን እንመለከታለን ኛ በመጻሕፍት ተጽፎ የማናገኘው «አብ ወልድን በማኅጸነ ማርያም በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ወለደው» የሚል ስህተት አለበት ኛ መጻሕፍት ፈለሰማያዊ ልደቱ እናት ለምድራዊ ልደቱም አባት አትሹለት» እያሉ እዚህ ላይ ግን ፈለምድራዊ ልደቱ አባት ሽተውለታል» ስለዚህም ኹለተኛ ስህተት ብለን ቆጠርነው ኛ የተቀመጠው ምሳሌ «ሦስት ጊዜ የተቆጠረውን ልደት ኹለት» ብለን እንድንቀበለው የሚያደርግ ማስረጃ አለመሆኑ በእነዚህ ቅደም ተከተሎች በማስረጃ እያስደገፍን የዚህን ስህተት እናጋልጣለን «ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ» የምንል ክርስቲያኖች የምናምናቸው ልደታት ኹለት ናቸው እነዚህም ኛ ቅድመዓለም ባሕርይ ዘእምባሕርይ አካል ዘእምአካል ሳይቀድም ሳይከተል በዚህን ጊዜ ተወለደ በማይባል ረቂቅ ጥበብ ወልድ ከአብ ያለ እናት የተወለደው ቀዳማዊው ልደት ነው ኛ የአዳምን በደል ለማጥፋት ከሴት የሚወለድበት ዘመን በደረሰ ጊዜ በኅቱም ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ በተዋሕዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለአባት የተወለደው ደኃራዊው ልደት ነው ሊቃውንቱ «ፉቀዳማዊ ልደቱ በደኃራዊ ልደቱ ታወቀ» ይላሉ ሁለቱም ልደታት ከሰው ኅሊና በላይ ከመመርመርም እጅግ የራቁ ናቸው ማንም እነዚህን ልደታት መርምሮ አይደርስባቸውም በረቂቅ ምሥጢር የተከናወኑ ናቸውና ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን የምትቀበላቸው የምታምናቸው የምታስተምራቸው በመጻሕፍት የጻፈቻቸው የጌታ ልደቶች ቅድመ ዓለም ያለእናት ከአብ በመለኮት የተወለደው ልደት እና ድኅረ ዓለም ያለአባት ከቅድስት ድንግል ማርያም መለኮት በሥጋ የተወለደው ልደት ነው ከዚህ ውጭ በቅብዐቶች ዘንድ ። ስለዚህ ሥጋ ወልደ አብነትን የአብ ልጅ መባልንን ገንዘቡ አደረገ አለ ሊቁ ይህን ምሥጢር አርቀቆ የተናገረበት ግሩም ትምህርት እንደኾነ በዚህ እንረዳለን ቅብዐቶች ከላይ እንደጻፍነው ፈእምቅድመዓለም በመለኮቱ ተወለደ ብለናል ኋላም በማኅጸን በሰውነቱ ከአብ ተወለደ እንላለን ዳግም ከእመቤታችን በስጋ በጎል ተወለደ እንላለን ይህማ ሦስት አይደለምን እንደምን ኹለት ነው ቢሉ እምቅድመዓለም በመለኮቱ የተወለደው ልደትና ዛሬ በማኅጸን በሥጋ በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ የተወለደው ልደት አንድ ልደት ይባላል እንጅ ኹለት አይባልም። እዚህ ላይ በግልጥ የምንመለከተው ሦስት ልደታትን ማመናቸውን ነው መጻሕፍት «ኹለት ልደታትን እናምናለን» ብለው ስላጠሩባቸው ለመንፈራገጥ አልመች ቢላቸው ሦስት ጊዜ ቆጥሮ ኹለት ማለት ይገባል ብለው ተናገሩ እነርሱ የሚጠቅሷቸው በግልጥ የተቀመጡት የጌታ ልደቶች እነዚህ ናቸው ኛ እምቅድመ ዓለም በመለኮቱ የተወለደው ልደት ኛ በማኅጸን በሥጋ በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ የተወለደው ልደት ጀኛ ከእመቤታችን በስጋ በጎል ተወለደ በማለት ሦስት ልደታትን አስቀምጠውልናል ከእነዚህ ልደታት መካከል ኛው ልደት በየትኛውም መጽሐፍ ተጽፎ እንደማይገኝ ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች በማስረጃ በማስደገፍ ጽፈናል እነርሱ እንደሚሉት ኛ እና ኛ ላይ የተገለጡት ልደቶች አንድ ተብለው ይቆጠራሉ እንጅ ኹለት አይባሉም ይላሉ ለምን ለሚለው መልስ ሲመልሱ «ኹለት ጊዜ ቆጥረነው አንድ ማለታችን እንዴት ነው ቢሉ እምቅድመዓለም በመለኮቱ የወለደው አብ ነው። ወላዲው ተወላዲው ዛሬም የተወለደበት መንፈስ ቅዱስ ያ የጥንት የባሕርይ ሕይወቱ ስለአልተለወጠ አንድ ልደት ይባላል እንጅ ኹለት ልደት አይባልም» ብለው መከራከራቸው አይቀርም ነገር ግን ወላዲው አብ ይኹን ተወላዲውም ወልድ ይኹን አይቀየር አይለወጥ እንጅ ልደቱ ግን ለየቅል ነው እንላቸዋለን ምክንያቱም ። ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው ምነው ይህስ ቢኾን ወልድ በአብ ያልተወለደ በራሱ ያልተወለደ ስለምን በመንፈስ ቅዱስ ተወለደ ቢሉ ይህስ ወላዲ በሚመስለው ሕይወት ይወልዳል እንጅ በማይመስለው አይወልድም ለዚህም ምሳሌ ያስረዳል እነሆ ዛሬ በደመ ነፍስ ሕያዋን የሆኑ እንስሳ ከእንስሳ ይወለዳሉ በነባቢትም ነፍስ ሕያው የኾነ ሰው ከሰው ይወለዳል መንፈስ ቅዱስ ለአብ ሕይወቱ ነው በደመ ነፍስ ሕያው ያልኾነ ከእንስሳ በነባቢት ነፍስ ሕያው ያልኾነ ከሰው እንዳይወለድ እንደዚህም ኹሉ በመንፈስ ቅዱስ ሕያው ያልኾነ ከአብ አይወለድምና ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ከአብ ተወለደ» ይላል እስኪ ቃል በቃል እንመልከተው ወ መን የባሕርይ ልጅ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው ኹላችን እንደምናውቀው በከዊን አብን «ፉልብ» ወልድን «ፈቃል» መንፈስ ቅዱስን «እስትንፋስ» እንላለን የአብ ፈልብነት» ከወልድ «ፉቃልነት» ከመንፈስ ቅዱስም «ሕይወትነት እስትንፋስነትን» አይቀድምም አይከተልምም በተመሳሳይ የወልድ «ቃልነት» ከአብ «ልብነት» እና ከመንፈስ ቅዱስ «እስትንፋስነት» አይይቀድምም አይከተልምም የመንፈስ ቅዱስም «ሕይወትነት ርእስትንፋስነትን» ከአብ ፉልብነት» ከወልድ «ቃልነት» አይቀድምም አይከተልምም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ለአብ እና ለወልድ እስትንፋሳቸው ነው ማለት የባሕርይ ሕይወታቸው ነው ማለት ነው በቅብዐት እምነት ውስጥ ግን ። ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ» ይላሉ እንግዲህ ፈወልድ» ማለት ልጅ ማለት እንደኾነ እናውቃለን ልጅነቱም ከአብ የባሕርይ ልጅነት ነው ይህ ፈወልድ»ን የሚለው ስም አብ «አብ» ከተባለበት መንፈስ ቅዱስም «መንፈስ ቅዱስ» ከተባለበት ጥንት ከሌለው ዘመን ስሙ አይቀድምም አይከተልምም ስለዚህ ፈወልድ» የሚለው ስም የተገባው የኾነ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ አይደለም ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜስ «። ስለዚህ ይህ ህልውና ቀድሞ ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ ያለ በመሆኑ እና ወልድ ከዚህ ህልውናው የተለየበት ጊዜ ስለሌለ «ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ» ቢባል ክህደት ነው ሪበቅብዐት የባሕርይ ልጅ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው» ማለትን ከማን እንደተማሩት አይታወቅም አብ በመለኮቱ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ወለደው እንጅ ድኅረ ዓለምም ዳግመኛ በሰውነቱ ከእናት አልወለደውም በሰውነቱስ ከአብ ዳግመኛ ተወልዶ ቢኾን ኖሮ ፉወልደ አብ» መባል «ወልደ ማርያም» ከመባል በበለጠበት ነበር ነገር ግን ቅድመ ዓለም ፈወልደ አብ» የተባለው ድኅረ ዓለም ፉወልደ ማርያም» ቢባል እኩል ነው አንጅ አይበላለጥም እንዲያውም ሊቃውንቱ ሲያመሰጥሩ «ቀዳማዊ ልደቱ በደኃራዊ ልደቱ ታወቀ» ይላሉ ይህ ማለት «ወልደ አብ» መባሉ ። ሰው ቢወለድ ከእናት እና ከአባቱ ዘር ነው እንጅ በድንግልና አይደለም እንስሳትም ከእንስሳት ቢወለዱ እንዲሁ በተራክቦ ነው እንጅ በድንግልና አይደለም የወልድስ ከድንግል ማርያም መወለድ በማክሰኞ ቀን ኅቱም ምድር ለታብቁል ባለው ቃል አብቅላ አፍርታ እንደተገኘች ያለ ነው ሰው ከሰው የተለየ እንስሳን እንስሳም ከእንስሳ የተለየ ሰውን ይወልዱ ዘንድ ፈጣሪ ተአምሩን ከገለጸ ይወልዳሉ ይህንንም በተለያዩ ዜናዎች እየሰማን እና እየተመለከትን ነው ስለዚህ ይህ ምሳሌ «ፉወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወለደ ማለት ነው» ለሚለው ማስረጃ ሊኾን አይችልም ፈእንደዚህም ኹሉ በመንፈስ ቅዱስ ሕያው ያልኾነ ከአብ አይወለድምና ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ከአብ ተወለደ» ብለው ፖ ክህደታቸውን በአራት ነጥብ ይቆልፉታልኽመንፈስ ቅዱስ ሕያው ያልኾነ ከአብ ኣልተወለደ በቀዳማዊ ልደቱ አብ ወልድን የወለደው የባሕርይ ሕይወቱ ከኾነው መንፈስ ቅዱስ ሕያው ከኾነ በኋላ ነውን ቢሏቸው መልስ የላቸውም በነገራችን ላይ ፈበግብረ መንፈስ ቅዱስ» የሚለውን የሊቃውንቱን ትምህርት በማጣመም ነው ለራሳቸው እየተጠቀሙበት ያሉ። እስኪ አሁንም ቃል በቃል እንመልከት ፉይህ የጸጋ ልጅነት የሌለው ባእድ ሥጋ እምቅድመ ዓለም የባሕርይ ልጅነት ካለው መለኮት ጋራ ቢዋሐድ የቃልን ገንዘብ ተቀብሎ ወልደ አብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ልጅነት አገኘ» ሥጋ ከፈጣሪው የጸጋ ልጅነትም የለውም ነበር ማለታቸው አዳም ስለበደለ እና ጸጋ እግዚአብሔር ስለተገፈፈበት ነው ኾኖም ግን እምቅድመዓለም የባሕርይ ልጅነት ያለው መለኮት ሲዋሐደው የቃልን ገንዘብ ገንዘቡ አደረገ እና ወልደ አብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ልጅነትንም አገኘ ብለው ይደመድማሉ በጣም ጥሩ ነው አሁን ላይ መለኮት ሲዋሐደው ሥጋ አምላክ ኾነ ክቡር ኾነ የቃል ገንዘብ ገንዘቡ ኾነ እና ወልደ አብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ማለት ነው ይህ ነው በተዋሕዶ ከበረ ማለት። ነገር ግን ቀጥለው ይህንን ያፈርሱትና «ፉይህ ልጅነት ያለው ቃል ልጅነት ከሌለው ሥጋ ጋራ ቢዋሐድ በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ ኾነ» ከላይ ፉየቃልን ገንዘብ ተቀብሎ ወልደአብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ኾነ ልጅነት አገኘ» ብለው ነበር አሁን ደግሞ እንደገና ተመልሰው «በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ ኾነ» ብለው የሚጋጭ ሐሳብ አስፍረዋል ለዚህ ሐሳባቸውም የሚደግፍ ማስረጃ ብለው ሰውን ለማደናገር ግዕዙን ብቻ ጠቅሰው አማርኛውን ሳያስቀምጡት አለፉ አብዛኛው ሕዝብ ግእዝን እንደማይችል ስለሚያውቁ እንዲህ ይላልሳ እያሉ ያወናብዳሉ «እንዘ ባዕል ውእቱ በኩሉ አንደየ ርእሶ እን ጳውሎስ ኛ ቆሮ ም ቁጀ» ፍችውም «ፉሃብታም ሲኾን እናንተ በርሱ ድህነት ባለጠጋዎች ትሆኑ ዘንድ ስለእናንተ ደሃ ኾነ» የሚል ነው እነርሱ ግን ሙሉውን ሳይጠቅሱ ቆርጠውታል ሆኖም ይህ ጥቅስ «ፉቃል በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ» ለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለውም ስለዚህም ማስረጃነቱን ለማወናበድ ካልተጠቀሙበት በቀር ምንም ማስረጃነት የለውም ማስረጃ ሊኾን የማይችለውም ነድየ የሚለው የሚስማማው ለሥጋ ነው እንጅ ለመለኮት አይደለምና ቃል ከሥጋ ጋር በተዋሐደ ጊዜ የሥጋ ንድየት በቃል ባዕልነት ተወግዷል ስለዚህ የዚህ ማስረጃነት ተቀባይነት የለውም ቀጥለውም «ፉስለዚህ ከእምቅድመ ዓለም ልደቱ ድ ለማድረግ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወቱን በመላ ተቀብሎ ከአብ ተወለደ እንጅ የቀደመ ልጅነቱስ አልተነሣውም» ይላሉ በመቀጠልም «ወልድስ በሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን ከአብ ተቀብሎ ባይወለድ ወልድ በሰውነቱ እንደ አብ ባልገዛም አብም ለወልድ በሰውነቱ አገዛዙን ክብሩን በመላ በሰፋ ባልሰጠውም ነበር» ብለው ወልድን ከአብ ያሳንሳሉ አብ ወልድ እና መንፈ ቅዱስ በመግዛት አንድ ናቸው ይህ ምስጢረ ሥላሴ ነው ይህ የመግዛት ሥሪ ወልድ ሥጋን በለበሰ ጊዜ አልተቋረጠም ስለዚህ ወልድ የመግዛት አንድነቱን ይዞ ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ ሥጋን ቢዋሐድ ሥጋ የመግዛት ሥልጣንን ከወልድ ያገኛል ገንዘቡ ያደርጋልን እንጅ ከአብ አያገኝም አስቀድመን እንደተናገርነው ወልድ ባለበት አብና መንፈስ ቅዱስ አሉና አብ ለወልድ የመግዛት ስልጣንን የሚሰጠው ወልድም የመግዛት ስልጣንን የሚቀበል አይደለዎ ምክንያቱም ከመግዛት አንድነቱ የተለየበት ጊዜ ስለሌለ አሁንም በግእዝ ጠቅሰው ለማወናበድ «ኢይሁብ ክብርየ ለባዕድ ለተሳትፎ ወስብሐትየ ለግልፎ እን ኢሳ ምዌ ቁ» ይላሉ ትርጉሙን እንመልከት «እኔ እግዚአብሔር ነኝ ክብሬን ለሌላ ምስጋናየንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም» የሚል ነው ቆርጠው ስላስቀሩት ነው እንጅ እስኪ አስተውሉ ወገኖቼ። ለዚህም ማስረጃቸው ያው የተለመደው ነው «አኮ ዘይሁብ እግዚአብሔር ዳቫ ዌጩጩሜሯሙጭ ብ » እዴሁ እን ወን ዮም ቁ ቋ» ትርጉሙም «ፉእግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና አባት ልጁን ይወዳል ኹሉንም በእጁ ሰጥቶታል» የሚል ነው አንድምታውን ስትመለከቱ ፈከእግዚአብሔር አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ተወልዶ የመጣ እሱን እግዚአብሔርነቱን ያስተምራል ሀብተ መንፈስን በልክ የሚሰጥ አይደለምና» ይላል ተመልከቱት ኹላችሁም ሌላው የጠቀሱት «ፉወረሰዮ ወራሴ ለኩሉ እን ጳው ዕብ ም ቁ» የሚል ነው ትርሙም «ኹሉን ወራሽ ባደረገው» ማለት ነው እንግዲህ እዚህ ላይ ኹለቱም ቦታዎች ላይ ያስቀመጧቸው ጥቅሶች «ፉወልድ መንፈስ ቅዱስን ከአብ ተቀብሎ ቢወለድ ግን እንደአብ ገዛ አዘዘ አብም ለወልድ በሰውነቱ አገዛዙን ክብሩን ሰጠው» የሚል አይደለም ስለዚህ ማስረጃ ተብለው የተቀመጡት ኹሉ ማስረጃነት የሌላቸው የመጽሐፉን ገጽ ብቻ ለመጨመር የተጻፉ እንደሆኑ ልብ ይሏል ወልደ አብ ገጽ ላይ ፈመንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ተሠጠ ማለት ነው መሠጠቱ ወርቅ ተመዝኖ ከብት ተቆጥሮ እህል ተሰፍሮ እንዲሰጥ እንደዚያ ተሰጠ ማለት ማለት ነውን ቢሉ እንዲህስ አይደለም እንዴት ነው ቢሉ ጥንተ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ ለወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወት ኾነው ማለት ነው በእንተዝ ይትበሃል ከመ ነሥአ መንፈሰ ዚአሁ ዘተነግረ በኢሳይያስ ነቢይ እንዘ ይብል መንፈሰ እግዚአብሔር ላዕሌየ ቀብዓኒ በእንተዝ ሰበከ እንዘ ይብል እስመ መንፈስ ዘዚአየ በህላዌ ለሊሁ ኀደረ ላዕሌየ በእንተ ዝንቱ ወለምንትኑ ተሰመይኩ መሣሐ እንበለ ዳዕሙ ሶበ ኮንኩ ሰብአ እን ሳዊሮስ ዘአንጾ ሃ አ ክ ቁንኃ ይላል ሙሉ ንባቡ እንግዲህ እንደተለመደው ቃል በቃል ለማየት እንሞክር መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ኾነ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ተሠጠ ማለት ነው መሠጠቱ ወርቅ ተመዝኖ ከብት ተቆጥሮ እህል ተሰፍሮ እንዲሰጥ እንደዚያ ተሰጠ ማለት ማለት ነውን ቢሉ እንዲህስ አይደለም እንዴት ነው ቢሉ ጥንተ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ ለወልድ በሰውነቱ የባሕርይ ሕይወት ኾነው ማለት ነው» በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ፉመንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ኾነ» የሚል ትምህርት የለም በቤተክርስቲያናችን ካሉት ምስጢራት መካከል አንዱ «ሜሮን» ነው በዚህ ሜሮን በሚባል ቅዱስ ቅብዐት ላይ መንፈስ ቅዱስ ያድርበታል መንፈስ መንፈሶ በመስፈርት አላ አብሰ ያፈቅር ወልዶ ወኩሎ ኩነኔሁ አወፈዮ ለወልዱ ቅዱስ ያከብረዋል እንላለን እንጅ ፈመንፈስ ቅዱስ ቅብዐ ሜሮን ነው» ብለን አልተማርንም በሐዋ ሥራ ላይ እንደምንመለከተው መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ አደረባቸው እንላለን እንጅ ፉሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ሆኑ» አንልም ምክንያቱም የሚያድርባቸው በጸጋ ነውና ስለዚህ ይህ አስተምህሮ የእኛ አይደለምና በአንዲት ገዳማችን ስም እንዲህ ዓይነቱን ኑፋቄ ማውጣት ድፍረት ካልኾነ በቀር ሌላ ምን ሊባል ይችላል። የምንድንበት ይህ ነው የሚፈውሰን ይህ ነው የጎበኘን ይህ ነው» ይላል እንግዲህ ኹላችሁ እንደምታዩት ቆራርጠው በጠቀሱት ጥቅስ መንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ የባሕርይ ሕይወት ኾነው የሚል ትርጉም አንድም ቦታ ተጽፎ አላገኘንም ፈበባሕሬዬ ገንዘቤ የሚኾን መንፈስ ቅዱስ በህልውናየ ጸና ብሎ አስተማረ» ይላል እንጅ ዳግመኛ መንፈስ ቅዱስን ተቀበልሁ አላለንም ሰው ስለኾነ ይህንን ተናገረ ክርስቶስ የተባለው ሥጋና መለኮት ከተዋሐዱ በኋላ ነው እና ከተዋሕዶ በፊት ክርስቶስ አልተባለም ነበርና አሁን ግን ሲዋሐድ ክርስቶስ ተባለ ስለዚህም ሰው በመሆኑ ፉበእኔ ህልው ሆኖ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ በህልውናየ ጸና ለሥጋየ ገንዘቡ ኾነ» አለን እንጅ እነርሱ እንደሚሉት ዳግመኛ መንፈስ ቅዱስን ተቀበልሁ አላለንም ፈዳግመኛ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ» የሚሉት በወልድ ህልው ሆኖ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ወዴት ሄዶ ነውን እዚህ ላይ ማስተዋል ያስፈልገናል ዋናው የክህደታቸው ምንጭ ይህ ስለኾነ እኛ የምንለው መንፈስ ቅዱስ ለአብ እና ለወልድ የባሕርይ ሕይወታቸው ነው ይህም ጥንት ከሌለው ዘመን ጀምሮ በሰው ህሊና በማይመረመር አምላካዊ ጥበብ ማለት ነው ስለዚህ ወልድ ከሥጋ ጋር ሲዋሐድ ይህ የወልድ የባሕርይ ሕይወቱ የኾነው የመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ለሥጋ ገንዘቡ ኾነ ነው እነርሱ የሚሉት ደግሞ ወልድ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ ዳግመኛመንፈስ ቅዱስን ሕይወቱ አደረገ ነው እኛ የምንጠይቀው ያ በቃል ህልው ሆኖ ይኖር የነበረው መንፈስ ቅዱስ የት ሄዶ ነው ዳግመኛ አከበረው የሚባለው። ስለዚህ ላከኝ አለ መንፈስ ቅዱስ ገንዘቡ ኾነ መባሉ ቃል ሰው ስለኾነ ነው ሰውማ ባይኾን ኖሮ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ህልው እንደኾነ መንፈስ ቅዱስ በባሕርየ መለኮት ገንዘቡ ነውና እንደምን ገንዘቡ ኾነ ይባላል አብ በወልድ መንፈስ ቅዱስ ህልው መሆኑን እንደተናገረ» ሳዊሮስ እዚህ ክፍል ላይ የተረጎመው ኢሳ ላይ ያለውን ቃል ነው እንግዲህ ሳዊሮስ በግልጽ እንዳስቀመጠልን መንፈስ ቅዱስ በወልድ ህልው ሆኖ ይኖራል ያ ህልው ሆኖ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ወልድ ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ ለሥጋ ገንዘቡ ኾነ ማለት ነው እንጅ ዳግመኛ በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚል ትምህርት አላስተማረም እንዲያውም እዚሁ ክፍል ቁጥር ላይ ሊቁ ሳዊሮስ እንዲህ ይላል ። በዚህም ግብር ተዋሕዶ ጠፍቶ ከነቢያት እንደ አንዱ አልኾነም መንፈስ ቅዱስ ያደረበት አይደለም» ይላል ስለዚህ የት ቦታ ላይ ነው ወልድ መንፈስ ቅዱስን ዳግመኛ ተቀብሎ አብ ከማኅጸነ ማርያም ወለደው የሚለው ትምህርት ያለው።