Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

ህይወተ ማሪያም ድንግል.pdf


Advertisement
  • word cloud

ህይወተ ማሪያም ድንግል.pdf
  • Extraction Summary

ሰማያውያኑም ሆኑ ምድራውያኑ በእነዚህ የተወሰኑ በእነዚህ ዓለማት የሚያድሩ ናቸው አንዱ ወደ ሌላው ገብቶ ከተወሰነለት አልፎ እንዳይኖር አግዚአብሔር በልዩ ጥበቡ አንዱን መሠረት አንዱን ግድግዳ ሌላውን ጣራ አድርጐ አያይዞታል እንደ መንበር ሆነው የተሠሩ በመሆናቸው ሁል ጊዜ ቅዳሴ አይቋረጥም ሙሴ በደብረ ሲና ያያቸው ሰባቱ የአሳት መጋረጃዎችም የሚገኙት በዚህ ቅዱስ ቦታ ነው እርሱ ደግሞ ንጉሥ አንደ መሰከረው መድኃኒት ነው ፌኢጮ ጮጮ ሙጨ የ ጾመ ሚቹ ኣመ የማቴ ወንጌል ትርጓሜ ሕደወተ ማርያም ሯኀገል በእሊህና መሰል ነገሮች ገነት ብለናታል የዕረፍት ቦታ ናትና በገነት ያሉ ነፍሳት በተድሳ በደስታ ይኖራሉ ኃጥአን ከቦታቸው ሆነው አሻቅበው እያዩ የተሰጣቸውን ጸጋ ያደንቃሉ ሉቃ እመቤታችንም ለኛ ለኃጥአን ዕረፍትን ያስገኘት ገነት ናት።ለጊዜው ያይደለ ለዘለዓለም ማረፊያው ገነት አመቤታችን ናትና በፍጥረታት ልማድ ከእናትና ከአባቷ በሥጋና በደም ተከፍላ በነባቢት ነፍስ ሕያው የሆነው ሰውም ጽድቅን ሲመሠርት እና ሕይወትን ወደ ዓለም ሲያስገባ ብቻውን ሆኖ ነው በዚህ ጊዜ ከሁሉም በላይ የመረረውን ሐዘን ገፈት ቀማሽ እናቱ ድንግል ማርያም ናት ምክንያቱም እናቷ ሔዋን መርገም በእርሷ ስለተጀመረ ክፉኛ ልቧ በሐዘን ነዶ ተስፋዋም ተወግዶ የመጀመሪያውን ሐዘን የቀመስሰችው እርሷ ናትና በእናቷ ፈንታ የተፈጠረችው አዲሲቱ ሔዋን አመቤታችን የእናቷን የተጀመረ ሐዘን ለማደማደም መሪር እንባን አነባች የሔዋን ለቅሶ ነፍስ ገዳዩንና አስለቃሹን ሰው ቃኤልን አስገኝቷል የአመቤታችን ለቅሶ ግን የስሙ ትርጓሜ ፍሥሓ ወሐሴት የሆነውን ዮሐንስን በልጅነት አስገኝቷል ከዚያም አልፎ ሁላችንን ጠቅሟል እንዴት ከተባለ የሙት ልጆች እንዳንሆን ድንግሊቱን እናት አድርጐልናልና ነው አባቶቻችን እንደነገሩን አነኋት እናትህ ማለት በዮሐንስ ግብር ጸንተው ለሚኖሩ እስከ አለተ ምጽአት ለሜነሱ ደቀ መዛሙርት የተገባ ቃል ኪዳን ነውና በጌታ ያመኑ ከቃሉ ግሩምነት የተነሣ መቀበል አቅቶአቸው ሕዝቡ በሸሹ ጊዜ አቤቱ ወደ ማን እንሄዳለን ብለው የቀሩት ደቀ መዛሙርቱ ኑሮ ውስጥ እመቤታችንም ነበረችበት በበዓለ ሃምሳ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ አመቤታችንን በመካከላቸው አንደ ታቦት አድርገዋት እንደነበር ታሪክ ምስክር ነው። በዚህም ዓመት ሲሆናት ለአምላክ አናትነት መታጨቷ የሔዋን ደኅንነቷን ዳግማዊት ሔዋን አርሷ መሆኗን ሲያጠይቅ ነው። ብለው በመፍራት እናጠፋለን ብለው የቀረቡትን አይሁድ በመቅጣት የእግዚአብሔር መላክ አምጥቶ ሰጥቶአቸው አነሱም ደስ ብሎአቸው ተቀብለው ዕለቱን ቀብረዋታል የተነሳችውም እነሱ ቀብረዋት ከሄዱ በቷላ ነሐሴ ቀን ዓም በዚሁ ዕለት በዕለተ እሁድ ነውና ኛ በሐዲስ ሥጋ ዳግመኛ ሞት የማያሰጋው ሥጋ መነሣቷን ያጠይቃል ከፍጡራን መካከል ዳግም ሞት የሌለበት አማናዊ ትንሣኤ የሚደረገው በፅለተ እሑድ ብቻ ነው።በመጨረሻ ዘመን የማታልፍ ፅለተ አሁድ ብቻ ናት ።

  • Cosine Similarity

ወደሕይወት ዛፍ የምታደርሰው መንገድ አኮ እመቤታችን ናት የሕይወት ዛፍ ልጂ ክርስቶስ ነውና ሁላችን ተመግበነው በሕይወት አንኖር ዘንድ አስጠብቆ እስከ ጊዜው ያቆየልን ጊዜው ሲደርስ ግን እኔ የወይን ግንድ ነኝ ብሎ ዮሐ ራሱን የገለጠልን በኃጢአት ሳሉ ሊመገቡት የማይገባ በኃጢአት ሳሉ ቢመገቡት ፍርድን የሚያመጣ እውነተኛ የጽድቅ ምግብ ነው ቆሮ ንግሥቲቱ የወርቅ መጎናፀፊያዋን ለብሳ በቀኝ ትቀመጣለች ብሎ አስኪገልጣት ድረስ የመንፈስቅዱስ ጥበቃ ያልተለያት የዲያብሎስ ሽንገላ ያልተቃወማት ንጽሕት ናትና ከፍጥረት ሁሉ በላይ ክብራን ከፍ አድርገን እንናገርላታለን የዛሬውን አያድርገውና በሀገራችን የበሉበት እቃ እንኳን ክቡር ነው አመቤታችን ደግሞ ከዚያ በላይ ሕደወተ ማርያም ደኀግስ የሕይወት እንጀራን ያስገኘችልን የኤልያስ መሶበ ወርቅ ናት ነገ ስለዚህ እንወዳታለን እናከብራታለን እንዲያውም ክብሯን ለመግለጥ ቢያቅተን እንዲያው ለጥ ብለን እንስግድላታለን ለፍጡር አይሰገድም የሚለኝ እንዳይኖር እንኳን ማደሪያው ለሆነች አመቤት አግሮቹ ለቆሙበት ሥፍራ እንኳን እንድሰግድ በመጽሐፍ ታዝዣለሁና መዝ እንግዲህ ምን እንላለን ሕዝቅኤል ያያትን አዳራሽ ቁራዎች ቢከቧት ምን አደረጉ እንዲያው እነሱ እየታጨዱ ወደቁ እንጅ ዛሬም የእመቤታችንን ክብር ያቃለልን መስሏቸው ተረፈ ቁራዎች ዙሪያዋን ከበው መጽሐፍ ይጽፋሉንግግር ያደርጋሉ ግን በአዳራሷ ላይ ቅንጣት ታክል ነውር መጨመር አንደማይችሉ የምናገርበት አጋጣሚ ቢሆነኝ ብዬ እኔም አባቶቼ ስለእመቤታችን ከተናገሩት የውዳሴ ውቅያኖስ ቀድቼ እንደ ክብሯ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በረዳኝ መጠን በማብዛት ያይደለ በማሳነስ በማስረዘም ያይደለ በማሳጠር ጥቂት ቃላትን ተናግሬአለሁና እንድታነቡልኝ በእንተ ስማ ለማርያም እላለሁ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መላክ በምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት የቱ ጉባኤያት መምህር ማውጫ ገጽ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ከዓለም በፊት የነበረ ሌላ ዓለም ዓለም ስለ አመቤታችን ህህ ««« ሁለተኛው የሰማይ ክፍል ጌ ፊህህ«« በ እ እን እ ንእን ዓንሄሄ ሄሄ ሄሄ ቴቱ ከ ሄሄ » ወላዲተ አምላክ ማእምንት ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት መገኛ መሆኗ በአዲስ ሰማይና በአዲስ ምድር መተካቷ ዔደን ገነት ሊ እእህህኤኢፊ ሁለቱ ጠባቂዎቿ ሰባቱ የገነት ርስቶች ቅድመ ጽንስታ እምፅንሰታ እስክ ልደታ ሀ «« የእናት እና አባቷ ቤት ህህ ህ ከሦስት ዓመት በላ ፊ ሀ አስራ አምስተኛው ዓመት ህህህዚዚህ መታጨት ከታጨችበት ጊዜ በኋላም ድንግል ሆና መገኘቷ ዮሌፍ ፅለቱን ንግድ ተሸኝቶ ማደሩ ለቅዱስ ገብርኤል በስጠችው መልስ ምጽአተ ስብአ ሰገል ዘምስለ ብዙኅ አምኃ የስብአ ስገል ከብዙ እጅ መንሻ ጋር መምጣት በኅቱም ድንግልና ጸንሳ በኅቱም ድንግልና መውለድ ብሥራተ መልአክን መስማት»»»»» ሞትና ሕይወት በሁለቱም ሔዋኖች የአዲስ ኪዳኑ አገልግሉት መጀመር ሊቃውንት ስለ ማሕአጸአነ ማርያም ነጻነት ጌትነት መንፈስ ቅዱስ ስለ እመቤታችን ቅዱስ ገብርኤል ተናጋሪው ጽንስ በኤልሳቤጥ ቤት ከስድስት ወር በንሳፊህተኀኀ ዱግ ዓጣ ዓዓዱ ኀሓኀ ሓግ ሓሓኀሓኀሓሓ ሓሓ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ምጽአተ ዮሳ ወልደ ዮሴፍ። ጸድቃን ስማዕታት ነቢያትና ሐዋርያት የተስኙት ደናግልና መነኮሳቱ የተገኙባትና ዛሬም ለዘለዓለም የሚኖሩባት እግዚአብሔር ለማረፊያነት የተመኛት ልዩ ዓለም ናት በእርሷ ዘንድ ሞት የለም ሐዘንና ድካምም አይታይም ምክንያቱም ደስ ብሏቸው የሚኖሩት የቅዱሳን ማደሪያ ሆናለችና በአምላክ ኅሊና የታሰበችው ለዚህ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ክፍል ሕደጠተ ማርያም ድጀነገፅ ዓለም ለመዳኑ ብቻ ሳይሆን ለመፈጠሩም ምክንያት የሆነችው ይህች ዓለም እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ይህን የመለኮት ሐሳብ ሲገልጽ የተአምረ ማርያም መቅድም ጸሐፊ የሚከተለውን ተናግሯል እግዝእትነ ማርያም ነበረት እምቅድመ ዓለም በኅሊና አምላክ እመቤታችን ማርያም ከዓለም መፈጠር በፊት በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር ደራሲው በጥቅሉ ዓለም ብሎ የጠራውን በሦስት ከፍለን ልንተረጉመው እንችላለን ኛ ቀደም ሲል እንደገለጽነው የመጀመሪያው የዓለም ትርጉም የሚታየውንና የማይታየውን ማኅደረ ፍጥረት የሆነውን ዓለም የሚያመላክት ነው ይህ ዓለም ከመፈጠሩም በፊት እርሷ ታስባ ትኖር ነበር ተብሎ መነገሩ ለዓለሙ መፈጠር ምክንያት መሆኗን ለመናገር ነው እንኳን ለዚህኛው ለወዲያኛው ዓለም መሪያችን እርሷ አይደለች እንዴ። ያሉ እንደሆነ እግዚአብሔር ከዓለም መዘጋጀት አስቀድሞ የወሰነለትን መናገሩ እንጂ ከክዋክብት መፈጠር በፊትስ ሰው አልነበረም ምንም እንኳን የሰው ተፈጥሮ ከከዋክብት በኋላ ቢሆንም ክርስቶስ ወልደ ዳዊት ተብሎ ሲጠራ ከከዋክብት በፊት ለነበረው ጌታ አባት በመሆኑ ከዓለም በፊት የነበረ አድርጎታል ይህ ሁሉ አስቀድሞ በአምላክ ኅሊና የተዘጋጀ ነበር እግዚአብሔር ይህን ዓለም ለፍጥረታቱ ሲያዘጋጅ ለክብሩ መገለጫ ትሆን ዘንድ ያዘጋጃት ሌላኛይቱ ዓለም ደግሞ አመቤታችን ድንግል ማርያም ናት እግዚአብሔር ሕይወት በሌለው ዓለም ውስጥ የሚያድር አይደለም ሕደወጠተ ማርያም ፎገገስ ስለሆነም ሕያው የሆነች ከተማ ድንግልን አዘጋጀ እንዲያውም መጽሐፍ ስለ እርሷ ሲናገር ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት መዝ ነው የሚለው ዓለምነቷ ከዚች ዓለም የተለየች ናት ይህች ዓለም ማረፊያ የሌላት ስለሆነች መቆያ እንጂ ማረፊያ አይደለችም ይኸውም ጌታ ከዚህ ዓለም የሚለይበት ወርኀ ዕርገት በደረስ ጊዜ በተናገረው ንግግር ይታወቃል ማረፊያ ላዘጋጅላችሁ አፄዳለሁ ማለቱ ያለንባት ዓለም የምታሳርፍ ዓለም ባለመሆኗ ነው ስለ እመቤታችን ዓለምነት ሲናገር ግንማረፊያዬ ነው ያላት ለሰው ልጆች ማረፊያ ባልነበረበት ሰዓት አመቤታችን የአምላክ የዘለዓለም ማረፊያ ሆና በመገኘቷ ለሰው ዘር በሙሉ ማረፊያ የሚሆነው ያ ልዩ ዓለም ተዘጋጀ ለዚያኛው ዓለም መመሥረት መሠረት ከሆነች ለዚህኛውማ ምን ይገርማል በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ስለ አዲሱ ዓለም ስለ መንግሥተ ሰማያት ከመስማታችን በፊት በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የሰማነው የሀገረ እግዚአብሔር የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ታሪክ ነው የወዲያኛውን ዓለም ታሪክ የሰማነው ጌታ በዕርገት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ሊመለስ በተቃረበበት ሰዓት ሲሆን የእመቤታችን ጉዳይ ግን ወንጌላውያን ለወንጌላቸው መግቢያ ያደረጉት ዐቢይ ጉዳይ ነው ወንጌል ማለትኮ ተስፋ የምናደርገው ዓለም መንግሥተ ሰማያት ነው መንግሥተ ሰማያት ለምንለው ዓለማችን ለሕገ ወንጌል መግቢያ የሆነው የእርሷ ታሪክ እንደሆነ ሁሉ ለዚህ ግዙፍ ዓለም መፈጠርም እመቤታችን መቅድም ናት ኛዓለም የሜለው ቃል ሁለተኛ ትርጉሙ ሳው ተብሎ ይተረጎማል አዳሪውን በማደሪያው መጥራት የቅዱሳት መጻሕፍት የተለመደ ጠባያቸው ነው በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችን ሰመጥራት አሌ ሕይወተ ማርያም ደኀኘገስ ለኪ ኢየሩሳሌም የኮራዚን ሰዎች ለመጥራት አሌ ለኪ ኮራዚ ማቴ እንደ ማለት በዓለም የሚኖር ሰውንም ሰመግለጽ ዓለም ብሎ መጥራት የተለመደ ነው እስመ ከመዝ አፍቀሮ እግዚአብሔር ለዓለም እግዚአብሔር ዓለሙን እንዲሁ ወዶታልና ዮሐ አሁን እንዲህ ብሎ ወንጌላዊ ሲናገር እግዚአብሔር የሰማይና የምድር ፍቅር አደረበት ለማለት እንዳልሆነ አዕምሮ ያለው ትውልድ ሁሉ ሊዘነጋው አይችልም እመቤታችንም ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር ተብሎ ሲነገር በቁሙ ዓለሙን ብቻ የሚይሳይ ሳይሆን ከለው ልጆች መፈጠር በፊት እርሷ በፈጣሪ ዘንድ የታስበች መሆኑን የሚያሳይ ነው አበው በታሪክ እንደሚነግሩን ሰው የሚፈጠርባት ዕለተ ዓርብ ከመድረሷ በፊት እግዚአብሔር በመላኩ ቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ስሎ አመቤታችንን ለመላእክቱ አሳይቷቸው ነበር በመላእክቱም ዓለም ከአባቷ ከአዳም ከእናቷ ከሔዋን ቀድማ የታወቀች አመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ተፈጥራ በምድር ላይ መኖር ከጀመረችባቸው ጊዜያት በፊት ለእርሷ ከመላእክት ምስጋና አልታጎለባትም ነበር ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ በመባል የሚጠራው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ይዌድስዋ መላእክት ለማርያም በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት መላእክት ማርያምን በመንጦላዕት ውስጥ ያመስግኗታል ሲል ያመስገናት በመንጦላዕት ውስጥ የተባለው አመቤታችን በሥጋ ያልተገለጠችባቸው ዘመናት ናቸው በተመሳሳይም ሌላኛው የሀገራችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ጾራ መንጦላዕተ ደመና ሰወራ ሚካኤል በክንፍ ር መጽሐፈ ሰዓታት ሕደወዉተ ማርያም ጀፎንገፅ ተሸከማት የደመና መጋረጃንም ጋረደላት በማለት በነዚያ እርሷ ባልነበረችባቸው ዘመናት መላእክቱ በዘመን መጋረጃ አሾልከው አየተመለከቱ የሚገባትን የምስጋና እጅ መንሻ ያቀርቡላት እንደነበር ሁለቱም ሊቃውንት ተስማምተውበታል ቀደም ሲል እንዳየነው አመቤታችን ለዚህ ዓለም መፈጠር ምክንያት ሆናለች የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ ለደቀ መዝሙሩ ቀሌምንጦስ እንደነገረው ሶበሰ ኢኮነት ዛቲ ቅድስት ድንግል እም ኢፈጠርክዎሙ ለአዳም ወለሔዋን። ከዘመናት መቆጠር በፊት ያለውን ቀርቶ የሰው ልጅ ከዘመናት መምጣት በኋላም ቢሆን ያለውን ወቅት ምን አይነትና ስንት እንደሆነ ለማወቅ አልቻለምአምላካችን ግን ከወቅቶችም መፈራረቅ በፊት የነበረ ነው ከዘመናት በፊት የነበረው እግዚአብሔር አብ ያለ እናት በቅድምና እግዚአብሔር ወልድን ከአካሉ ከባሕርዩ ባስገኘ ጊዜ የእናትነት ሥልጣኑ በአካል ከመገለጧ በፊት በአምላክ ኅሊና ለእመቤታችን የተሰጠ ነበር የሚያደርገውን እንጂ የማይሆነውን የማያስብ አግዚአብሔር ዘመኑ በደረስ ጊዜ ከአካሏ አካልን ከባሕርይዋ ባሕርይን ነሥቶ ከእርሷ ተወለደ ዘመናት መቆጠር ዓለማትም በዘመን መሰፈር ከመጀመራችው በፊት እርሷ በእግዚአብሔር ዘንድ ታስባ ትኖር ነበር እንዲያውም ቅዱስ ያሬድ ሸመንየ አዝማንኪ መጠንየ አምጣንኪ በማለት በድጓው ያመሰግናታል ሲተረጎምም ዘመኔ ዘመንሽመጠኔም መጠንሽ ነው ማለት ሲሆን ዓለም ከተዘጋጀ ከብዙ ዓመታት በኋላ ጌታ ከእመቤታችን የነሣው ሥጋ ቀዳማዊ መሆኑንና የእመቤታችንም ወላዲተ አምላክነት ከዓለም አስቀድሞ የታሰበ መሆኑን በዝማሬው ያረጋግጥልናል አሮጌው ዘመን አልፎ አዲሱን ዘመን መቁጠር ሲጀመር ኅሊናሁ ለአብ ብለን የምንጠራው ጌታ ከእርሷ ተገኘ ፈጣሪያችን ያለጊዜው የሚያደርገው ነገር ባለመኖሩ የሚያደርጋቸውን ነሮች ዘመን ይቀድማቸዋል እንጂ ሐሳቡን ዘመን ቀድሞት አያውቅም ፖመርለእኋ አውር ጾመ ድዕነ ዘቅዱስ ያሬድ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ትምህርተ ኀቡዐት ሕደጠተ ማርያም ድደንገፅ ዓለም ስለ እመቤታችን ዓለሞት በአራት ዐበይት ክፍሎች የተከፈሉ ናቸው ከምድር በላይ ያለው ሰማይ ብቻውን በሁለት ይከፈላል የመጀመሪያው መቅደሰ እግዚአብሔር ተብሎ የሚጠራው ክፍል ሲሆን በዚህ ዓለም ውስጥ ሦስት ሰማያት ይገኛሉ የሁለቱ ሰማያት ጽንፋቸው የማይታወቅ መሆኑን የሥነ ፍጥረቱ መጽሐፍ ይመሰክራል አንደኛዋ ሰማይ ግን አራት ማዕዘን ሆና በልክ ከላይ እንደ ክዳን ሆና የተሠራች ሰማይ ናት እንጂ እንደ ሁለቱ ሰማያት ዳርቻ የሌላት አይደለችም እነዚህን ሦስቱም ሰማያት ማኅደረ እግዚአብሔር በመሆናቸው ፍጡራን ሰግደው ለመመለስ ካልሆነ መኖር አልተፈቀደላቸውም እግዚአብሔርም በልዩ ጥበቡ አንዱን መሠረት አንዱን ግድግዳ ሌላውን ጣራ አድርጐ አያይዞታል እንደ መንበር ሆነው የተሠሩ በመሆናቸው ሁል ጊዜ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ጸንተው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል ለወዳጆቹ ሲገለጥ እግዚአብሔር በዚህ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ክኪሩቤል ትክሻ ላይ ሆኖ ነው የሚገለጠው ሕዝ ኢሳ በዚህ ሰማያዊ ዓለም ውስጥ ሁል ጊዜ ቅዳሴ አይቋረጥም ሙሴ በደብረ ሲና ያያቸው ሰባቱ የአሳት መጋረጃዎችም የሚገኙት በዚህ ቅዱስ ቦታ ነው ከዚህ ቤተ መቅደስ በላይ ምንም ነገር የለም የፍጥረት ሁሉ ቁንጮ ነው ይህ ሁሉ ፍጥረት ወደ ዚህ ስማይ ያንጋጥጣል የፍጥረት ሁሉ የተስፋ ፍጻሜ ከዚህ ሰማይ ይወጣል ምድራውያንን የሚያረካው የምሕረት ጠበል ከዚህ ሰማይ ይመነጫል በአጠቃላይ ለተገፉት ፍትሕ ለግፈኞች ቅጣት የሚወጣው ከዚህ የጽድቅ አዳራሽ ነው ሰማያትን በምጥቀታቸው ምድርን በጥልቀታቸው አየረ አክሲማሮስ ዘእሑድ ዣ ሕደወተ ማርያም ድገግፅ አየራትን በንስርነታቸው የፈታተሹት እነዚያ አፅማዶቻችን እንደነገሩን ይህ ሰማይ የእመቤታችንን ምጽአት የሚሰብክ የአመቤታችን ምሳሌ ነበር። ከሰማያት በላይ ያለው ይህ ሰማይ ፍጡራን ለሚኖሩባቸው ሰማያት ሁሉ አክሊል ነው እመቤታችንም አክሊለ ፍጡራን ናት የቅዱሳን ቁንጮም ናት እንደነዚህ ሰማያትም እመቤታችን መቅደሰ እግዚአብሔር ናት ሌላውን ቅዱስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ኛ ቆሮ ብንለው እግዚአብሔር በኅድረት በረድኤት ስለተገለጠበት ይሆናል እንጂ እንደ እርሷ በከዊን ተዋሕዶ መች ነውና በአውነት አመቤታችን እግዚኡኃያላን የሚኖርባት ከተማ ናትና ፍጥረት ላይኖርባት የተዘጋጀች አማናዊት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናት አንድ ሊቅም መቅደስ አንቲ ዘረሰየኪ ታዕካሁ እአግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መመስገኛ ያደረገሽ አንች ነሽ» ሲል ያወድሳታል የመጀመሪያው ዓለም ሲፈጠር የነበረው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የነዚህ ሰማያት ኅብረት ነበር ዓለምን በሐዲስ ተፈጥሮ እግዚአብሔር ሊሠራው ባስበ ጊዜ ግን ሦስቱን ሰማያት በሦስት ነገር በተከበበች ድንግል ለወጠው ማለትም ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና በተገኘባት በእመቤታችን ተክቶታል ለሐዲሱ ዓለም እመቤታችን የመጀመሪያዋ የምስጋና ሥፍራ ናት የመጀመሪያው የመላእክቱ ቅዳሴ የትጉዛትኑ ሠራዊት ማኅሌት የተቆመው በአርያም ሥርዓት ዝማሬ በምድር ላይ የተንቆረቆረው በእመቤታችን ማሕጸን አይደል። ከሾማት ንጉሥ በስተቀር የእርሷን ጸጋ ቆጥሮ የሚያውቀው እንደሌለ እውነት ብየ እነግራችቷለሁ አብርሃም ያያት ሰፊ ሰማይ እኮ እመቤታችን ናት በሌሊት ከቤቱ ወጥቶ ሽቅብ አንጋጦ በርቀት ካያት ሰማይ ላይ ሥሩ መ ሥርዓተ ቅዳሴ ሕይወተ ማርያም ድገገስፅ ያያቸውን ከዋክብት መቁጠር ተስኖት አይደል አብርፃም ወደ ቤቱ የገባውዘፍ የአመቤታችንንም ክብር ለመመርመር አብርፃም ልቡናቸውን በቀደሙት ዘመን የተነሠት አባቶቻችን ወደ ጥልቁ አውርደውታል ወደ አየር አውጥተውታል አብርሃም ከዋክብቱን መቁጠር አልችል ብሎ እንደተመለሰ አባቶቻችን ቅዱሳኑም ልቡናቸው የእመቤታችን ክብራን መመርመር አልችል ብሉ መመለሱን ይነግሩናል ከነሱ አንዱ አባ ህርያቆስ እንዲህ እንዳለ ይስእን ወይገብእ ኀበ ዘትካት ህሳዌሁ አልመረመረው ብሉ ወደ አለመመርመሩ ይመለሳል ብሉ ማለቂያ የሌለው ይህ ዓለመ ሰማይ ማለቂያ የሌለውን የድንግል ማርያምን ክብር ሊያስነብበን የተዘረጋ ንጹሕ ብራና ነው ላለፈውም ለሚመጣውም ለሕያዋኑም ለሙታኑም ማደሪያ ሊሆን የተሠራው ይህ ሰማይ ስንመረምረው ይገርማል ከዚህ በላይ ያለፈውም የሚመጣውም ትውልድ ብፅዕት የሚላት ለሕያዋኑም ለሙታኑም ለፊተኛውና ለኋለኛው ፍጥረት ማረፊያ ሆና የተሠራች እመቤታችን ደግሞ ትገርማለችና በሰማይ ብንመስላት ሰማይ ቢያንስብን ሁል ጊዜ በምንጸልየው ጸሎታችን አንቲ ተዐብዬ እምሰማይ ከሰማይም ይልቅ አንቺ ትበልጫለሽ ብለን እንዘምርላታለን ሦስተኛው ክፍል በሶስተኛነት ተቀምጦ የምናገኘው በዕለተ ሰኑይ እንደተገኘ የሚነገርለትን ጠፈር እየተባለ የሚጠራው ዓለም ነው ይህ ዓለም የዕለተ ረቡዕ ናጥዋረታት ፀሐይ ጨረቃና ክዋክብትን ሰብስቦ የያዘ ዓለም ነው ከነዚህ ፍጥረታት በስተቀር በዚህ እንዲኖር የተፈቀደለት ሌላ ፍጥረት የለም ምንም እንኳን ከውኃ ተከፍሎ በቃለ እግዚአብሔር ጽና ተብሎ ቅዲማር ጭ» ውዱ ማር ሕይፀዉተ ማርያም ደገግፅ የጸና ውኃ መሆኑን ብናውቅም አንዳንድ ጊዜ ይህን ጠፈር ሰማይ ብሎ መጥራት የተለመደ ነው ሰማይ ማለት ስዕለ ማይ ማለት በመሆኑ በምሥጢር ተነጥቀው እንጂ አባቶቻችን ሰማይ ብለው የጠሩት አውነት ነው ቁጥሩስ ከሰባቱ ሰማያት ውጭ ነው ዓለማችን ከተፈጠረች በሁለተኛው ቀን ይህ ግዙና ሆኖ የምንመለከተው ጠፈር ታየ እስከዚያ ድረስ ታላቁ መጽሐፍ እንደሚነግረን ከዚህ ካለንበት ዓለም አንሥቶ እሰከ ብሩህ ሰማይ ድረስ ዓለሚቱ ልክና መጠን በሌለው ውኃ ጢም ብላ ተሞልታ ነበር ሁለተኛው ቀን ግን ለምድር የብስን ለሰማይ ደግሞ ጠፈርን መጋረጃ አድርጎ አስገኘ በሰማይና በምድር መካከል የጠፈር ግድግዳ ተፈጠረ በዚህም ምክንያት ከብሩህ ስማይ የሚፈልቀውን የብርሃን ጠል እንዳትጠጣ ምድር ተከለከለች በአራተኛው ቀን ግን ከመለኮታዊ ብርሃኑ የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል የተሳለባቸው ታናሽና ታላቅ ብርፃናት ለምድር ያበሩላት ጀመሩ እነዚህን ታላቅና ታናሽ ብርፃን ብዙ የብዙ ብዙ ከሆኑ ከዋክብት ጋር የሚያስተናግደው ዓለም ስሙ ጠፈር ተብሎ በፈጣሪ ተሰይሟል ጠፈርን በፈጠረው ጊዜ አመቤታችንን በምሳሌ ሲነግረን ነው ይላሉ አባቶቻችን በሁለተኛው ቀን መፈጠሩ እመቤታችን በሁለተኛው ክፍለ ዘመን በዘመነ ኦሪት የምትገኝ መሆኗን አመላካች ነው ይህን ጠፈር ሲሠራው እግዚአብሔር ከበላዩ ወንዳ ወንድ ውኃ ከበታቹ ደግሞ ሴታ ሴት ውኃን አስቀምጦበታል በዚህም ድንግል ማርያም በሌትና በወንድ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም የምትገኝ እንጂ ከሰማይ የምትገኝ ሰማዊያት እንዳልሆነች ተናገረ ሔኖ ከበላዩ ያለው ወንዳ ወንዱ ውኃ ሁሌም ሲገማሸር የሚኖር ቁጣ የማይለየው ኃያል ውኃ ሲሆን በኖኅ ዘመን ለተደረገው ብር ሕይወተ ማርያም ድንገፅ ጥፋት የእግዚአብሔር በትር ሆኖ በማገልገሉ ይታወቃል ወደ ታች ወርዶ ጠፈሩን እንዳያበላሽ አምላካችን ባቢል የሚባል የነፋስ ምሰሶ ተክሎለታልአባቶቻችን ይህን ውኃ በጥንተ አብሶ ይመስሉታል ለጠፈሩ ከዚያ ውኃ ጋር አለመገናኘት ከነፋስ በቀር ሌላ ማን የቆመ አለ። ሁሉን መሸከም የምትችለውን ምድር ምንም መሸከም ከማይቻላቸው ረቂቃን ፍጥረታት አናት ላይ ሲያስቀምጣት በጥንቃቄ ነው ምንም አንኳ ጽናት ከሌላቸው ከነዚህ ፍጥረታት ላይ ቢያስቀምጣትም እሷን ግን ሁሉን እንድትችል ከሁሉ በላይ አድርጎ ጽናትን አስታጥቆ ፈጠራት እንደለው ሰውኛው ቢታሰብማ ኖሮ ጽንዕት ምድር ከሥር ኦነዚህ ደግሞ ከላይ በሆኑ ነበር አምላካችን ሁሉን ቻይ ነውና ከሰው አዕምሮ በላይ የሆነውን ሥራ ሠርቶምድሪቱን አጸናት ከሥር ያሉት በተለይም እሳትና ነፋስ ቀላሎች አንደመሆናቸው መጠን ሽቅብ ወደ ላይ እንውጣ ይላሉ ምድርና ውኃ ከላይ ሆነው ወደታች ሲገፏቸው ይኖራሉ እናም አሁን ስለምድር ዘፍ ሕደጩዉተ ማርያም ጀኀኝገል ስናነሣ ቀላሎችን ፍጥረታት እሳትና ነፋስን የተሸከመች እርሷ ነች እንጂ ምንም በላያቸው ብትሆንም እነርሱ የተሸከሟት አይደሉም ከሥሯ የሚገኙ እነዚህ እሳት ውኃና ነፋስ ከላይዋ ቢፈለጉም አይታጡም ሁሉን የተሸከመች ሥጋዊና ደማዊ ፍጥረታት የተወሰኑባት ይህች ምድር አመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ስው ከምድር አፈር ተበጅቶ ምድርን በልቶ ምድርን ለብሶ በምድር ላይ ይኖራል ከአሮጊቷ ምድር ወደ አዲሲቷ ምድር እስኪሸጋገር ድረስ ታላቁ መጽሐፍ ከፍጥረታት ሁሉ ታላቅ የሆነውን የሰውን ተፈጥሮ ሲናገር ከምድር አፈር የተበጀ መለኮታዊ ሸክላ እንደሆነ ይመሰክራል ዘፍ ይህች ምድር የመጀመሪያውን ሰው አዳምን ከባሕርይዋ ያለ ዘርና ሩካቤ በእግዚአብሔር ቃል ብቻ አስገኘች ከዚህ ተያይዞ ፍጥረት ሁሉ ከእርሷ ማሕጸን የወጣ መሬታዊ ሆነ ሁለተኛይቱ ምድር ድንግል ማርያም ደግሞ የአዲሱ ፍጥረት አባት የሆነውን አዲሱን ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን አስገኝታለች በማሕጸኗ ስታሳድረው እንደ ፍጥረት ልማድ ዘር ምክንያት አልሆናትም ገዥዋ አለቃዋ ጠባቂዋ ተንከባካቢዋ አዳምን ምድር እንዳስገኘች ሁሉ እመቤታችን ድንግል ማርያምም ፈጣሪዋን ወለደችው ገዥዋን አስገኝዋን አስገኘችው የቀደማት እርሉን ቀደመቸው ከእርሱ ተያይዞ ከማይሞትና ከማይጠፋ ዘር የሚወለዱት ምአመናን የዘር ሐረግ ሳይቋረጥ መቆጠር ጀመረ ታላቁ መጽሐፍ ዓለማችን ህልውናዋ ከተረጋገጠ በቷላ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ቀን የነበረውን ትዕይንት በተናገረበት አንቀጹ ስለ ምድር የተናገረው እጅግ አስደናቂ ነገር ነው ወምድርኒ ሀለወት እራቃ ወኢታስተርኪኢ ምድርም ባዶዋን ነበረች አትታይምም ነበር ዘፍ ይሳል ርክ መ ሕደወጠተ ማርያም ድገግስ ምድርም ባዶ ነበረች ስትል ቅድስት ኦሪት መናገሯ ስለዚህ ግዙፍ ምድር አይደለም ምክንያቱም በዚያ ወቅት ባዶውን አልነበረምና ከዚህ እስከ ብሩህ ሰማይ ውኃ ሞልቶ ይኮት ነበር እንጂ። አስቀድመን እንደተናገርነው እርሷ ከዓለም በፊት የነበረች ሌላ ዓለም ከመገለጧም በፊት በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር የነበረች ናት ይህን ያስበ ጊዜ ሙሴ የተናገረው ነገር ምንኛ ድንቅ ነው ምድርም እራቁቷን ነበረች አትታይምም ነበር ዘፍ ራቁቷን ሆና ነገር ግን የማትታይ ምድር ነበረች ለምን ከተባለ ሊቀ ነቢያት ሙሴ መልስ አለው ወኢኮነት ድሉተ የተዘጋጀች አልነበረችም በአምላክ ኅሊና የተገለጠች መሆኗ ዕራቁቷን ነበረች አስኝቷታል ገና በእዝነ አዳምም ያልተሰማች ልዩ የእግዚአብሔር ምሥጢር በመሆኗ ደግሞ አትታይምም ነበር ተባለላት ታስበች እንጂ አልተፈጠረችም ነበርና ይልቁንም በሥራው ድንቅ የሆነው አምላክ ከዳር እስከ ዳር በውኃ መልቷት የነበረ መሆኑ በሥነ ፍጥረታት ታሪክ የተረጋገጠ ነው እስከ ሁለተኛው ቀን ድረስ በውኃው ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ ሰፍፎ ይዞት ምድሪቱ ፊቷ እንዳይታይ አድርዓት ነበር ሁሉን የሚያዘጋጀው እግዚአብሔር እስኪያዘጋጀው ድረስ ምድሪቱን ሸፍኖ የነበረው ውኃ እመቤታችን ድንግል ማርያም አእስከተገለጠችበት ጊዜ የነበረውን ዘመን ያመላክታል ይህን ውኃ አምላክ በቃሉ ከፈለው በሁለተኛይቱ ቀን ከሦስት ቦታ ላይ እንዲሰበሰብ ተወስኖበት ውኃው እንደተከፈለ ለዓመተ ፍዳ ለዓመተ ኩነኔ ሁለተኛ በሆነች ዓመተ ምሕረት በተሰኘው ዘመን ጌታን በድንግልና ጸንሳ በትንቢተ ነቢያት የተዘጋጀች ሆና እስከተገለጠችበት ጊዜ የነበረውን ዘመን ለሦስት ይከፈላል ዘመነ አበው ዘመነ መሳፍንት ዘመነ ነገሥት ተብሎ ር ሕደጠተ ማርያም ደገገፅ በነዚህ በሦስቱም ክፍላተ አዝማን መንፈስ ቅዱስ በላይዋ ላይ ሰፍፎ እስከ ዳግመኛው የምሕረት ዓመት ድረስ የማትታይ ምድር አደረጋት በእውነት ይህ የአግዚአብሔር ሐሳብ ስለ እመቤታችን ባይሆንማ ኖሮ ሊቀ ነቢያት ሙሴን በውኃ ላይ በረቂቅ ሰፍፎ ስለነበረው የአግዚአብሔር መንፈስ እንዲናገር ምን አስገደደው ምክንያቱም በእያንዳንዱ ፍጥረት ላይ የአግዚአብሔር መንፈስ የማይለይ ሆኖ ሳለ ከዚህ ሲደርስ ለይቶ አስቦታልና እስከ ሁለተኛው ቀን ድረስ በመንፈስ ቅዱስ ጥላ ሥር የምታርፍ መሆኗን ውኃውም ተዘጋጅቶ ሲያልቅ የምትገለጥ መሆኗን አሳየን ውኃ ብለን የጠራነው ዘመን ሲፈጸም ያለ ገበሬ ድካም ያለተክልና ያለዘር ማፍራትና ማለምለም የሜቻላት የተዘጋጀችዋ ምድር እግዚአብሔር የቀጠረው ቀን ሲደርስ ተገለጠች ዓለማችን በጥንተ ተፈጥሮዋ ከእግዚአብሔር በሆነ ብርሃን ስትመራ የቀናቱ ሁሉ መካከለኛ በሆነው በዕለተ ረቡዕ ፀሐይ እንደተገለጠች ክብሯ ከፀሐይ ይልቅ የሚያበራው እመቤታችንም የዘመናት ማዕከል ላይ ማለትም በዓመተ ፍዳ መካተቻ በዓመተ ምሕረት መባቻ ላይ ተገለጠች በጣም የሚገርመው ፀሐይ በአራተኛው ቀን በከዋክብት ተከባ እንደታየች እመቤታችንም ከአራተኛው ትውልድ ከቤተ ይሁዳ ነው የተወለደችው አስራ ሁለቱን ነገደ እስራኤል ከሮቤል ጀምረን ስንቆጥር ይሁዳ አራተኛ ስለሚሆን ነው የዓለም ብርፃን ክርስቶስ ከእርሷ ይወጣ ዘንድ የጽድቅ ፀሐይ አመቤታችን ከአራተኛው ትውልድ ወጣች ያውም በከዋክብቱ በነቢያት በካህናት ታጅባ ዮሐ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርፃን ሰው እንዲወጣ የአማናዊው ብርፃን ሰሌዳ ድንግል በሰማይ ሰሌዳ ላይ ተቀረጸች ሕደዉተ ማርያም ደፎገገል ሦስቱ ነገሮች ለዚች ምድር መሠረት ሆነዋታል በሳይዋም እነርሱ ያድሩባታል በምድር ላይ የሚርመሰመሰው ማንኛውም ፍጥረት ቢሆንም ከነዚህ በምንም ያልተለየ የነዚህ ነገሮች ውሕድ ውጤት ነው ያለ እነርሱም ምድር ባዶ ናት እመቤታችንም መሠረቷ ሥሉስ ቅዱስ የሆነላት ንጽሕት አዳራሽ ናት ጉልላቷም እግዚአብሔር ነው በውስጧም የሞላው እርሱ ነው እርሷ ለእርሱ ማደሪያነት ተዘጋጅታለች እንጂ ሌላ ምን አላት ከአርሱም በቀር ሌላ ቢፈለግ በውስጧ ምንም የለም ለእርሱ ብቻ የተሠራች ምሥራቃዊት አዳራሽ ናትና ወደእርሷ ተልኮ የመጣውም መላክ ያረጋገጠላት እውነት ይህ ነው የሦስቱ አካላት ማኅደር መሆኗቧን በውኃ ላይ ተመሥርታ በእሳትና በነፋስ ላይ ጸንታ የምትኖረው ምድራችን ቢያንስ በሦስት ታላላቅ ቄም ነገሮች ተለይታ ስትመሰገን ትኖራለች ታማኝ የሚያምነው ቢታጣ እንኳን ታማኝ ሆኖ ለዘለዓለም የሚኖረው ንጉሣችን እግዚአብሔር ብቻ ነው መታመን የባሕርይ ገንዘቡ በመሆኑ የሚያምኑ ፍጥረታት ከመኖራቸው በፊትም እርሱ የታመነ ነበርና ፍጥረታት ግን ሲሞላ ሲጐድል ነው ማመንና መታመን ክዳትና ሽንገላ ይፈራረቁባቸዋል ከፍጥረታት ሁሉ እንደ ምድር በታማኝነቱ የተመሰከረለት ደግሞ ማንም የለም ምድራውያን ሁሉ የአንድ ነገር ጥገኛች ናቸው የምድር የሥጋ ለባሹ ነሮ በሁሉም መንገድ ከምድር ጋር የተያያዘ ነው ሁሉም በእርሏ እንጂ ያለ እርሷ መኖር የማይችል መሆኑ ቢታወቅም ምድሪቱን ሁልጊዜም በታማኝነት ገበሬው ከጐታው ከጐተራው እያወጣ ያለውን የሚበትነው በምድር ላይ ነው ከምድር የሰበሰበውን መልሶ በምድር ላይ ሲበትነው ያለ አንዳች መጠራጠር ነው ንጉሥ መጫወ ፀመሠመሎሙውኢገክስ ት ሕይደጠተ ማርያም ጀገገስ በመኳንንቱ በሠራዊቱ ጳጳሱ በሊቃውንቱ መምህር በአርድእቱ ታማኝነትን አጥቶ ተስፋ በቆረጠበት በዚህ ዘመን በምድርና በገበሬው መካከል ግን ዛሬም መተማመን አለ አርሷ ለዘለዓለም ታማኝ ናትና አመቤታችን ድንግል ማርያምም በሦስቱ ነገርች ለዘለዓለም የታመነች ናት ሀ በድንግልና አንከን የሌለው የውስጥና የውጭ ድንግልናን መኖር የቻለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ብቻ ናት ድንግል የተባሉ በዚች ዓለም ብዙዎች ቢሆኑም በድንግልናቸው ጥያቄ ያልተነሣባቸው ግን የሉም በዚያውም ላይ የውስጥና የውጭ ድንግልናቸውን ጠብቆ በመቆየት ለነፍሳቸውም ለሥጋቸውም ድንግልና ታማኞች አይደሉም አመቤታችን ብቻ በዚህ የታመነች ናት። የጳጳሳትን ነፍስ ይቅር ይል ዘንድ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ እያልን ላለፈውም ለሚመጣውም ለሙታንም ለሕያዋንም የታመነ የምሕረት ቃል ኪዳኗን እንማጸናለን በአጸደ ሥጋ በአጸደ ነፍስ በገነት በመንግሥተ ሰማያት ለምንኖር ለሁላችንም ምሕረት ለማማለድ የታመነች በመሆኗ ሰዓሊተ ምሕረትኞ ማእምንት ብለን እናወድሳታለን ሐ ወላዲተ አምላክ ማእምንት ቀዳሚ አዳምን ለማስገኘት ባሕር አልተመረጠችም ሰማይ አድሉን አላገኘችም ይህች ያለ ንባት ምድር ብቻ በፈጣሪ የታደለች ሆነች እንጂ የምድር እናትነት ር ው መ ውዱማር ሕይወተ ማርይም ድንገፅ ለአዳም የታመነች ናት አንደዚሁ ዳግማዊ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስን ለማስገኘት እመቤታችን የታመነች ናት በሚያስደንቅ ተአምራት የሚያስደንቅ ጸጋ የተሰጣቸው ልጆችን ለመውለድ የታደሉ ብዙዎች ናቸው አምላክን ለመውለድ ግን አልታደሉም ለዚህ የታመኑ አልነበሩምና እመቤታችን ብቻ ለዚህ የታመነች ናት ለትንቢተ ነቢያት ለሱባዔ አበው ቀደምት የታመነ ከእርሷ በቀር በምድር ላይ ማንም አልተገኘም ነበርና ለመመረጧ ምክንያት የሆናትም የታመነች ሆና መገኘቷ ነበር የሰማዩን ምሥጢር ለመስማት ከርሷ በቀር ማን ብቃት ነበረው በሰማይ የሚኖሩ አልሰሙትም ለዚህ የታደሉ አልነበሩምና ምሥጢሩ ታላቅ በመሆኑ ከፍጡራን ሁሉ ታላቅ ለሆነችው ለአመቤታችን ካልሆነ ለሌላ ለማን ይነገራል በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የተመከረውን የሥጋዌ ምሥጢር የሰማዩ መላእክት የሰሙት አርሷ ከሰማችው ከ ዓመት በኋላ ነው እርሷ ግን ከባለሟሎቹ ይልቅ ባለሟል ከወዳጆቹም በላይ ወዳጅ ናትና አስቀድማ ብትሰማም በልብዋ ጠብቃ ትኖር ነበር ብሎ ታላቁ መጽሐፍ ነግሮናል ማርያምም በልብዋ ትጠብቀው ነበር ሉቃ እንዲል ለዚህ ሁሉ ጸጋ የተመረጠች ቢሆንም ብዙዎች ግን ወላዲተ አምላክ በመሆኗ ላይ ብዙ ብለዋል እነ ንስጥሮስ ወላዲተ ሰብእ እንጂ ወላዲተ አምላክ ልትባል አይገባም ሲሉ አይሁድና ፈረሳውያን ደግሞ አርሷ የወለደችው አምላክን አይደለም የአምላክ አናት ማርያም ገና አልመጣችም በማለት በነቢያት የተነገረላት ወላዲተ አምላክ እሷ ለመሆኗ ጥያቄን ያነሣሉ እነ ሣምሳጢ ጳውሎስ የአምላክ ማደሪያ ለመሆን የተመረጠውን ኢየሱስ የተባለውን ሰው ወለደች እርሷ ዴዴ ችዬ ይ ሕደጠተ ማርያም ደኀገፅ በወለደችውም አምላክ አደረበት በማለት የእመቤታችንን ክብር ብቻ ሳይሆን የክርስቶስንም የባሕርይ አምላክነት ይክዳሉ በዚህ በከፋው የክህደት መርዛቸው የዋሃን ምእመናንን ይዋጋሉ እንደ እውነቱ ከሆነ የእመቤታችንን ወላዲተ አምላክነት ሰይጣን ራሉ እንኳን አይክድም ምክንያቱም እነሱ ይህን መሰል ትምህርት ከማስተማራቸው በፊት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲል ተሰምቷልና ማቴ ሉቃ መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ ሰዎች ላይ አድሮ ሲናገር እንደሰማነው ግን እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ለመሆኗ ምንም የሚያጠራጥር ነገር አላየንም። ሕይጠተ ማርያም ድገግስፅ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ሐሳብ መሆኑን አስቀድሞ በኤልሳቤጥ ንግግር እንደተረዳነው በኋላም በኤፌሶኑ ጉባኤም መቅደንዮስን በመቅጣት ወላዲተ አምላክ መባል የሚገባት መሆኑን አስረዳ ከሰማይ እስከ ምድር በተዘረጋው የሥነ ፍጥረት ሥርዓት የፍጡራን አንደበት ሁሉ ወላዲተ አምላክ ብለው ይጣራሉ ስዕሏን የሚስሉ ሰዓልያን ይህንን ለማስረዳት አምላክን በግራ እጂ አስይዘው ይስላሉ ስሟን በሚጠሩበት ቦታ ሁሉ ወነዲተ አምላክ የሚል ቅጽል ያስቀምጣሉ ከሌሎች ማርያሞች ለመለየት ሁል ጊዜ ይህን መግለጫ ይጠቀማሉ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ከዛሬም እስከ ዘለዓለም የአምላክን ሰው መሆን በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ አምላክን ለመውለድ እርሷ የታመነች ናት እምኅበ አልቦ ኅበ ቦ ካለመኖር ወደ መኖር የመጣችው መሬት ቀዳሚ አዳምን እንዳስገኘት መካኒቱ የሐና ፍሬ እመቤታችንም የአዳም ሁለተኛ ኢየሱስ ክርስቶስን ማስገኘቷ የቀደመውን የአዳምን ተፈጥሮ እንድናስታውስ አድርጎናል የመጀመሪያይቱ ምድር በፍጡራን ፍላጎት የተገኘች ሳትሆን በፈቃደ እግዚአብሔር ጊዜዋ ሲደርስ ካለመኖር ወደ መኖር የመጣች ናት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህን ሲያስረዳ እመ ይፈጥራ እግዚአብሔር ለምድር ኢዜነዎ ለስማይ ወኢተማከረ ምስለ መላአክቲሁ አግዚአብሔር ምድርን ሲፈጥራት ለሰማይ አልተናገረም ከመላእክት ጋር አልተማከረም ይላል አሁን እንዲህ ማለቱ ሰማይ ቀድሞ ተፈጥሮ መላእክቱም ከምድር በፊት ኑረው አይደለም ምክንያቱም ታላቁ መጽሐፍ በመጀመሪያ አግዚአብሔር ሰማይና ምድርን እንደፈጠረ ነግሮናልና ዘፍ ሊቁ በመንፈስ ቅዱስ በተቃኘው አንደበቱ ሊናገር የፈለገው ስለ ዳግማዊት ምድር ስለ እመቤታችን መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም ከሰማይ ዚቅ ዘኀዳር ሚካኤል ን ሕደጩተ ማርያም ደኀኝቫስ መዘርጋት ከመላእክትም ሥርዓት በኋላ የተፈጠረች ምድር የለችምና እንዲያም ከተባለ ድህረ ዓለም የተፈጠረች ምድር አመቤታችን ናትና እርሷንም ሲፈጥራት ከሰማያውያትኑ መላእክት ከምድራውያኑም የአዳም ዘሮች ጋር አልተማከረም እሱ በፈቀደ ጊዜ ፈጥሮአታል እንጂ እርሷ ምድር ተብላ መጠራቷም ለክርስቶስ አዳም ተብሎ መጠራት ምክንያት ሆኖታል ያለ ዘር ያለ ሩካቤ ፍጥረትን ማስገኘት የቻለ በጥንት ዘመን ከምድር በቀር ሌላ ነበርን። በዚህና በሌሎች ነገሮች ምድር እመቤታችንን ትመስላለችና ብለው የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት ዳግማዊት ምድር ብለው ይጠሯታል ስለ ምድር የተነገረውን ሁሉ ለአመቤታችን ሰጥተው ይተረጉማሉ ምድርን የሕያዋን እናት ብለን እንደምንጠራት ዘፍ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምንም እሞሙ ለኩሎሙ ሕያዋን ብለን አንጠራታለን የቀደመው ሰው ከምድር አፈር ተበጅቶ ሕያው ሆኖ ለዘለዓለም እንዲኖር ተወስኖለት የእግዚአብሔርን ሕያው አስትንፋስ አግኝቶ ሕያው ሆኖ ይኖር ነበር ይህን የሕይወት ጉዞ ሞት ሲያደናቅፈው ዳግመኛ ሕያው ፍጥረት ማስገኘት ምድራችን ሲሳናት ሌላ ሕያው ሰው ያስገኘችልን ሁለተኛዋ ምሥኗዴር እመቤታችን ናት በአንዱ በአዳም ምክንያት ሁሉም ሞተ ነበርና በሁለተኛው አዳም ፍጥረት ሁሉ ዳግም በሕይወት ሲፈጠር በሁለተኛው ጊዜ ሕያዋን ፍጥረታት የተገኙባት አመቤታችን ድንግል ማርያምን አሞሙ ለኩሎሙ ሕያዋን ብለን መጥራታችን ተገቢነት አለው የመጀመሪያው ሕያው ፍጥረት ሲገኝ ወነፍሐ ውስተ ገጹ ለአዳም መንፈስ ሕይወት በአዳም ላይ የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት ሸፍ ተባለ ስለ ሁለተኛው ሰው ሕይወት ግን የተነገረው ነገር ድንቅ ነው መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ አንች ይመጣል ሉቃ የሚል ነው የመጀመሪያው ከአፉ በተቀዳ የጸጋ ሕይወት የከበረ ሕያው ርቪር ቲቲ ጋ ኢኢሙሙሙ ፕ ሕይበተ ማርያም ድገገግስ ፍጥረት ሲሆን ከሁለተኛይቱ ምድር የተገኘው ሁለተኛው ሕያው ሰው ግን በባሕርይ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ሕያው የሆነ መሆኑን ያሳያል ከመጀመሪያይቱ ምድር የተገኙት ሕያዋን ፍጥረታት በነፍስ ሕያዋን የሚሆኑ ሲሆን ከሁለተኛይቱ ምድር የተገኙት ግን በመንፈስ ቅዱስ ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ የመጀመሪያው የየነፍስሕያውነት በተፈጥሮ የሚሰጥ ነው ሁለተኛው ሕያውነት ክርስትና ደግሞ በፈቃድ የሚሰጥ ነው ሰው ከመጀመሪያይቱ ምድር የተገኘ መሬታዊ ፍጡር መሆኑን አምኖ በጥንተ ተፈጥሮው እኔ አመድ እና ትቢያ ነኝ አለ ከሁለተኛይቱ ምድር የተገኘ ዳግማይ አዳም ክርስቶስ ከማይሞትና ከማይጠፋ ዘር ወልዶኛል ብሉ ከአመነ በኋላ በሐዲስ ተፈጥሮ ከአባቱ ዳዊት ጋር ኢይመውት ዘእንበለ ዘአሐዩ በሕይወት እኖራለሁ እንጅ አልሞትም መዝ እያለ አብሮ ይዘምራል ይህች ያለንባት መሬት እንኳን ማለፍ መለወጥ ማርጀት የሚስማማት ሲሆን በውስጧ የሚኖሩት ፍጥረታትን የምታድስበት ጊዜ አላት እንደ እባብ ያሉ ሥነ ፍጥረታት በልባቸው ተስበው አመድና ትቢያን ምግብ አድርገው የሚኖሩ ሲሆን የሕይወት ዋስትናቸው የአርጅና መከላከያቸው መሬት እንደሆነች የታመነ ነው እንደ አባብ ሁሉ የቀደመውን የመርገም ጽዋ የጨለጠው የቀደመው ሰው አዳምም የታደሰው እርጅናውን ያስወገደው ከዳግማዊት ምድር ከአመቤታችን ነው ዳግመኛ ላያረጅ አዳም አዲስ ሰው ሆኗል ለዚህ ነው መንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስን እዲህ ብሎ ያናገረው ወብኪ ተሐደሰ ቀዳሜ ኩሉ ፍጥረት የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ በአንቺ ታደሰ ከመጀመሪያይቱ ምድር ለተገኙት ሰዎች እንዲህ ተብሎ ተነግሮላቸው ዴ ማም ጾጾ ከ ሕደወተ ማርያም ድኘገስ ነበር በእድሜአቸው ፈጽመው ሽምግለው አርጅተውም ነበር ዘፍ ሉቃ ከስሰው ልጆች ነውርን ያስወግድ ዘንድ ባረጀውና በሸመገለው ዓለም ውስጥ ከአዲሲቱ ምድር አዲስ ሰው ተወለደና አሮጌውን አስወገደ እንዲያውም ሁሉን አዲስ አደረገ ኛ ቆሮ አዲስነቱ ደግሞ ለጊዜው አዲስ ሆኖ ቆይቶ የሚያረጅ እንዳይሆን ባለመለወጥ አጸናው ከዚያም አያይዞ ለስው ዘለዓለማዊነት ተሰጠው ሞት ሲገዛው ለነበረው የሰው ልጅ ባሕርይ ወተውህበ ሎቱ ሥልጣን ወምዙናን ዘለዓለም የዘለዓለም ግዛት ተስጠው ዳን ተብሎ ተነገረለት በዘመናት ተወስኖ ይኖር የበረው የስው ልጅ ዘመናትን አልፎ የሚቀር ክብርና ጌትነትን ተቀበለ ወደ ኋላም ወደ ፊትም ቢሆን የሌለበት ጊዜ የሌለና የማይኖርበት ጊዜ የማይኖር ሆነ ይህ ሁሉ በአዲሲቱ ምድር በእመቤታችን ላይ የተከናወነ ጣፋጭ የሰው ልጆች ታሪካችን ነው ይህች ምድር ካስገኘቻቸው ልጆቿ ዳግማዊቷ ምድር እመቤታችን ያስገኘቻቸው ይበዛሉ የዚች ምድር ልጆቿን ሞት ቀምቷታል ከአመቤታችን የተገኙት ግን ሁሉም በሕይወት ያሉ ናቸው እንዲያው ለዘለዓለም ምድራቸውን ወርሰዋት ሊኖሩ ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን አላቸው እንጂ ኢሳ ለዚችኛዋ ምድር ጥሩ ምሳሌ ይሆን ዘንድ ያችኛዋ ምድር በልብ የሚሳቡትን በእግር የሚሽከረክሩትን በክንፍ የሚበሩትን በደመ ነፍስ ሕያዋን ሆነው ጸንተው የሚኖሩትን ሦስት ሕያዋን ፍጥረታት እንድታስገኝ ታዝዛ ነበር። እንደ እግዚአብሔር ቃል ሁሉም ፍጥረታት ከመሬት የተገኙ ናቸው ምድራችን በራሷ ሕይወት ሳትሆን ሁሉን በቃሉ የሚያከናውነው እግዚአብሔር ሕይወት ሳሳቸው ርች መገኘት ምክንያት አድርጓታልና ሕይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ ከርሷ የተገች ናቸው ሕደይጠተ ማርያም ደንገፅ በዚህም አመቤታችን የሦስት ነገሮች እናት መሆኗ ታወቀ ተረዳ የሰብአ ዓለም የባሕታውያን የሰማዕታት ከዚህ ዓለም እስከ ታላቁ ዓለም መንግሥተ ሰማይ ድረስ የሚኖሩ ጻድቃን በነዚህ ሦስት ሰዎች የተጠቃለሉ ናቸው በክንፍ የሚበሩ በሰማዕታት ይመሰላሉ እንደ ሰማይ ንስር ከሚያውቁት ዓለም ወደ ማያውቁት ዓለም በተመሥጦ ስለሚነጠቁና ሽቅብ ወደ ጽርሐ አርያም ወጥተው ይህን ዓለምና ክብሩን ንቀው አጥቅተው ቁልቁል ስለሚመሰከቱ ነው በልብ የሚሳቡ በዚህ ዓለም በፈቃዳቸው በሕጋዊ ጋብቻ ተወስነው በሚኖሩ ጻድቃን ልጆቿ ይመሰላሉ እነዚህ በልብ የሚሳቡ እንስሳት በምድር ላይ ሲርመሰመሱ የሚኖሩ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ቀና ብለው ከዕፀዋት ፍሬን ለቅመው ወደ መሬት መመለሳቸው የማይቀር የተፈጥሮ ተግባራቸው ነው ሰብአ ዓለምም ሰባት ጊዜ ወድቀው ሰባት ጊዜ ተነሥተው በሚያደርጉት መንፈሳዊ ጉዚጺቸው የጽድቅ ፍሬን የሚቀምሱ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን በመሬታዊ ግብር ሲርመሰመሱ የሚኖሩ መሆናቸውን የሚያመላክት ነው ሰብአ ዓለም ባሕታውያን ሰማዕታት ደጅ የሚጠኗትን የሚጋደሉላትን መንግሥተ ሰማያትን ያስገኘችላቸው እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው ሊቃነ ጳጳሳት የጵጵስናቸውን ዋጋ ነቢያት የትንቢታቸውን ሐዋርያት የስብከታቸውን ሰማፅታት የተጋድሎአቸውን ዋጋ ለማግኘት ደጅ የሚጠኑት ክርስቶስን ወለደችላቸው ብሎ አመስግኗታል ከሷ በፊት የነበሩ ነቢያትና ጻድቃን ጽድቃቸው አንደመርገም ጨርቅ የተናቀ ሆኖ እንደነበር ታላቁ መጽሐፍ የሚነግረን እውነታ ነው ኢሳ ዛሬ ግን ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ይከፍል ዘንድ » ሕደወተ ማርያም ደኀገስ የሰው ልጆች ዋጋ በእጁ የተያዘለት ጌታ ከእመቤታችን ተወልጳልና እንዲያውም በተላ በተረዳ በር እንስሳት አራዊት አዕዋፍ የተሰኙ ፍጥረታትን አንድ አድርጐ በመያዝ የቀደመችው ምድር እመቤታችንን መሰለች እኛ በልማዳችን እንስሳት የምንላቸው ሣር ነጭተው ውኃ ተጎንጭተው የሚኖሩትን ሲሆን አራዊት የምንላቸው ደግሞ ሥጋ ነጭተው ደም እንደ ውኃ ተጐንጭተው የሚኖሩትን ነው በሌላም መንገድ የሚበሉትን እንስሳት የማይበሉትን አራዊት እንላቸዋለን እነዚህ ሁሉ ፍጥረታት በምድር ላይ ሲኖሩ አንድም ቀን የፍቅር ታሪክ ሳያስመዝግቡ አንዱ አንዱን ሲያሳድደው በጠላትነት ይኖራሉ አዳም ከፈጣሪው ከተጣላበት ቀን ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በዚህ ሕግ ጸንተው ይኖራሉ ከዚያ በፊት ግን ይህ እንዳልነበረባቸው ግልጽ ነው እመቤታችንም ከአዳም ርኩሰት አስቀድሞ የነበረችው ሰላማዊ ምድር ናትና እንስላት አራዊት አዕዋፍ የተሰኙ እስራኤልን ካህናተ እስራኤልንና አሕዛብን በፍቅር መረብ አስተሳስራ አንድ መንጋ አድርጋለች የቀደመ ታሪካቸውን ስናይ ጦርነት ነው እስራኤል ምድረ ርስትን ሲወርሱ አሕዛብን አሳደው ነበር ኢያ ዛሬ ግን ነገሩ እንዲህ አይደለም ዘለዓለማዊቷን ምድር መንግሥተ ሰማያትን አብረው ለመውረስ ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት ተራራ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ ተብሎ ጥሪው ተላልፏል ኢሳ የቀደመውን የፅርቅ ዘመን የመለሰች የመጀመሪያውን የሰላም ኑሮ ያስታወስች ከጥንተ አብሶ በፊት የነበረችዋ ንጽሕት ምድር በአውነት አመቤታችን ናት ለጴጥሮስ እውነቱን ሊመሰክር የመጣው የእግዚአብሔር መላክስ ቢሆን ያስረዳው ነገር ቢኖር ይህን አይደል። ሳይገባው ይህን ኅብስት የበላ ይህንም ጽዋ የጠጣ የጌታችን የኢየሱክ ክርስቶስ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት እንዲል ቆሮ አባቶቻችንም መንፈስ ቅዱስ የነገራቸውን ሲነግሩን ይህ የሕይወት ዛፍ ክርስቶስ እንደሆነ ነግረውናል ዳግመኛ ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን ይፄውም ሥጋና ደሙ ነው እያሉ በጣም የሚገርመውና ይህን ቃላችንን የሚያስረዳልን ደግሞ ከዛፉ ሥር የሚፈልቁት አራቱ አፍላጋት ናቸው እነዚህ አራቱም ወንዞች ከአንዱ ዛፍ ሥር ይመነጫሉ መጀመሪያ ገነትን ከዚያም በአራቱ የዓለም ማእዘናት እየዞሩ መላውን ዓለም ያጠጣሉ የደረቀውን ያለመልማሉ ለፍሬም ያደርሳሉ እነዚህ አፍላጋት የማይከቡት ምድር የለም ቅድስት ኦሪት ይህን ስትናገር ዘፍ ቅድስት ወንጌል ደግሞ የዚህን ምሥጢራዊ ትርጓሜ ትናገራለች እንዲህም ስትል ታስረዳለች የሕይወት ምንጭ ውኃ ከሆዱ የሚፈልቅ ዮሐ የሕይወት ምንጭ ክርስቶስ ሲሆን ውኃው ደግሞ ከሆዱ ማለትም ከባሕርዩ የሜፈልቀው ቅዱስ ቃሉ ነው እሱም በአራቱ ወንጌላውያን በኩል የደረስን ነው በገነት መካከል የበቀለው የሕይወት ዛፍ ከበታቹ አራቱን አፍላጋትን እንዳፈለቀ ጌታችንም አራቱን ወንጌላውያን ር መ ውዳዘሐሙስ ሕፎወተ ማርያም ድገገፅ አሥነስቶ ወንጌልን አራት ክፍል አድርጐ የማዳኑን ምሥጢር የሚገልጽ ነው መጀመሪያ ኢየሩሳሌም ለአንድ ዓመት ከሌላው ዓለም ተለይታ በዚህ ቃል መንፈሳዊ ልምላሜን እንድታገኝ የተደረገ መሆኑን ታሪክ የሚነግረን እውነት ነው ምን አልባት የበዓለ ሃምሳ ቀን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ በዓለ ሠዊትን ለማክበር ከተሰበሰበው ልዩ ልዩ ሕዝብና ነገድ በስተቀርና እግዚአብሔር የመረጣቸው እንደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ያሉ ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር በዚያች አንድ ዓመት ውስጥ ወንጌልን ሰምቶ ያመነና የተጠመቀ ፍጡር በምድር ላይ አልነበረምየሐ ሥራ ችኃ ለአንድ ዓመት በኅብረት ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ የአራቱንም ወንጌላውያን ቃል በኢየሩሳሌም ብቻ ይሰብኩ ዘንድ ታዘዋልና ከዕፀ ሕይወት ሥር የሚመነጩት አራቱ ወንዞችስ በኅብረት ሆነው ገነትን ዞረው ካጠጡ በኋላ አይደል ወደ ሌላው ዓለም የሚወጡት ከወጡ በኋላ ግን አራቱም ወንዞች ዓለምን ለአራት ተካፍለው ያለ ከልካይ ይፈሳሉ የደረቀውን ይህን ዓለም ያለመልማሉ ወንጌልና ወንጌላውያንም ከኢየሩሳሌም በሏላ ዓለምን ተካፍለው መጥተው ሲስብኩ በመላው ዓለም ያልደረሱበት የለም ያለ ከልካይ እንደሚፈስ ውኃ ከዓለም ዳርቻ አስከ ሌላው ዳርቻዋ ተጉዝዘዋል እንዲያውም ነቢዩ ይህን ሲገልጽ ውስተ ኩሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ ወእስክ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ ሲል ዜና ስብከታቸው ያልደረሰበት ዓለም የሌለ መሆኑን ተናገረ መዝ እንዲያውም በገነት ያሉት አራቱ አፍላጋት ከምድራዊው የሕይወት ዛፍ ሥር የሚመነጩ መሬታውያን በመሆናቸው ወደ ምድር እንጂ ወደ ሰማይ የፈስሱበት ጊዜ የለም። ማረፊያው ልትሆን መርጧታል ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለሁና በእርሷ ውስጥ አድራለሁ መዝ ዘፍ ይህንንም ቅዱስ ገብርኤል ሲተረጉመው መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል ብሎ በመናገሩ ለዘለዓለም የተዘጋጀች የአምላክ ማረፊያ ድንግል ማርያም እንደሆነች ታወቀ ተረዳ ን ሕደዉተ ማርያም ደገገስ ምዕራፍ ቅድመ ጽንሰታ እግዚአብሔር ለሚሠራው ሥራ ሁሉ ጊዜ አለው ውብ አድርጎ የሠራቸው ነገሮችን በጊዜውና በፈቀዴው ስዓት አድርጓቸዋል በምድር ላይ ከሠራቸው ውብ ነገሮች አንዷ አመቤታችን ናትና በፍጥረታት ልማድ ከእናትና ከአባቷ በሥጋና በደም ተከፍላ በነባቢት ነፍስ ሕያው ሆና በደማዊት ነፍስ ከብራ ከመገለጧ በፊት ለማኅበረ መላእክት በታላቁ መላክ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ ስሎ አሳይቷቸዋል ይህንም ቅዱስ ያሬድ በዜማው ሲገልጽ ሚካኤል መልአክ በክንፉ ተሸከማት የደመና መጋረጃም ጋረደላት ይላል የደመና መጋረጃ ብሎ የገለጸው በደመና የተሸፈነ እንዳይታይ በአካል አልታየችም ማለቱ ነው ለማኅበረ መላእክት በዚሁ መልኩ እንደገለጻት ለሰው ዘር ደግሞ በተለያየ መልክ የገለጻት ቢሆንም አዳም ከገነት በወጣ ጊዜ ኃጢአት ባወየበው ባሕርዩ ውስጥ እድፈት እና ርኩሰት የሌለባት ሆና በተስፋ ተገልጻ ነበር በጭቃ ውስጥ የወደቀ ወርቅ ከጭቃው ጋር ምንም አይነት ዝምድና እንደማይኖረው ሁሉ በበደሉ እና በመተላለፉ ሳትተባበር በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንዮ ታበራ የነበረች ንጽሕት ደም ነበረች እና በዚች ንጽሕት ባሕርይ የሚያድነው መሆኑን ገልጾለታል ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በአንድ ቦታ በተናገረው ማርያምስ ተኀቱ ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ፀዓዳ ማርያም ግን እንደ ነጭ ፅንቱ በአዳም ገላ ውስጥ ታበራ ነበር ብሉ የ ው መ መ አ ዋዜማ ዘታህሳስ ገብርኤል ሕደጠተ ማርያም ድገገስ ለአዳምም ትልቅ ተስፋ የሆነው ይህ እንደሆነ በአባ ሕርያቆስ በኩል መንፈስ ቅዱስ ተናገረን አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ አምገነት አዳም ከገነት በወጣ ጊዜ አለኝታ ስንቁ አንቺ ነሽ ብሉ በዚህም ሆነ በሌላ ምሳሌ ለፍጥረት የተገለጠችው ድንግል አመቤታችን የአግዚአብሔር የምሥጢር ሐሳብ ናትና በትንቢትና በምሳሌ እንጂ በአካል ሳትገለዋጥ ዘመናት ነጐዱዓመታት ዓመታትን ወለዱ ፅለታት ከወራት ጋር ተዋሐዱእመቤታችን ግን በእግዚአብሔር ኅሊና ተጠብቃ ለረጅም ዘመናት ተቀመጠች እንጂ አልተገለጠችም ሊደርሱባት ፈልገው አንዳንዶቹ በፍኖተ አዕምሮ ተፐዝው ፈለጓት አነ ሙሴ እነ አሮን ለአርባ ዓመታት በባሕርና በየብስ ሌሊትና ቀን ተጓዙ አሻግረው አዩአት እንጂ ወደ አርሷ ገብተው ማረፍ ከፍሬዋም መብላት ግን አልተቻላቸውም ሞት ከልክሎአቸዋልና ባለተስፋዎቹ አባቶቻችን ሁሉ የተሰጣቸውን ተስፋ እየጠበቁ ሳሉ አንቀላፉ የተስፋይቱን ምድር ዜና ከመልእክተኞች ብቻ እንደሰሙ የስንዴና የወይን ምድር መሆኗን እንደተረዱ ሳይወርሏሷት አለፉ ዘ ሙሴ የተስፋይቱን ምድር እንዲሰልሉ የላካቸው መልእክተኞች የነቢያት ምሳሌዎች ናቸው እንጂ ሌላ ምንድን ነው። አባ ዘዝዘክሦስ ዓዔ ሕደጠተ ማርያም ድንገስ ዜድ ን መቆ ድመነገስ በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊው ሊቅ የምታውቀው ሳይሆን የማታውቀው ሌላ መላክ መጣ ቀኝ ክንፉን ቢባርከው ኅብስት ሆነ ግራ ክንፉን ቢባርከው ወይን ሆነ በማለት መላክ የተባለው ቅዱስ ፋኑኤል ሳይሆን ክርስቶስ እንደሆነ ይተረጉማልዝማሬ ከዚህ በኋላ እናትና አባቷ ካህናቱና ሽማግሌዎችም ጭምር ተለይተዋት ፄዱ በዚህ ጊዜ አባቷ ዲዊት ከአንድ ሺህ ዓመት በፊት የመከራትን በጐ ምክር ተግባራዊ አደረገች ንጉሠ ዳዊት ይህን ቀን አስቀድሞ አይቶት ኖሮ ለሦስት ዓመቷ ብላቴና ምክርን ይለግሳታል ስምዒ ወለትየ ወርእዩ ወአጽምኢ እዝነኪ ርስኢ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ እስመ ፈተወ ንጉሥ ሥነኪ ልጀ ሆይ ስሚኝ አድምጭኝም የአባትሽን ቤትና ወገኖችሽንም እርሺ ንጉሥ ውበትሽን ወጻልና መዝ በዚች ዕለት ለቤተ አግዚአብሔር ሰጥተዋት ሲሄዱ እናትና አባቷን ምድራውያን ዘመዶቿንም ሁሉ ተወች እናትና አባት እግዚአብሔርን ዘመድ እና ወገን መላእክትን አድርጋለችና እናትና አባቷም ለእግዚአብሔር ሰጥተዋታልና እንደ ሳሙኤል እናት ሐና በየዓመቱ አልጉበትም አባ ሕርያቆስ እንደተናገረው መላእክት እና ሊቃነ መላእክት ካህናት እና ሊቃነ ካህናት ገብኙት እንጂ እንዲህ ሆና ከዓለም ርኩሰት ተሰውራ የሚያታልሉ የጐልማሶችን ድምፅ ሳትሰማ በመላእክቱና በካህናቱ ዜማ እየተጽናናች አደገች ዋዛና ፈዛዛ ሳቅና ጨዋታ ዘፈን እና አስክስታ ያልተቀላቀለበት አስተዳደግ አደገች አስቀድሞ በትንቢት እንደተነገረላት ለአስራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች የአሮን በትር ለአስራ ሁለት ሰዓት በቤተ መቅደስ መቆየቷ ሳይተክሏትና ውኃ ሳያጠጧት ለምልማ አብባ ው ሕደመዉተ ማርያም ደኀገስ አፍርታ መገኘቷ እመቤታችን በቤተ መቅደስ አስራ ሁለት ዓመት ለመኖሯ ማሳያ ሆኖ አስቀድሞ በምሳሌ የተቀመጠ ምሳሴአዊ ድርጊት ነበር አማናዊቷ በትረ አሮን ያለዘርዐ ብእሲ በኅቱም ድንግልና ጌታን የወለደችው ለአስራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ የቆየችው አመቤታችን ድንግል ማርያም ናት በዚያችኛዋ በትረ አሮን አሮንና ወገኖቹ ከሞት እንደዳኑባት በእመቤታችንም ፍጥረትን ሁሉ ከሞት የሚያድነው ፍሬ ሕይወት ጌታ ተገኝቷልና ሊቃውንት እመቤታችንን ሲያመሰግኗት በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ብለው ያመሰግኗታል ለጊዜው ይህ ሆኖ ሳለ ፍጻሜውና አማናዊው ምሥጢር ግን ያችኛዋ ለቱ ነገደ እስራኤል ምልክት ሆና ለዘለዓለም በቤተ መቅደስ እንድትኖር እንደተደረገች እመቤታችንም ለቱ ሐዋርያት ምልክታቸው ናት ነቢዩም ስለ አርሷ ሲናገር እርሱ እግዚአብሔር ምልክትን ይሰጣችኋል ብሎ የሐዲስ ኪዳኑ ታላቅ ሕዝብ ምልክት እመቤታችን እንደሆነች ይመሰክራል ኢሳ ዘጉል አስራ ሁለቱ ዓመት ሕገ መላአክትን ሥርዓት ሰማያዊትን ያጠናችበት ትንቢተ ነቢያትን ያወቀችበት የብዙ መጻሕፍትን ትንቢታዊ ቃል ያነበበችበት ወቅት ነው በአጠቃላይ ጥበብ ሥጋዊን ጥበብ መንፈሳዊን የተማረችበት ወቅት ይህ ነው ማለት ነው ጥበብ ሥጋዊ ማለት ወርቅና ሐር እያስማሙ መፍተል ያን የፈተሉትን ምንጣፍ መጋረጃ አድርጐ ለቤተ እግዚአብሔር መስጠት ነው ይህ ከቤተ እግዚአብሔር ደጅ ተሰብስበው እግዚአብሔርን ከሚያገለግሉ ከደናግለ እስራኤል የተማረችው ጥበብ ነው ተ ሩሩ መ ሕደጠተ ማርያም ድገንገፅ ጥበብ መንፈሳዊ ማለት ትንቢተ ነቢያትን ምሥጢረ መጻሕፍትን መመርመር ትንቢት የተነገረለት ሱባዔ የተቆጠረለት መሲሕ መጣ ቀረ ብሎ ማውጣት ማውረድ ሲሆን ይሄን ከካህናት አለቆች ከቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ተምራለች ከዚህም ጋር ከሰማያውያኑ መላእክት ቅዳሴን ዝማሬን የተማረችበት ወቅት ነበር ይህም በቀጣይ ሕይወቷ ይታወቃል በጸሎትና በዝማሬ ያሳለፈችው ጊዜ እንደሚበዛ ታሪክ ያስረዳናልና በመሆኑም በሕይወቷ ውስጥ ይሄ ዘመን ልዩ ነው ክእናት እና አባቷ ቤት ከቆየችው ሦስት ዓመት ጋር ሲደመር የአስራ አምስት ዓመት ብላቴና አድርጓታል » ን ሕደወተ ማርያም ድገገፅ ምፅራፍ ኛው ዓመት በሕግ ጠባይዓዊ በየጥቂቱ ማደግ ግዴታ ነውና በልማደ ፍጥረት እመቤታችን ድንግል ማርያምም አንድ ሁለት እያለች አስራ አምስተኛው ዓመት ላይ ደረሰች የሴቶች ትክክለኛ ጊዜ ማለት ይህ ዘመን ነው ዐቅመ ሔዋን የሚያደርሱበት የሚታጩበት በኋለኛውም ዘመን ከትንሣኤ ሙታን በጊላ በመንግሥተ ሰማያት የሚኖሩበት ለእግዚአብሔር ማደሪያነት የሚታጩበት ከሰማያዊው ንጉሥ ጋር የሚዋሐዱበት ዘመን ነው አመቤታችንም በዚህ ዘመን ሦስት ዐበይት ቁም ነገሮችን አከናውናለች ከጠላት ጋር መዋጋት አስከዚህ ዓመት ድረስ በአመቤታችን ሕይወት ውስጥ የተመዘገበ ከፍተኛ የጦርነት ወቅት የለም አሁን ግን እናቷ ሔዋንን ስታክል ጦርነቱ ተጀመረ ሰይጣን ከሔዋን ጋር ጦርነትን የጆመረው በዚህ እድሜዋ ላይ ሳለች ነበርና ቀዳሚት ሔዋን በዚህ እድሜዋ ድል እንደተነሣችለት ዳግማዊት ሔዋን እመቤታችንም ድል የምትነሣ መስሎት ጦርነቱን ጀመረው የሁሉ እናት ሔዋንን ራሱን በእባብ ሰውሮ እንደተዋጋት አመቤታችንንም የተዋጋት በካህናተአይሁድ በሕዝበአይሁድ ላይ ሆኖ ነበር የመጀመሪያይቱ ሔዋን ጦርነት የተጀመረው በገነት መካከል በቅዱስ ስፍራ ሲሆን ዳግማዊት እመ ሕያዋን ድንግል ማርያምንም ሰይጣን ጦሩን ያነሣባት ገና በመሠዊያው ስፍራ በተቀደሰው ተራራ በቤተ መቅደስ ሳለች ነው መ ሕደጠተ ማርያም ድንገፅ ምናምንቴ ሰዎችን አሥነሥቶ ከቤተ መቅደስ የመውጣቷን ጉዳይ ለማስፈጸም ደፋ ቀና ማለት የጀመረው ሰይጣን በገነት የነበረችውን ሔዋን ለመጣል የተጨነቀውን ያክል ተጨንቋል በሕዝቡ ጩት በካህናቱ ክፋት በጠንቋዮች አስማትና ምትሐት በእግዚአብሔር እጅ የተያዘች ክብርት ሕይወቷን ለማጥፋት በቅጠል ቀዳዳ እየተመለከተ ይከታተላት ነበር በ ዓመት የቤተ መቅደስ ቆይታዋ ከመላክቱ በሰማችው ስመ እግዚአብሔር ብቻ መጥቁል የተባለውን ጠንቋይ ከተከታዮቹ ሦስት መቶ ሰባ የሚጠጉ አጋንንት ጋር ከምድር በታች እንዲሆነ ያደረገች መሆኗን በታላቁ ነገረ ማርያም መጽሐፍ ተመዝግቧል ሰውን ወደ መቃብር ማውረድን በሴቶች በኩል የጀመረው ጠላታችን ሰይጣን በዛሬዋ ሴት በኩል ደግሞ ራሱ ወደ መቃብር ወረደ በመላእክት ሰይፍ አየታጨዱ የጠፉ አጋንንትም ብዙ ናቸው በታላላቅ ጦርነቶች ድልን የተጐናጸፉ እንደነ ዲቦራ ያሉ ታላላቅ ሴቶችን ታላቁ መጽሐፍ የመዘገበልን ሲሆን መሳ እና በረቂቃኑ የክፋት ሠራዊት ላይ ድልን በመጐናጸፍ ግን እንደ አመቤታችን የተሳካለት የለም ሁሉንም የማሸነፏ ምሥጢር ግን ትዕግሥት ነው በሕማሙ ሁሉ የማይናገረው የትዕግሥት እናቱ ትፅግሥት ድንግል ማርያም ሰይጣንን ያሸነፈችበት መሳሪያ ትዕግሥት ነው የቀደመችው ሴት በሰይጣን ለመሸነፏ ምክንያቱ ትዕግሥት አልባነቷ ነበር አዲሲቷ ሔዋን ግን ትዕግሥትን የተጐናጸፈች የትፅግሥት እናት ናትና በሔዋን መቸኮል ምክንያት የተወለደውን ሞት ክንፉን የሚሰብር የዘለዓለም ሕይወትን ወለደች በሕይወት መኖር ለሚታገጮ ሰዎች የተሰጠ ጸጋ ነው ዴዴመመቼ መ ብ ን ሕደወዉተ ማርያም ፎንገስ የሰው ትዕግሥት የሚገለጠው በፈተና ውስጥ ማለፍ ሲችል ነው የአመቤታችንም ትዕግሥት እስከ ወዲያኛው ለዓለም የተገለጠ ይሆን ዘንድ ሰይጣን በፈተና ላይ ፈተናን እየደራረበ ከቤተ መቅደስ እስኪያስወጣት ደርሶ ተፈታተናት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ በአርሷ ላይ ሥልጣን የሌለው መሆኑ ይታወቅ ዘንድ ብዙ ጊዜ ጥፋት ያላደረስባት ቢሆንም ከቤተ መቅደስ ልትወጣ ከሰማይ አምላክ ተወሰነ ከቤተ መቅደስ ስትወጣ እርሷን ግን አማናዊት ቤተ መቅደስ አደረጋት ሰዎቹ የሰው ልጅ የሠራውን ቤተ መቅደስ ሲከለክሏት እግዚአብሔር ግን የማትፈርስ ቤተ መቅደስ አድርጎ ለዘለዓለም ማረፊያ ልትሆነው ፃያውን ዓለማት ፃያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረት በሠራባቸው ቅዱሳት እጆቹ ሠራት ያን ጊዜ በነቢይ ስለ እርሷ የተባለው ተፈጸመ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ እግዚአብሔር በመካከሏ ነውና አትታወክም መታጨት ማጨት የነገሮች ሁሉ መቅድም ነው አዳም ሚስቱ ሔዋንን ሚስት ከማድረጉ አስቀድሞ አጫት። እያለ በዐውደ መስቀል ይናዘዝ ነበር ጦረኛው ሞት ተረታ ብዙዎችን የማረከው ዲያብሎስ ተማረከ ይህ የሹም ሽር ሥርዓት የተጀመረው ደግሞ በማሕጸነ ማርያም ነው ሕደወተ ማርያም ደንገስ መላኩ ገብርኤል እንደተናገረው በማሕጸነ ማርያም የነገሠው ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ የዳዊትን የአባቱን ዙፋን የሚሰጠው ለመንግሥቱም ፍጻሜ የሌለው ንጉሠ ነገሥት ነውና በዚህም የአዳም ባሕርይ ከቀደመው ይልቅ ወደ ተሻለ ጌትነት እንደመጣ አናምናለን እግዚአብሔር እንደተናገረ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነብሎ ዘፍ አዳም ከሦስቱ አካላት እንደ አንዱ ሆኖ በማይቋረጠው ምስጋና የተመሰገነበት ዘመን ነው የጸጋ የነበረው ምስጋና ለአዳም ባሕርይ የሚስማማ የባሕርዩ ሆነ የክርስቶስ ባሕርይ የአዳም ባሕርይ ነውና አሁን የሰው ልጅ የባርነቱ ደብዳቤ ተቀዶ ነጻነቱ ታውጆ በሥልጣን እንዲኖር ተፈቅዶለታል ያውም ከሥልጣን ሁሉ አንቀጥቅጦ በገዛን ጥንተ ጠላታችን ላይ መሾም እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሥልጣን ነው ለሰው ልጆችም የተሰጠው ሥልጣን ይፄው ነው ማቴ ከዚህ በኋላ ከእርሱ መከራን ከተቀበልን ክአርሱ ጋር አብረን እንነግሣለን እንዲያውም ባሪያዎች ሠልጥነውብናል ከእጃቸውም የሚሜታደገን የለም የልባችን ደስታ ቀርቷል አክሊል ከራሳችን ወድቋል ሰቆ ኤር ብሎ ይናገር የነበረው የሰው ልጅ ዛሬ ግን እንዲህ አይናገርም ከፍ ካለ ተራራ ላይ ቆሞ ተውህበ ሊተ ኩነኔ ሰማይ ወምድር በሰማይ እና በምድር ሥልጣን ተሰጠኝ ማቴ ብሎ ይናገራል እንጅ ክብሩን አጥቶ ለተለያዩ ጣዖታት አንዳልሰገደ ዛሬ ግን ፍጥረት ሁሉ ይሰግድለታል ፊል ይህ ሁሉ የሆነው በ ዓመቷ ብላቴና በእመቤታችን ማሕጸን ነው ከመጀመሪያይቱ ሔዋን የኃጢአት ባሪያ ቃኤል ማሕጸኗን የሚፈታ በዙር ሆኖ ተወለደ ከሁለተኛይቱ ሔዋን ደግሞ ለጌትነቱ መጨረሻ የሌለው ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስ ማሕጸኗን ሳይፈታ የበኩር ልጂ ሆነ ሕደወዉተ ማርያም ደገገፅ ገና በአባታችን በአዳም ወገብ በእናታችንም በሔዋን ማሕጸን በነበርን ጊዜ ያጣነውን ጌትነት ደግሞ በማሕጸነ ማርያም አገኘነው አሁን ግን በክርስቶስ በኩል ባገኘነው ድል ሐዋርያው እንደተናገረው ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋል ቆሮ መንፈስ ቅዱስ ስለ አመቤታችን ስንኳን የሰው ቅድስናና ንጽሕና የእግዚአብሔርም የማያጠራጥረው ጌትነቱ ያለምስክር ሊረዳ ሊረጋገጥ ስለማይችል የእመቤታችንም ቅድስናዋንና ባለሟልነቷን ያረጋገጥነው መንፈስ ቅዱስን ምስክር አድርገን ነው መንፈስ ቅዱስ ለሰው የሚመሰክረው በተለያየ መንገድ ነው በተአምራት ደጋግ ሰዎችን በማሥነሣት ግዕዛን ባላቸው እና በሌላቸውም ሥነ ፍጥረታት ላይ በማደር ከተፈጥሮአቸው ውጪ ታላላቅ ነገሮችን እንዲያደርጉ በማድረግ ሊሆን ይችላል ለአመቤታችንም ፈጥኖ በተደረገ ሦስት ምስክር ወላዲተ አምላክ መሆኗን መሰከረላት ይህ መላክ ቀደም ሲል እንዳነሣነው ከእግዚአብሔር የተላከ መሆኑን በብዙ መንገድ የገለጸ ሲሆን ከዚያ በመቀጠል የእመቤታችንን ክብር በሰፊው ይገልጻል ለክብሯ እንደሚገባ ሦስት ጊዜ ስግደትን ካቀረበ በኋላ የንጉሥ ማደሪያ ናትና የሚያምረውን ውዳሴ ልብን በሚመስጥ ድምፀ ቃና ለክብሯ እንደ ሚገባ አድርጐ አቅርቦላታል ከዚህም የተነሣ የመጀመሪያው ውዳሴ ማርያም ደጋሚ መላክ ብለው ይጠሩታል ዴ ዴዴ ቁጩ መራ ሽ ሕደወዉተ ማርያም ደንገፅ በዚህም መንፈስ ቅዱስ እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ የከበረች ቅድስት መሆኗን አስመሰክከረ እናታችን ሔዋን ፅፀ በለስን በልታ ባደረገችው ዓመፃ በስው ዘር ላይ በአጋንንት ይደርስ የነበረው ሽሙጥ እና እንግልት የሚያልቅበት ዘመን እንደደረሰ ለማጠየቅ በፊቷ ቆሞ ውዳሴን ያቀርብላታል ለቀደመችው ሔዋን ሰይፍን መዝዘው ግሩማን ሆነው ከታዩት መላእክት አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ነበርዛሬ ግን ከፊቱ ለተቀመጠችው ሔዋን ሰይፍን አይደለም የምስጋና እጅ መንሻን ይዞ ቀረበ ያችኛዋ እኮ የቃኤል እናት ናት ምን ብሎ ያመስግናት ይህችኛዋ ደግሞ የንጉሥ ክርስቶስ አናት ናት ክብራቸው ልዩ ልዩ ነው የመከራው ዘመን ማብቃቱን የምሕረት ዓመት መጀመሩን መንፈስ ቅዱስ መጀመሪያ የገለጸው ለእመቤታችን ነው ተፈሥሒ ፍሥሕት ማለቱ መርገም እንደተወገደ መዓዛ ንጽሕናዋ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደተወደደ የሚያመላክት ቃል ነው የመጀመሪያይቱ ሔዋን ከገነት ስትባረር በሕማም በጭንቅ ትወልጃለሽ የሚለውን የመርገም ቃል ሰምታ ነበር የወጣችው እመቤታችን ግን የስደተኞች ማረፊያ ገነት ክርስቶስን ስትጸንስ ከመጽነሷ አስቀድሞ በጆሮዎቿ የምስጋናን ቃል ሰማች ። ብሎ በሕዝቡ መካከል ሙታን ምስክርነትን እንዲሰጡ እስካደረገበት ጊዜ ድረስ የአባቶቻችን ከሳሽ እርሱ ክሱን አላቆመም ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያድግ እንደ ሁሉም ምድራውያን ሕጻናት ነውና ለእናቱ በነገር ሁሉ ይታዘዝ ነበር ውኃ እንዲቀዳ ስታዘው ውኃውን በወንፊት ቀድቶ ያመጣላት ነበር ውኃውን ቋጥሮ በነፋስ ምስሶ ላይ ሰቅሎ ስሙን ስማይ ብሎ ለሚጠራው ለእርሱ በወንፊት ውኃን መቅዳቱ ምን ይገርማል ተአምረ ኢየሱስ ሕይወተ ማርያም ድገገስ እንጨትም ልቀም ከተባለ ለቅሞ በነፋስ ትክሻ ላይ ጭኖ እያመጣላት ለአናቱ እና ለዘመዶቹ ሁሉ ያገለግል ነበር ሉቃ በዚህ ሁሉ ነገር መላእክት እና ሊቃነ መላእክት ይገረማሉ አጋንንት ይደነግጣሉ ባለመታዘዝ የተጀመረውን ኃጢአት በመታዘዝ ሊሽር መጥቷልና ይህን አገልግሎቱን ሲያዩ መላአክት በመገረም ዝም ይላሉ ሏያገለግሉት አንጅ ሊያገለግል የማይገባው ሆኖ ሳለ በፈቃዱ ይህን አድርጓልና በነገር ሁሉ እንደ ሕጻናት ሆነ እንጂ ከሕጻናት የተለየበት ምንም መንገድ አልነበረም ሁለት የስው ልጅ ሊያልፍባቸው የሚችሉ ሕግጋትን ፈጸመ ሩ ሕግ ጠባይዓዊ በተፈጥሮ የተሰጠ የፍጥረት ሕግ ሲሆን በቀዳማዊው ልደቱ ይህ አልነበረበትም በደኃራዊ ልደት ከድንግል ሲወለድ ግን ይህን የተፈጥሮ ሕግ ሳያዛባ ከማሕጸን ጀምሮ በየጥቂቱ አሳደገችው እንጂ አምላክ ነኝና ዕለቱን ተወልጄ ዕለቱን ልደግ አላለም ቀሩ ሕግ መጽሐፋዊ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ሕግ ሥር እንዲያልፍ አድሜው ለትምህርት ሲደርስ እመቤታችን ወስዳ ለገማልያል አስተምርልኝ ብላ ሰጠችው ሰው የሚሆነውን ለመሆን ይህን አደረገው እንጂ የመምህራን መሪያቸው የአዋቂዎች አውቀታቸው እርሱ እኮ ነው አናቱ ድንግል ማርያም ግን ነገሮችን ሁሉ በልብዋ እየጠበቀች ታስቀምጥ ነበር ለበዓል በኦሪታውያን ልማድ ወደ ቤተ መቅደስ የወጣችም እንደሆነ አስከትላው ትፄድ ነበር ወደ ቤተ መቅደስ መሄድን የጀመረው ልክ አስራ ሁለት ዓመት ሲሞላው እንደነበር መጽሐፍ ይመሰክራልሉቃ መቅ ወንጌል ሕደወዉተ ማርያም ድንገል በሌሎች ሌዋውያን ከፃያ ዓመት በታች እንዳይወጡ ሥርዓት ተሠርቶባቸዋል እርሱ ግን የሚወጣው በሊቃውንቱ መካከል ተገልጦ ለማስተማር ነውና በዚህ ታናሽ አድሜ ወጥቷልዘሌ እመቤታችን በእለተ ዐርብ ፅለተ ዓርብ ከሰማይ እስከ ምድር ከአድማስ እስከ አድማስ በሚኖሩ ፍጡራን ላይ በማለዳዋ ኀዘን የታወጀባት ሲመሽ ወደ ማታ ደግሞ በአጸደ ሥጋ በአጸደ ነፍስ ተድላ ደስታ የበዛባት ልዩ የመዳናችን ቀን ናት በዚህች ዕለት ግፅዛን ያላቸው እና የሌላቸው ልዩ ልዩ ሥነ ፍጥረታት አንገታቸውን ደፍተው በተሰበረ ልብ ሐዘናቸውን ገልጠዋል ሐዘናቸው ወደ ደስታ እስኪለወጥ የመክራ እንባን አንብተዋል አንዳንዶቹ የሚደርሱበትን አጥተው ብር ብር ሲሉ ነው የዋሉት በተለይም ደቀ መዛሙርቱ መድረሻ ለሌለው የሰው ዘር መድረሻ ሊሆን ጌታ በመስቀል ላይ ነውና እስከዚያው ድረስ ሁሉም መድረሻ አጥተው ተቸገሩ ኀዘን ሲበዛ ከባድ ነውና ምድር ሳትቀር ከኀዘኑ ከባድነት የተነሣ መሸከም አቅቷት ተንገፈገፈች ይህም ምሬቷ ደግሞ በአሕዛብ መንደር ሳይቀር ተሰማ እንዲያውም በአቴና ባለቸው አርዮስፋጎስ በተሰኘው ሥፍራ ቆሞ ይሰብክ ለነበረው ታላቅ የጥበብ ሰው ቅዱስ ዲዮናስዮስ ወደ ክርስትና መመለስ አንድ ምክንያት የሆነው የምድር መናወጧ የፀሐይም መጨለም የጨረቃም ደም መሆን የዓለማችን በጨለማ መዋጥ እና እነዚህን የመሳሰሉ የሥነ ፍጥረታት የሐዘን መግለጫዎች ናቸው ና ሕደጠተ ማርያም ድንገስ ፅለቲቱ አንገት ካስደፋቻቸው ሐዘን ልባቸውን ከሰበረባቸው ሰዎች አንዲ እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት አስቀድሞ ከሰላሳ ዓመት በፊት ሕጻኑን በቤተ መቅደስ የታቀፈው ሽማግሌው ስምዖን እንደተናገረው ልቧን የሚከፋፍል የመከራ ሰይፍ በነፍሷ አለፈ ሉቃ ጌታም አናቷ ሔዋን በሲኦል የምትቀበለውን መከራ እንድትቀበል ፈቃዱ ነውና ለአዳም እና ለሔዋን ልጃቸው አቤል በሞተ ጊዜ የሚያጽናና መላክ እንደላከላቸው ልጂ በመከራ ተይዞባት ለምታለቅሰዋ ሴት ለእመቤታችን የሚያጽናና መልአክ የላከላት አይደለም ቀኑን ሙሉ በመከራ እንድታሳልፍ ዝም ብሏታል እንጂ እርሷም የልጂን በአይሁድ እጅ መያዝ ከሰማችበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ጊዜ ከድንጋይ ሌላ ጊዜ ከመሬት እየወደቀች አለቀሰች ሲወለድ ጀምሮ በስደት በረሐብ በብዙ መከራ የተፈተነችለት ልጂ ሲያዝ እንደምን አታለቅስ ታለቅሳለች እንጂ በስደቱ ስለ እርሱ ራሳቸውን ለሞት የሰጡ ምድራዊ ሕይወታቸውን በዘለዓለማዊ ሕይወት የለወጡ ብዙ ሕጻናት ነበሩ ዛሬ ግን ስለ አርሱ መከራን ለመቀበል የደፈረ ማንም የለም አብረውት የነበሩት ሁሉ ከድተዋል የባሰባቸው አናውቅም ብለው ምለው ሸሽተዋል እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘንብሏል አብረውት ሊሞቱ ቃል የገቡት ሁሉ ከአጠገቡ ሲታጡ መንገደኛው ስምዖን ቀሬናዊ አፍሪካዊው ሰው ሸክሙን ተጋራውዓለምን ከነበረባት ሸክም ሊያሳርፍ እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ ወደ እኔ ኑ ማቴ ብሎ የጠራንን ጌታ ስምዖን አንድ ለአንድ ምዕራፍ አሳረፈው ምሥጢሩ ግን መስቀሉን ከክርስቶስ ተቀብላ ቤተ ክርስቲያን ልትሸከመው እንደሚገባት የሚያሳይ እንጂ የሚሜያሳርፈንን ጌታ ሕደፀተ ማርያም ደገገስ ለማሳረፍ የተደረገ አልነበረም ፍጡርማ የፍጡራንን ሸክም መሸከም ቢችል ኖሮ ይሄን ያክል ዘመን ከነነውራችን ባልቆየንም ነበር ጌታ እኮ የተሸከመው ነውራችንን ነው ከደቀ መዛሙርቱ ተለይቶ የመከራውን ጉዞ መጀመሩስ ለዚህ አይደል ደቀ መዛሙርቱም ተሳታፊዎች ሆነው ቢሆን ኖሮ በክርስቶስ የቤዛነት ሥራ የፍጡራንም እገዛ አለበት በተሰኘ ነበር።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Advertisement
Bottom banner

Download options | Convert to Pdf | Reading List | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact