Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

መልእክተ አትናትዮስ 1.pdf


Advertisement
  • word cloud

መልእክተ አትናትዮስ 1.pdf
  • Extraction Summary

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ መልእክት ዘቅዱስ አትናቴዎስ ቁጥር አርባ አምስት ዴዴ ጨሙ መ መ ው መጆቨሽ መግቢያ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ወሳኝ ጊዜያት የሚባሉ ወቅቶች ነበሩ ቤተክርስቲያን በአገልግሎት ስኬት ያስመዘገበችበት ወይም ተፈትና እንደ ወርቅ ጠርታ የተገኘችበት ጊዜ ሊሆን ይችላል ከእነዚህ ጊዜያት አንዱ ቅዱስ አትናቴዎስ በእስክንድርያ በ ዓም ተወልዶ በዚያው አድጎ ተምሮ ለክብር የበቃ ነው። መልእክቶቹ የቀረቡበት ርአስ የተላኩት ክታቦች ቁጥር ሲሆን ከምንጩም በዚሁ አግባብ የቀረቡ ናቸው ስለዚህ ያልተገዑት ደብጫቤዎች ያልተካተቱበት በመሆኑ በቅደም ተከተል የቀረቡት በተገኙት ደብዳቤዎች ቁጥር ነው። እንግዲህ እርሱ ያለጊዜው የመጣ አልነበረም በጊዜው እንጂ እንዲህም አለ በተወደደ ጊዜ ሰምቼፃለሁ በመድኀኒትም ቀን ረድቼፃለሁ ኢሳ በዚህ መልእክቱም ቅዱስ ጳውሎስ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ ሳታቋርጡ ጸልዩ በሁሉ አመስግኑ ብሎ እንዳዘ ዘው ዘወትር ደስ ይለናል ተሰ ስለዚህ ከአባቶቻችን በተቀበልነው መሠረት ይህንን ወቅት ለማስታወስ ጊዜውን ለማወጅ ቸል የምንል አይደለም ስለዚህ የሐዋርያት ትውፊት እንዲጠበቅ እንጽፋለን ለጸሎት በተሰበሰብን ጊዜ አንዳችን አንዳችንን እናስብ ዘንድ በዓሉን በጋራ እናክብር በአንድ አፍም በአውነት ለጌታችን ምስጋና እናቀርብ ዘንድ። መዝ ሙረኛው ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜም ምስጋናህን ይናገራል እንዳ ለው መዝ ለእርሱ ምስጋና እያቀረብን የቅዱሳንንም ፍኖት መከተል የሚገባ ነው።

  • Cosine Similarity

አርዮሳውያን ካጎረፉት ጎርፍ ካነፈሱት ነፋስ በረድኤተ አግዚአብሔር ብቻውን ያሻገረ ድንቅ ቅዱስ ነበር ማለት ይቻላል ቅዱስ አትናቴዎስ በአገአግሉት ዘመኑ ከሚያከናውናቸው መንፈሳዊ ተግባራት አንዱ የእስክንድርያ መንበር ያደርግ የነበረውን የበዓላት በተለ ይም የትንሣኤ በዓል የሚከበርበት ቀን ማወጅ ነበር ሊዚህም ዓላማ ከበዓሉ አስቀድሞ በመላው ዓለም ላሉ አብያተክተርስቲያናት የበዓሉን ጊዜ ያውጅ ነበር ይህ ሥርዓት አስቀድሞም የነበረ ሲሆን ቅዱስ አትናቴዎስም አጠ ናክሮ ይፈጽመው የነበረ አባታዊ ተግባር ነበር ቅዱስ አትናቴዎስ በሚያስ ተላልፋቸው በእነዚህ መልእክቶችም የበዓሉን ቀን ከማብሰር ባለፈ ስሰበዓሉ አከባበር ስለክርስትና ሕይወት ስለቤተክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ ስለ መጻሕፍት ምሥጠራት ያበራራል ያስተምራል ይሰብካል ሸጊዜው በሚል ካቸው በእነዚሁ መልእክቶቹ ቀኖና ቤተክርስቲያን ሠርቶ ለሁሉም አብያተክርስቲያናት ይልክም ነበር በመከራ በስደት በፈተና የነበሩትንም ያጽናናል በእርሱ ላይ የሚደርሱ ፈተናዎችንም በመግለጽ እንዲጸልዩለት ለአብያተክተርስቲያናት ያሳስብ ነበር መልእክቶቹን የሚልከውም በሰላም ጊዜ ከመንበሩ ተቀምጦ ብቻ ሳይሆን በስደትም እያለ ካለበት ይልክሳቸው ነበር ሁሉም ክታቦቹ ባይገ ችም ተፈልገው የተገኙት ግን በያዚቸው መልእክቶች በየትኛውም ዘመን ላሉ ክርስቲያኖች የሚያንጹ በመሆናቸው በዓሰም አብያተክርስቲያናት ዘንድ እስከዛሬ እየተነበቡ አገአግሎት ይሰጣሉ ተጠርዘው በብዙ ቋንቋ ተተርጉመው በየአብያተክርስቲያናቱ አገልግሎት ይሰጣሉ ይህ መጽሐፍም እነዚህ መልእክቶቹ ተተርጉመው የቀረቡበት ነው የቅዱስ አትናቴዎስ የበዓሳት መልእክቶች ጳጳስ ሾሞ ቤተክህነቷን ላቀናላት ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምእመናንንም የእነዚህ መልእክቶቹ ጣዕም እንዲደርሷቸው ማድረግ አግባብ ነው በየደረጃው እየተጠኑ እየተስ ተካከሉ እየዳበሩ አዳዒስ መረጃዎችም እየተካከቱበት ወደፊት ዳብሮ የበለጠ ቭ እንደሚዘጋጅ ቢታመንም አሁንም በተዘጋጀበት ደረጃ ቢሆን የቃሉን በረከት መቋደስ አግባብ ነው ብዬ አምናለሁ እያንዳንዱ መልእክት ከጥቂቶች በቀር በተሟላ ሁኔታ ከጅምር እስከ ፍፃሜ ይዘታቸው ተጠብቆ ያሉ ሲሆን በዚህ የትርጉም ሥራም በአያንዳንዱ መልእክት ከአንድ አንቀጽ በላይ ከማይሸፍነው የበዓል ቀን አዋጁ በስተቀር ለክርስቲያናች ሕይወት በየትኛውም ጊዜ ያንጻሉ የተባሉ ሁሉም ክፍሎች ተተርጉመዋል ቅዱስ አትናቴዎስ ጽፏቸው ሳይገኙ ከቀሩት ደብዳቤዎችና አስተዳደራዊ ሆነው በጊዜው ብቻ ጥቅም ከሰጡ መልእክቶቹ የጳጳሳትን ዝርዝር ከያዙና የበዓሉን ቀን ብቻ ከማሳወቅ ባለፈ ሌላ ይዞታ ከሌላቸው ከጥቂት ደብዳቤዎች በቀር ሁሉም ተተር ጉመው ቀርበዋል ደብዳቤዎቹ ከ አስክ ዓም ድረስ እንደተጻፉ የሜታመትኑ ዓቸው የተገኙት በአጠቃላይ ከ የማይበልጡ ሲሆኑ የቀሩት ከተለያዩ ደብዳቤዎቹ የተወሰዱ ቁንጽሎች ናቸው በይዘታቸውም አብዛኞቹ በዓልን የማክበር ምስጢር አስፈላጊነት መሠረት ጥቅም ወዘተ የሚተነትኑ የሚያብራሩ የሚያመሰጥሩ ናቸው ሴሎች ደግሞ በዜው በአብያተክርስቲያናት ላይ ክአርዮሳወያንና ከመንፈቀ አርዮሳውያን በኩል ይደርስ የነበረውን መከራ እያነሣ ራሱንና ክርስቲያ ኖችን የሚያጽናናበት መከራውን አልፈው ለክብር የሚበቁበትን የቃሉን ኃይል የሚያስታጥቅባቸው ነበሩ ከኃጠአት ከኑፋቄ ስለመ ጠበቅ መከራን ስለመታገስ በዓል ለተባለ ለመንግሥተ ሰማያት ለመብቃት መኖር ያለበትን ፍጹም የሆነ ይክርስትና ሕይወት ደጋግሞ ስለሚያነሣ በየትኛውም ዘመን በየትኛውም ወቅት ክርስቲያኖች ቢያነቧ ቸው በሕይወታቸው የሜበረቱበትን የቃሉን በረከት ያገኛሉ እኔም ይህንኑ በማመን ቅዱስ አትናቴዎስ በልቡ የነበረ የፃ ይማኖት ሐሳቡን ለማወቅ ለመረዳት ለማመን ቅዱሱን ለማክበር አርአያ ነቱን ለመከተል ይጠቅማል በሚል ተርጉጫ እንደ አግዚአብሔር ፈቃድ ም ጨሥሥ»ሙጨጨጠ። እንግዲህ እርሱ ያለጊዜው