Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ይህ አጭር ጽሑፍ በኢትዮጵያና በኢጣልያ መካከል ስለተነሣው ጦርነት ነገሩን ለመወሰን የሚቀርብለትን ጠቅላላ አስተያየት ለመቀበል የሚፈቅድ መሆኑን ሲገልጽ የኢጣልያ መንግሥት ከፋሲካ አስቀድሞ አይቻልም ብሎ አስታወቀ። ይኸውም ጦርነቱን ለማቆም ሲታሰብ አርሚስቲስ እንዲጠየቅና በዚሁ ረገድ የሚቀርበውን ዕርቅ እንዲደራደር ነው። የቪሬ ጦርነት። የጐጃም አውራጃ ገዥ የነበሩት ራስ እምሩ ስለ ነገራቸው በሻለቃ ዮሐንስ አብዶ መሪነት ጥቂቶች ወታደሮ አደጋ ይጥሉ ዘንድ ተላኩ። በመጀመሪያው ጊዜ የጠላት ወታደሮች በጩቤ ወይም በሳንጃ የኛዎቹ በጐራዴ ሲቃሉ ነበረ። ስለዚህም ብዙ ሰው ጣሉ። በዚያን ጊዜ በባላምባራስ መኩሪያ መሪነት የክብር ዘበኛ የሠራው የጀብዱ ሥራ በታሪክ ገጽ የመጀመሪያውን አምድ ሊይዝ የሚገባው ነው። እንዲሁም ምክቱሉ ሹም ግራዝማች ክፍሌ እገቱ ዛሬ ኮሎኔልን ባለ መድፍ ይዞ በአይላ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቀጥቋጦ ውስጥ ነበርና በኢጣልያ ሠፈር ላይ ባለማቋረጥ እየተኩሰ ያደረገው ጉዳት ከታሰበው በላይ ነው። በዚህ አኳኋን የቀጠለው ጦርነት ጨለማ ስላቋረጠው ፋታ ሳይሰጥ እንደክረምት ነጐድጓድ የንጉድ የነበረው የመትረየስና የመድፍ የአኤሮፕላንና የቦምብ ድምፅ ጋብ ሲል እንግዳ ነገር መሰለ። የእግዚአብሔር ኪነ ጥበብ ካስገኘው ብረት ጋራ ተጋጭቶ መሰበር እንጂ መስበር እንደማይቻል የታወቀ ነው። ይልቁንም የሠራዊቱን መበታተን በግርማዊነታቸው አጠገብ የሚገኙ ልዑላን መሣፍንትና ክብራን መኳንንት አይተው «ይህን ስፍራ ለቀን ሌላ አዲስ የጦር ሜዳ ለመክፈት የማይችል መሆኑ ተገመተና አዲስ አበባ ቀድሞ ለመድረስ ጥድፊያ ያለው እርምጃ ይሆን ዘንድ ተቁረጠ። እነዚህ ከዚህ በላይ የተመለከቱት የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በሰሜን ግንባር የማይጨው ጦርነት ከተደረገ በኋላ ኢጣልያኖች ድል አደረግን ንጉሠ ነገሥቱም ሞተዋል እያሉ ከሚነዙት ወሬ በቀር እርግጠኛውን ነገር ለማወቅ ካለመቻላቸው የተነሣ በጣም ተቸግረው ነበረ።
ነገር ግን የወልወል ግጭት ከተነሣ ከ ዓም ከኅዳር ወር መጨረሻ አንስቶ እስከ ዓም እስከ መስከረም ቀን ድረስ በሽምግልና ዳኝነት ወይም በቀጥታ ማኅበሩ ላደረገው ጉባኤ የጠፋው ጊዜ ለጠላት መሰናዶ ጠቃሚ ከመሆኑ በላይ እርግጠኛው ጦርነት ከተነሣ በኋላ አጥቂውን በኃይል በመጨቆን ፋንታ በዓለም መንግሥታት ማኅበር አሳቢነት የቆመው ይህ ኮሚቴ የጠላት ወራሪነት የሚወልደውን ፍጻሜ ለመመልከት በሚቻልበት መንገድ ለመጠበቅ ብቻ ምክንያት ከመሆኑ በቀር ለኢትዮጵያ መንግሥት ጠቃሚነት የሌለው መሆኑ ተገምቷል። ጠቅላይ አዝማች ማዕርጉ ዋና የጦር ግንባር ስም ራስ ሙሉጌታ የጦር ሚኒስትር ትግሬ ሰሜንን ራስ ደስታ ዳምጠው የሲዳሞና የቦረና ገዢ ዶሎ ኔጌሌ ደቡብ ደጃች ነሲቡ ዘአማኑኤል የሐረር አውራጃ ገዢ ውጋዴን ምሥራቅ እነዚህ የሦስቱ ዋና ዋና ግንባሮች አዝማቾች በውስጣቸው ያሉትን የጦር አለቆችና ወታደሮች በሚገባ እንዲያሰማሩ በሚቻልበት መንገድ እያንዳንዳቸው ቀጥሎ የተመለከተውን ማስጠንቀቂያ ከግርማዊነታቸው ተቀበሉ። ደግሞ ከዚህ በቀር የጀርመን የጦር ሠራዊት ወደ ፈረንሳዊ ከተማ ወደ ፓሪስ በተጠጋ ጊዜ የመንግሥቱ ሰዎች ቦታ ለውጠው የጦር ሠራዊታቸውን በብልሃት እንዲገጥም አድርገው ወደ ሌላ ከተማ ተዛወሩ። ከዚህም በኋላ የወረራዋ አኳኋን ስለ ተጀመረ ዋናውን ጦርነት ግጥሞያ እስከሚያደርጉበት ጊዜ ድረስ በየወሰኑ አቅራቢያ የሚገኑት የጦር አለቆቹ ምቹ ስፍራ እያዘጋጁና የጠላትን አደራረግ እያጠኑ እንዲቆዩ ተነግሮዋቸው ስለ ነበረ በሰሜን ግንባር የልዑል ራስ ሥዩም ጭፍሮች ማለት እነ ቀኛዝማች ዐባይ ካሣ በደሮ ተክሌ እነ ደጃዝማች ወራሴ አውግር በሚባለው ተራራ በኩል እርድ እየሠሩ ታጥቀው ይጠባበቁ ጀመር። ነገር ግን መጀመሪያ ጊዜ ኢጣልያኖች የድንበሩን መስመር አልፈው አገሩን ሲወሩ ቢራማና በዓዲ አርባዕቲ በኩል ከነበረው ከደጃዝማች ሣህሌ ጦር ጋራ ስለተገናኙ ምንም እንኳ በሚገባ ጦርነት ለማድረግ ባይፈቅድ ግጭቱን ለማስቀረት የማይቻል ሆነ ስለዚህ ደጃዝማች ሣህሌ በቴኔንቴ ምርጋንቲኒ አዝማችነት የሚጓዘውን የኢጣልያ ጦር ከጥቂቶች የቪሬ ወታደሮች ጋራ ሁነው በተጣራ ሜዳ ላይ ገጠሙት። በዚያን ጊዜ ከውጭ አገር የጦር መሣሪያ እንደሚበቃ ለማግኘት ተስፋ የተደረገበት ነገር ሁሉ በማወላወል ላይ ስለ ነበረ ብዙዎቹ የጦር አዝማቾች የብስጭት ሁኔታ ከመግለጻቸው የተነሣ ኢጣልያ በአጥቂነት አድዋን ስትይዝ በብዙ አኤሮፕላን ዛቻ ሲሆን ኢትዮጵያ የለ መሣሪያ ባዶ እጅዋን እንደ ነበረች እያሳሰበ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀጥሎ የተመለከተውን ቴሌግራም ለዓለም መንግሥታት ማኅበር አስተላለፈ። ወዲያው ጦርነቱ ከመነሣቱ ትንሽ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ስለ ጦር መሣሪያ ግዢ ከጀርመን ከቤልጅክ ከዳነማር ከፈረንሳይ ከስዊስ ከስዊድን ከቼኮዝሎባኪያ ከቱርክ መንግሥታት ጋራ ተነጋግሮ ስለ ነበረ ይህንኑ ምክንያት በማድረግ የኢጣልያ መንግሥት ከመቃወሙ የተነሣ ታገደ። ይህን ሁሉ የመሰለው ግጭት እየቀጠለ ሳለ ልዑል ራስ ስዩም ጦርነት ይገጥሙ ዘንድ አልተፈቀደም ነበርና የጠላት ጦር ወደ ፊት እርምጃውን ከማፋጠኑ የተነሣ አደጋ እንዳይሆን ሠራዊታቸውን ይዘው ወደ ተንቤን ለመሄድ ቆረጡ። ከዚህ በኋላ ጃንሆይ ወደ ሰሜን የጦር ግንባር ለመሄድ የሚነሠበት ጊዜው ስለ ደረሰ በውጋዴን ግንባር ከልዩ ልዩ አዝማች ጋራ የተሰለፈው የጦር ሠራዊት ምን ሞያ እንደ ሠራ ለመመልከትና ለማጽናናት ይልቁንም ብዙዎቹ የጦር አለቆች ከጃንሆይ ጋራ እንድንሠለፍ ይፈቀድልን ሲሉ ለምነው ነበርና በየትኛውም የጦር ግንባር የሚሠራውን ለማወቅ ጃንሆይ ቅርብ መሆናቸውን ለማስረዳት ኅዳር ቀን ሰዓት ሲሆን ከአዲስ አበባ ተነሥተው ቃኘው ይባል በነበረው አኤሮፕላን ጅጅጋ ልክ በ ሰዓት ደረሱ። ነገር ግን በችግር ምክንያት በቱ ማዕዘን ተበታትነው የነበሩት ኢጣልያኖች እንደመሪያቸው ቃል አዲስ ዓለም ለመውረስ ተጠርተው ሲሰበሰቡ በተደረገው ግምት ኢጣልያኖች ኢትዮጵያን ለመውጋት ቀርቶ ሌላም ጦርነት የጠማው መንግሥት ቢኖር በቂዎች ናቸው ቢባል አያሳፍርም ነበርና በዚያን ጊዜ ኢጣልያ በእውነትም እንደ ኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ አገር ርዳታ አላስፈለጋትም። ስለዚህ ራስ ደስታ በውጣቸው የሚገኙትን የጦር ሠራዊት ይዘው አብዛኛው የግራዚያኒ ጦር በውጋዴን በኩል ሰሞኑን የበረታ ጦርነት ያደርግ ስለ ነበረ ለጊዜው ከርሱ ጋራ የአለውን የጦር ኃይል ጥሶ በስተጀርባ ለመክበብ አስበው ነበረ። ታኅሣሥ ቀን በተደረገው የቦምብ አደጋ ምክንያት በጉዞም ሆነ በሠፈር የነበሩ ወታደሮች ተለያይተው ነበርና መንገሻ ያለው የሚባለው ሰው በግግሩ ውስጥ ከድቶ ወደ ኢጣልያኖች ለመግባትና ለጊዜው የኢትዮጵያ ጦረኞች የሚገኙበትን ሁኔታ ዘርዝሮ ለማስረዳት ተመቸው። ምንም የጦር ክፍል ሠራዊት የሌለበት መሆኑ በኦፊሲዬል ተነግሮ ሰላማዊነቱ በተረጋገጠው በሐረር ከተማ የተደረገው የኢጣልያ ቦምብ አደጋ ስለ ጦርነት የተወሰነውን ሕግ የሚሽር ነው። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ከኅዳር ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት ደ ቀን ድረስ እደሴ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ታላላቅ ሥራዎች ፈጽመዋል። በመጨረሻው ልዑል ራስ ሥዩም ወደ ልዑል ራስ ካሣ ተጉዘው ኅዳር ቀን ሙጃ ከሚባል ተራራ ተገናኙ። በላይኛው ፓራግራፍ እንዳታወቅነው ልዑል ራስ ሥዩም ከልዑል ራስ ካሣ ጋራ ለመገናኘት ገንቤንን ለቀው በተጓዙበት ጊዜ ተንቤን በጠላት እጅ እንዳትገባ ወታደሮች ከሁለቱም ወገን ተደርገው እንዲከላከሉ አስፈላጊነቱን ተመልክተው ነበርና በዚያ መሠረት ደጃዝማች ኃይሉ ከበደ ደጃዝማች ኃይሉ ተስፋዬ ጸሐፌ ትእዛዝ አፈወርቅ በጠቅላላው ደጃዝማች በበርጅሮንድ ለጥ ይበሉ ገብሬ አዝማችነት በግምት ከሺ ወታደር ጋራ ተላኩ። ስለዚህም ቀደም ብሎ በግብጽና በእንግሊዝ ሱዳን በኩል ሌላ የጦር ግንባር ለመክፈት ይቻል እንደሆነ በመመርመር አመካኝቶ ያን ጊዜ የቅኝ አገር ክፍል ዋና ጸሐፊ የነበረውን ማሬሻሎ ባዶሊዮን ከሴሶና ጋራ ልኮት ነበርና በተመለከተው መጠን የጦርነቱን ሁኔታ በማናቸውም አኳኋን ከርሱ በቀር ሊያውቀው ለመራ የሚችል የለም ሲል ለጄኔራል ደቦኖ ምትክ አድርጎ እንደገና ላከው። ከጥቂት ቀን በኋላ ማለት ጥር ቀን ልዑል ራስ ካሣ ከአቢይ አዲ ከተማ ስለ ደረሱ በደብረ አምባ ተራራ ላይ ከመኳንንቶቻቸው ጋር ወጥተው ወይም ጄ ኪሎ ሜትር ያህል ራቅ ብሎ በሹማርዌ አጠገብ የሰፈረውን የጠላት ሁኔታ ለመመልከት ቻሉ። እንዲሁም በዚያው ሰሞን ደጃዝማች ወርቅነህ በማልፋ በኩል ከጠላት ጋራ ጦርነት አድርገው ስለቆሰሉ ደጃዝማች ወንድ ወሰን ለእርዳታ እንዲደርሱላቸው ተደረገ። ጥር ቀን በዚሁ ጦር ሜዳ የጀብዱ ሥራ የሠሩ ጀግኖች በልዑል ራስ ካሣ ፊት እየቀረቡ ይፈክሩ ስለ ሥራቸውም አፈጻጸም ማስረጃ ጉዳይ ይጥሉ ወይም በምርኮ የያዙዋቸውን የኢጣልያ ወታደሮች ያስረክቡ ጀመሩ። በዚያን ጊዜ መቀሌ ሆኖ የአምባ አራዳምን ተራራ የሚመለከተውን የኢጣልያን ጦር ምቹ ሥፍራ ይዘው ይጠባበቁ የነበሩት ደጃዝማች መሸሻ ወልዴ የከንባታ ጦር አዝማችን ደጃዝማች በየነ አባ ስብስብ የኮንታና የቆጫ ጦር አዝማችን ደጃዝማች መንገሻ ይልማ የፈረስ ዘበኛ አለቃ ሌሎችም ጥቂቶች መኳንንቶች በተንቤን በኩል ገፍቶ የመጣውን ጠላት ይከላከሉ ዘንድ እንዲዘዋወሩ ስለ ተደረገ ጠላት አምባውን ለመያዝ የሚችልበትን ፕላን ያዘጋጅ ጀመረ። በዚያን ጊዜ በሺሬ በኩል ይከላከሉ የነበሩት ደጃዝማች ገብረ መድኅን ረዳት ጦር እስኪደርስላቸው ወደ ዳር ሆኖ መጠባበቅ ግድ ሰለ ሆነባቸው የኢጣልያ ጦር እሰክ ተከዜ ወሰን ድረስ ገፍቶ ነበርና የደጃዝማች አያሌው የጦር አዝማች ፊታውራሪ ሽፈራው አባ ከንትር ቀድመው ተጓዙ። በዚያን ጊዜ አኩስም የነበረው የጠላት ጦር አንዳንድ ጊዜ ነፈረስ እየወረረ የሺሬን አውራጃ ሰብልና የባላገሩን ቤት አቃጥሎ ከመመለሱ በቀር የራስ እምሩ ወታደር እስከሚገኝበት ደርሶ ጦርነት ለመግጠም አልደፈረም ነበር። ከጥቂት ቀን በኋላ ግን የራስ እምሩ የጦር አበጋዝ ፊታውራሪ ክንፌ በሰለክላካ ክፍል በእዳጋ ሰኑይ ሰፍረው ሳሉ የኢጣልያ ጦር መጥቶ የካቲ ቀን ዓርብ አደጋ ስለጣለባቸው በብርቱ ተከላከሉ። በዚያን ጊዜ ከርሳቸው ጋራ የነበረው ጦር በመጀመሪያው ጦርነት ምክንያት ጉዳት አግኝቶት ስለ ነበረ ከራስ ሙሉጌታ ጋራ በአምባ አራዳም ክፍል የነበሩት እነ ደጃዝማች በየነ አባ ሰብስብና እነ ደጃዝማች መሸሻ ወልዴ እነ ደጃዝማች መንገሻ ይልማና እነ ፊታውራሪ ዘውዱ አባኮራን በጠቅላላው ሺ ያሚያህል ወታደር ይዘው የካቲ ቀን ዓቢይ ዓዲ መግባት ጀመሩ። በዚሁ ቀን በ ሰዓት ተሩብ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ይጠበቅ የነበረው የጦር መሣሪያ ለልዑል እራስ ካሣ ስለ ደረሰ ለጦርነት መዘጋጀት ሆነ። እንዲሁም ከጀ ቀን በኋላ በዚሬ አውራጃ ጦርነት እንዲጀመር አዝዞ ኛው የተንቤን ጦርነት ለየካቲት ቀን ይሆን ዘንድ አስታወቀ። ቀጥሎም ደጃዝማች መሸሻ ወልዴ በብርቱ ስለ ቄሰሉ በየሌላው ክፍል የሚሠራው ጀግና ምንም እንኳ የአለበትን ግንባር አጠንክሮ ቢቄይ ከዚህ በላይ እንደጠቀስናቸው ያሉ የጦር አለቆች በመሞታቸው ወይም በመሰላቸው ምክንያት በሌላው በኩል ያለው ኃይል በመላላቱ ይልቁንም የወርቅ አምባ ተራራ በመያዙ ጦርነቱን ሳያቋርጡ ወደ ዓቢይ ዓዲ ማፈግፈግ ግድ ሆነባቸው። የኢጣልያ ወታደሮች ወደ ዓቢይ ዓዲ ሲገፉ ከኢትዮጵያውያን በኩል የጠነከረ መከላከል በሚደረግበት ጊዜ በልዩ ልዩ ሥፍራ ታልቦ የተጠመደው የኢጣልያኖች መድፍ በራስ ካሣ ሰፈር ላይ ከሚተፋው የእሳት አሎሎ በላይ አኤሮፕላኖች ሊነገር በማይችል ጭካኔ ቦምብ ስላዘነሙበት ልዑል ራስ ካሣ ልዩ የጦር ፕላን ለማዘጋጀት የዓቢይ ዓዲን ከተማ ለቀው ወደ ኋላ ከማፈግፈጋቸው የተነሣ በዚሁ ቀን በ ሰዓት ጠላት መንደሩን ለመያዝ ቻለ። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ደጃዝማች ወንድ ይራድ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ሊቀ ሊቃውንት ገብረ አብ ልዑል ራስ ካሣ ደጃዝማች ወንድ ወሰን ካሣ ልዑል ራስ ሥዩም ደጃዝማች አበራ ካሣ ፊታውራሪ ብሩ አቶ ወልደ ጊዮርጊስ ወዮ ከዚህ በኋላ ከሌሊቱ ሰዓት ሲሆን የጦር ሠራዊቱ ወደ ፊት እንዲገፋ ትእዛዝ ተሰጠው። ጦርነት ያልቀመሰ አዲስ ወታደርና ለቀህ ያላስፈነጠረ ገና ከፋብሪካው የወጣ መሣሪያ በየጊዜው ከሚልክ ጠላት ጋራ በብዙ የጦር ሜዳ ከመዋሉ በላይ በቦምብ የተደበደበ በኤፕሪት የተመረዘ በረሀብ የተሰበረ በጉዞው ሁሉ የባላገር ጦርነት ያልተለየው የኛ ወታደር አዲስ የጦር ሜዳ ለመክፈት የማይችል መሆኑ ተገመተና አዲስ አበባ ቀድሞ ለመድረስ ጥድፊያ ያለው እርምጃ ይሆን ዘንድ ተቁረጠ። እነዚህ ከዚህ በላይ የተመለከቱት የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በሰሜን ግንባር የማይጨው ጦርነት ከተደረገ በኋላ ኢጣልያኖች ድል አደረግን ንጉሠ ነገሥቱም ሞተዋል እያሉ ከሚነዙት ወሬ በቀር እርግጠኛውን ነገር ለማወቅ ካለመቻላቸው የተነሣ በጣም ተቸግረው ነበረ።