የመጣ አልነበረም በጊዜው እንጂ እንዲህም አለ በተወደደ ጊዜ ሰምቼፃለሁ በመድኀኒትም ቀን ረድቼፃለሁ ኢሳ በዚህ መልእክቱም ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ጊዜ እንድናስብ እንድናስታውስ በተወደደ ሰዐት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ብሎ ጻፈልን ቆቁሮ ስለዚህ እርሱ መድኀኒት ሆኖናልና ወደ በዓል ጠራን አስቀድሞ እስራኤልም በተገዙለት ባከበሩት ጊዜ ወደ በዓላት ጠራቸው በዓመት ሦስት ጊዜ በዓል ታደርግልኛለህ አላቸው በዳ ወዳጆቼ ይህ አሁን እኛ የያዝነው ከእነዚያ አንዱን ነው የካህናቱም መለክት ያስተጋባል እንድናከብር ያነሣሣል መዝሙረ ኛው በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ ሲል እንዳዘዘው መዝ እንግዲህ ይህ ቃል በሁለቱም በመባቻና በታላቁ በዓል ቀን መለከትን እንዲነፉ ያዛል የጨረቃ ብርፃን ሙሉ ሆና ፍፁም የምትሆንበትን ቀን ታላቅ የበዓል ቀን አደረገው ስለመለከት ጥሪ ትእዛዝም ሁሉ እንደ መለከቶቹ ዓይነት ነው። ጾም ምን እንደሚ ያደርግ ስንጾምም በምን መልክ ሁኔታ መጾም እንዳለብን ሕጉ ያዘዘንን እናስተውል ነፍስ ክፉውን ሐሳብ ሁሉ ባልተክከተለች ጊዜ ትሑት ናት ይልቁንም በትሩፋት የምትመላለስና የበቃች ለመሆን ክፋትን ሳይሆን መልካምን ነገር ትመገባለች መልካም ሥራና ክፋት የነፍስ ምግቦች ናቸው ነፍስ ባላት ነጻ ፈቃድ መሠረት ከሁለቱ አንዱን ሥራ መልካም ሥራን ወይም ክፋትን ትመገባለች ወደ መልካም ሥራ ካዘነበለች በበጎ ሥራ ታድጋለች በጽድቅ በእርጋታ በየዋሕነት በጽናት ትፋፋለች ቅዱስ ጳውሎስ በአምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃል የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ ጢሞ በማለት ተናገረ በጌታም ዘንድ ይህ እውነት ነበር። ይልቁንም እግዚአብሔርን ማሰብ ከእርሱ የሆነው ቃሉም የሚፈሩትንና በአምነት የጸኑትን ለማኖር በምግብ ሁሉ ፋንታ ብቁነው ካልሆነማ በሰማይ ያሉ መላእክት የአብንና የመድኃኒታችንን ፊት ዘወትር ባያዩ ባልጸኑ ነበር ሙሴ ከእግዚአብሔር እየተነጋገረ ባለበት ጊዜ ሁሉ በእውነት በሥጋው በነፍሱ ጾመ በመለኮት ቃል ይኖር ነበርና ወደ ሰዎች በወረደ ጊዜ ግን እግዚአብሔርም ከእርሱ በተስወረ ጊዜ እንደሌሎች ተራበ በዚህም ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ከተነጋገረባቸው ከአርባ ቀናት በላይ ከተራራው እንደወረደ ጾመ አይባልም በአጠቃላይ ቅዱሳን እያንዳንዳቸው ለዚህ ከፍተኛ ምግብና ትሮ የተገቡ ነበሩ አማናዊውን በዓል ስለማክበር ወዳጆቼ እንግዲህ ነፍሳችን በመለኮት ማዕድ ምግብ በቃሉ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውጫዊ ሰውነታችንም በጾም ከጎለመሰች ይህንን የሚያድን ታላቅ በዓል አእናክብር የማያውቁ አይሁድ እንኳ የፋሲካን በግ በበሉ ጊዜ ይህን አምላካዊ ማዕድ በጥላው በምሳሌው ተቀበሉት ነገር ግን ምሳሌውን ጥላውን አላወቁትምና በዚህም ዘመን እንኳ የፋሲካን በግ ይበላሉ አነርሱ ግን ስተዋል ያለከተማዩቱና ያለ እውነቱ አካሉ እየኖሩ ናቸውና የይሁዳ ግዛትና ከተማዬቱ እስካሉ ድረስ ምሳሌው የፋሲካ በግ ጥላ ሆኖ ነበር እንግዲህ ሕጉ እነዚህ ነገሮች በሌላ ከተማ እንዳይፈጸሙ አዛልና ቨዳ ከዚህ በተጨማሪ ሕጉ ሁሉንም የተቃጠለ መሥዋዕትና ቁርባን ከኢየሩሳሌም ውጪ በሌላ መሠዊያ ቦታ እንዳያቀርቡ አዚል በዚህ ገለጻ መሠረትም መሠዊያውና ቤተመቅደሱ የታነጸው በዚያች ከተማ ብቻ ነሮና በሌላ ከተማ እነዚህን የአምልኮ ሥርዓቶች እንዲፈጽሙ ርመአክክት ከዝትኮጵን ሽትዓቲዎስ አልተፈቀደላቸውም ያቺ ከተማ ባለፈች በጠፋች ጊዜ እነዚያ ምሳሌያዊ ነገሮች ይወገዱ ዘንድ አሁን ግን አማናዊውን በዓል እናክብር እንግዲህ ጌታችን ተገልጧልና ከተማዩቱ ፍጻሜዋ ሆኗል እንግዲህ ሌላ ምስክር የምንሻ ከሆነ ዓይኖቻችን ያዩትን ማስረጃ እናድርግ የአይሁድም ምድር ዓለም አሁን ጠፍቷል ይህም ለጥላው ማሰፍ ፍፁም ማረጋገጫ ነው እነዚህን ነገሮች ከእኔ ብቻ የተማራችኋቸው አይደሉም አስቀድሞም የቅዱሳን ነቢያት ድምፅ እንዲህ ሲል ይጮኻል እነሆ የምሥራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው ናሆ ይህ ነቢይ ያስተላለፈው ምን ዓይነት መል ኦክት ነው እንዲህ ሊለን ሲንደረደር ነው ይሁዳ ሆይ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቷልና ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ ስአለቶችህን ክፈል ናሆ ናሆ አንድ ሰው አይሁድን የምትመኩበት ጥላ ያልፋል ሊላቸው ይቻለዋል። በተቀደሰ ሰላምታ ሰላም ተባባሉ ከእኔ ጋር ያሉ ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል ር ክክት ሽትን መሰክክተ ስትናቴዎስ መልእክት ዘቅዱስ አትናቴዎስ ቁጥር ሁለት ትእዛዛትን ስለማክበር ወንድሞቼ ሆያ። ስለዚህ በዓሉን በእውነት ባከበርን ጊዜ በሰማይ ለሚሆን ደስታ የተገባን ሆነን እንቆጠራለን ስንብት ከእኔ ጋር ያሉ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርቡላችቷል በተቀደሰ ሰላምታ ሰላም ተባባሉ። እንደውም አማናዊ ቃልን እያከበርን ከእናንተ ጋር በኅብረት ቆመን በበዓላችን ቀን ከፍ አድርገን ድምፃችንን እናሰማለን የሁሉ አምሳክ እግዚአብሔር ተናገር የእስራኤል ልጆች ፋሲካን ያክብሩ ብሎ አዞናልናሸት ፀ በመዝሙረኛው ቃል በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ ይላል መዝ ነቢዩም እንዲህ እያለ ይጮ ኻል ይሁዳ ሆይ በዓሎችህን አድርግ ናሆ ያልተማራችሁ እንደሆናችሁ አስቤ ቃልን የምልክሳችሁ ሆፔ አይደለም ነገር ግን ለማያውቁት ለእነሱ የተገለጠ ሆኖ አንዲገኝ በማሰብ ነው ምንም እንኳ ሰዎች የለያዩን ቢሆንም እግዚአብሔር ግን አሁንም አንድነታችንን አጽንቷል ስለዚህ እስከ አሁንም አንድን በዓል እናከብራለን አንዱንም ጌታ ዘወትር እናመልካለን። በመከራ ጊዜ ይሸነፋል በፍፃሜውም ፍሬ የሌለው ይሆናል አሁን ግን ነቢዩ እንዲህ ያለውን ቸልተኝነት ፍዓሜውን የአግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያደርግ ርጉም ይሁን እያለ ይነግረናል ኤር የእግዚአብሔር አገልጋይ ጥንቁቅና ትጉ መሆን ይገባዋልና በተጨማሪም አንደ ነበልባል የሚቃጠል የሚነድ በጥልቅ መንፈስ ውስጥ በሆነ ጊዜ ሁሉንም የሥጋ ፍላጐቶች አጥፋቷልና እንደ ቅዱሳን አባባል የሚበላ አሳት ወደ ሆነ ወደ እርሱ ወደ እግዚአብሔርም መቅረብ ይቻለዋል ዘዳ ዘዳ ሩ ዕብ ስለዚህ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር መላእክቱን መንፈስ የሚ መመ ርከፏክክት ሽትናቹስ አተካቲዎስ ያደርግ አገልጋዮቹን የአሳት ነበልባል መዝ ከግብፅ በወጡ ጊዜ ሕዝቡን እግዚአብሔር ለአነርሱ ሕግን የሰጠበትን ተራራው እን ዳይቀርቡ ከለከለ ምክንያቱም እንዲህ ያለ ብቃት የነበራቸው አልነ በሩምና ነገር ግን በመንፈስ የበረታ የማይጠገብ ጸጋ ባለቤት የሆነውን ብፁዕ ሙሴን ግን ወደ እርሱ ጠራው ሙሴም ብቻውን ወደ እግዚአብሔር ይቅረብ አለው በጸ በዳመናውም ተሰወረ ተራራውም በጨሰ ጊዜ አልተጉዳም ነበር ይልቁንም በዚያ በምድር ላይ እንደተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት መዝ ይወርዳሉ የመንፈስን ጸጋ ስላለማጥፋት ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ለእኛ የተሰጠን የመንፈስ ጸጋ በቅዝቃዜ ማደግ እንደማይገባው በተማጽኖ ሲመክር መንፈስን አታጥፉ ተሰ ብሏል አስቀድሞ የተሰጠንን ጸጋ እስከፍፃዓሜው አጽንተን ብንገኝ ከክርስቶስ ተሳታፊዎች ሆነን እንጸናለን አታጥፉ ብሎ ሲናገር የመንፈስ ጸጋ በሰዎች ኃይል ውስጥ ሲያድር በእነርሱ አንዳች ስቃይ ወይም ጤና የሚያመጣ ሆኖ አይደለም ነገር ግን ክፉዎችና የማያመሰግኑ ሰዎች በግልጽ አርሱን ለማቀዝቅዝ የሚመኙ ናቸውናነው ርኩስ የሆነውን ያልተቀደሰውን ይወዳሉ ባልተቀደሰ ግብራቸው መንፈስን ያሳድዳሉና ነው ተግሳጽን የሚገልጽ መንፈስ ቅዱስ ክፉውን ትምህርት ያርቃልና ከስነፎች ልቡና ድል ነሥቶ ይሔዳልና በሚመጣም ጌዜ ክፉውን ይዘልፈዋል ጥበብ አሁን ከማስተዋል ውጪ ሆነው አታላዮች ኃጢአትን ዉጻጆች ናቸውና አሁንም ገና በጨለማ ይጓዛሉ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር ዮሐ የተባለው ብርሃን የላቸውምና ርኸአክት ኸት ን ስለቃሉ እሳትነት ነቢዩ ኤርምያስ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደገባ እንደሚነድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ ደከምኩ መሸከምም አልቻልኩም ኤር እንዳለው እንዲህ ያለው ኤርሚያስ የተሸከመው አሳት ቃሉ ነው መልካምና ሰው ወዳጅ የሆነ አርሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ቃሉን በምድር ላይ አመጣ የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን አፈልጋለሁ አለ ሉቃ በነቢዩ ሕዝቅኤል እንደተመሰረከው እርሱ የሰውን ከሞቱ ይልቅ መመለሱን ይሻል ሕዝ ስለዚህ ክፉው ሁሉ ከሰዎች ውስጥ ተቃጥሎ እንዲጠፋ ነፍስም ወደ ንጽሕና ደርሳ ፍሬን ታፈራ ዘንድ በእርሱም ላይ የዘራው ዘር ሠላሳም ስድሳም መቶም ያማረ ፍሬ ማር ያፈራ ዘንድ ነው ለምሳሌ እነ ቀለዮጳ በመጀመሪያ ከማስተዋል ዕጦት የተነሣ ቢደክሙም በቷላ ግን በመድኀኒታችን ቃል ልባቸው ይቃጠል ነበር ከዚያ የእርሱን የትምህርቱን ፍሬ አፈሩ። ይልቁንም አሁን ብዙ መከራ እየተቀበልን ብዙ መናፍ ቃን በእኛ ሳይ በተነሥሠብን በዚህ ጊዜ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁ ጴጥ ወደ እኛ የቀረበ ውን ቅዱስ በዓል በምስጋና እናክብረው ስለበዓለ ፋሲካ አክባበር የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል ተብሎ እንደተጻፈለት እያንዳንዳችን ከእሴይ ሥር በወጣ በትር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ኢሳ እጆች ውስጥ ነን እግሮቻችንም ለወንጌል በመዘጋጀት ተጫምተው የቆሙ ነንና በዓሉንም ርዉስክክተ አትናቲዎስ ን ስትካቱዎስ ቅዱስ ጳውሎስ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም እንዳለው እናክብር ቆሮ እኛን ባሮቹን አክብሮን በክርስቶስ እንደታ ረቀን በእርሱም ላይ ባለ እምነት አንድ ሆነን እናክብር ለእውነት እንግዳ በሆኑ ቃላቸውና ፈቃዳቸው ባዋረዳቸው መናፍቃን ሥራ አንርክስ ነገር ግን በመከራችን ደስ ቢለን ከብረት አጥርና ከጨለማ ሰብረን እንወጣለን አስፈሪውን ባሕረ ኤርትራን ያለጉዳት እናልፋለን እንዲሁም የመናፍቃንን መታወክ ባየን ጊዜ ከነቢዩ ሙሴ ጋር ሆነን ያንን ታላቅ የውዳሴ መዝሙር በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና ለአግዚአብሔር እዘምራለሁ እያልን እንዘመራለን ከጸ ይህንን የውዳሴ መዝሙር ስንዘምር በውስጣችን ያለ ኃጢአት ወደ ባሕሩ ይጣላል በበረፃውም መካክል እናልፋለን በአርባ ቀናቱ ጉዞም በጾም በጸሎት በመታዘዝ በመልካም ሥራ እንጸናለን በኢየሩሳሌምም ሆነን ቅዱሱን ፋሲካ መብላት ይቻለናል የተወደዳችሁ ወንድሞቼ በዚህ ረዘም ባለ የጸም ወራት በጾም በጸሎት በማስተዋል በመቃኖቻችን ወርቀ ደሙን እንቀበላለን ከዚያም ከሚያስፈራው ጠላት አናመልጣለን ዘጸ ስለዚህ በዕለተ ቀዳሚት ምሽት ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈል ጋላችሁ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Advertisement
Bottom banner

Download options | Convert to Pdf | Reading List | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact