Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

መምህር ወለልደ ትንሣኤ.pdf


Advertisement
  • word cloud

መምህር ወለልደ ትንሣኤ.pdf
  • Extraction Summary

ጄጋ መግቢያ ሲኖፕቲክ ወንጌላት ሲኖፕቲክ ሃዐዐከር የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን ከቱ ወንጌላት ውስጥ በሚገኘው ትይዩ ታሪክ ደግሞ ሌዊተብሎ ተጠርቷል ማቴ ከበ ማርሉቃ ከጥንት ጀምሮ ባለው ታሪክና ትውፊት መሠረት ማቴዎስ እና ሌዊ የዚሁ የአንዱ ሐዋርያ ሁለቱ ስሞች መጠራት የተለመደ ሲሆን ሌዊ ከቀድሞ ጀምሮ ይተራበት የነበረው ስሙ ማቴዎስ ደግሞ ጌታን ከተከተለ በኋላ የተጠራበት ስሙ የቤክ ሊቃውንት ያስረዳሉ ቤተሰቡ ስለማቴዎስ ቤተሰብና ስለ ነገዱ በመቅደመ ወንጌል የተገለጠው ዲቁ የሚለው ስም ምናልባት የማቴዎስ አባት አልፍዮስ ሌላ ስሙ ሊሆን ይችላል መጠራቱ ማቴዎስ በራሱ ወንጌል ውስጥ በሚገኘው የሐዋርያት ስም ዝርዝር ውስጥ ወማቴዎስ መጸብሐዊ ቀራጩ ማቴዎስም » ተብሎ ተጠርቷልማቴ ቀራጭ የተባለውም በሥራው የሮማውያን ግብር ሰብሳቢ ስለነበር ነው የቀራጭነት ሥራውን ይሰራ እንደነበር የገመቱ ሊቃውንት አሉ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታምራትና ትምህርቶች በታሪኩ ውስጥ ሊነገሩ ይችላሉ ነገር ግን ቀለዮጳ ሀ ራሱን የቻለ ሌላ ደቀ መዝሙር ሉቃስ ነው።

  • Cosine Similarity

የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ» ስንል በማስተማር ዘመኑ ያደረጋቸውን ታምራትና ያስተማራቸውን ትምህርቶች ሳያጠቃልል ከልጅነት እስከ ዕርገቱ የተመዘገቡትን ታሪኮች ያመለክታል በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብዙ የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪኮች ተመዝግበዋል ከብዙዎቹ ውስጥ በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብቻ የተመዘገቡትን ዐ ታሪኮች እንመለከታለን ከአብርሃም ጀምሮ የተቄጠረው የክርስቶስ ሐረግ ትውልድ የጌታ ልደትና በተወለደ ጊዜ የሰብአ ሰገል መምጣት ጌታ በሕፃንነቱ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር መሰደድ ጌታ የማስተማር ሥራውን ለመጀመር ወደ ቅፍርናሆም መሄዱ በቅፍርናሆም ለመንግሥት ግብር መገበሩ የአስቀፃሮቱ ይሁዳ ጌታን አሳልፎ እንዲሰጣቸው የካህናት አለቆች ብር እንደመዘኑለት የአስቆረቱ ይሁዳ ጌታ እንደተፈረደበት ሲያይ ተጸጽቶ ውን ብር በቤተመቅደስ ጥሎ በመሄድ ታንቆ እንደሞተ ዐ ጴላጦስ ጌታ እንዲሰቀል አሳልፎ በሰጠው ጊዜ አጁን መታጠቡ ጌታ ተሰቅሎ ከሞተ በላ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የተቀበረበትን መር አትመው በጭፍሮች እንዳስጠበቁ ጌታ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለጠባቂዎቹ ገንዘብ በመስጠት « ደቀ መዛሙርቱ » « ስረቁት» ብለው እንዳስወሩ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረጋቸውን ታምራት ይዚል በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ጌታችን በማስተማር ዘመኑ ብዙ ታምራትን አድርጉ እንደነበር በተለያዩ ቦታዎች ይገልጻል ነገር ግን በማቴዎስ ወንጌል ታሪካቸው በተላይ የተመዘገበው ታምራት ናቸው ከእነዚህም ውስጥ በማቴዎስ ወንጌል ብቻ የሚገኙት ታምራት ሲሆኑ እነርሱም በመንገድ ሲያልፍ የተከተሉትን ሁለት ዕውሮች ወደ ቤት በገባ ጊዜ ዓይናቸውን በመዳሰስ አበራላቸው ግብር እንዲሰጥ በተጠየቀ ጊዜ ጴጥሮስን መቃጥን ሲጥል መጀመሪያ ከሚወጣው ዓሣ አፍ አታቴር እንደሚያገኝ በነገረው መሠረት አገኘ በኢያሪኮ የሁለት ዕውሮችን ዓይን አበራ ዐ ጌታ የተሰቀለ ዕለት ምድር ተናወጠች ዓለቶች ተሰነጠቁ መቃብሮች ተከፈቱ ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ከሙታን ተነሥና እና ከተማ ታዩ ሌሎች ታምራት በማርቆስ ወንጌል ጥናት ተመልክቶ ማጥናት ያስፈልጋል ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸውን ትምህርቶች ይዚል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀና ከተፈተነ በኋላ መጥምቁ ዮሐንስ አልፎ እንደተሰጠ በሰማ ጊዜ በገሊላ ውስጥ በቅፍርናሆም ከተማ ወንጌለ መንግሥትን ማስተማር እንደጀመረ የማቴዎስ ወንጌል ይናገረናል በዚህ ወንጌል የተመዘገቡት የጌታ ትምህርቶች ብዙዎቹ በገሊላ ውስጥ ያስተማራቸው ትምህርቶች ናቸውቢሆንም በመጨረሻ ጊዜው በይሁዳ አውራጃዎችና በኢየሩሳሌም ከተማ ያስተማራቸው ትምህርቶች ተመዝግበዋል በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የተመዘገቡት የጌታ ትምህርቶች ብዙዎች በማርቆስና በሉቃስ ወንጌላት ውስጥ ይገኛሉ በተለይም ከሉቃስ ወንጌል ጋር የሚያመላልሳቸው መሠረታዊ ነጥብ ከጌታ ትምህርት በስፋት መመዝገባቸው ነው ስለዚህ በዚህ ወንጌል የተመዘገቡትን ሁሉ አሁን ተመልክተን በዚህም ወንጌል ያልመዘገቡትን ደግሞ በማርቆስና በሉቃስ ወንጌሳት መመልከቱ የተሻለ ነው የጌታን ትምህርቶች የምናጠናው በሁለት ከፍለን ነው ሀ ጌታ በቀጥታ ራሱ ያስተማራቸው ትምህርቶች ጌታ ከሕዝብ ወይም ክሕዝብ አለቆች ወይም ከተማሪዎች ሳይጠየቅ በቀጥታ ራሱ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ትምህርቶችን ተመዝግበዋል አነርሱም በተራራ ላይ ሆኖ የስተማረው ረጅም ትምህርት የተራራው ስብከት ወይም አንቀፀ ብፁዓን በስምንት ምሳሌዎች ያስተማረው ትምህርት ሊከተለው የሚወድ ራሱን ክዶ እንዲከተለው የሰጠው ትምህርት ለልጁ ሠርግ ባደገ ንጉሥ ምሳሌ ስለመንግሥተ ሰማያት ያስተማረው ትምህረት ለጻፎችና ለፈሪሳውያን ስለግብዝነታቸው የሰጠው የተሣጽ ትምህርት ለ ከሚቀርቡለት ጥያቄዎች በመነሳት ያስተማራቸው ትምህርቶች ጌታ ከሚከተሉት ሕዝብና ከደቀመዛሙርቱ አንዲሁም ከተቃዋሚዎቹ ከሚቀርቡለት ጥያቄዎች በመነሳት ብዙ ትምህርቶችን አስተምሯል በዚህ ጥናት መሠረት በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የተመዘገቡት በጥያቄዎች መነሻነት ያስተማራቸው ትምህርቶች ናቸው እነርሱም ደቀ መዛሙርቱ ስለምን አንደማይጦሙ በተጠየቀው ተነስቶ ያስተማረው መጥምቁ ዮሐንስ በወኅኒ ሳለ በሳከለት ጥያቄ መነሻነት ያስተማረው ሕዝቡ የዳዊት ልጅ ይሆንን። የኢየሱስ ክርስቶስ የሕፃንነቱ ታሪክ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በተወለደ ጊዜ የሰብአሰገል መምጣት ሁ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ መሰደዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት የተደረጉ ነገሮች የመጥምቁ ዮሐንስ ምስክርነት ሁ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ መጠመቁ ቀንና ሌሊት ከጦመ በላ በዲያብሎስ መፈተኑ ጌታ በማስተማር ዘመኑ በገሊላ እና ባካባቢዋ የሠራው ሥራና ያስተማረው ትምህርት ማስተማር ሲጀመር ቱን ደቀ መዛሙርት እንደጠራ በተራራ ላይ የሰጠው ሰፊ ትምህርት በገሊላ ውስጥና ባካባቢዋ ያደረጋቸው ታምራት ቱ ደቀ መዛሙርትን በላካቸው ጊዜ የሰጣቸው ሥልጣንና ትአዛዝ በተለያዬ ጊዜያትና ቦታዎች ያስተማራቸው ትምህርቶችና ያደረጋቸው ታምራት ጌታ በማስተማር ዘመኑ መጨረሻ በይሁዳ አገር የሠራው ሥራና ያስተማረው ትምህርት ወደ ኢየሩሳሌም ከመውጣቱ በፊት በይሁዳ ያደረገውና ያስተማረው ወደ ኢየሩሳሌም በመውጣት ላይ ሳለ ስለሞቱና ስለትንሣኤው መናገሩ ጋ ሁ በኢያሪኮ ያደረገው ታምር ጋዐ ወደ ኢየሩሳሌም ከገባ ጀምሮ እስከተያዘ ድረስ ያደረገውና ያስተማረው የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በይሁዳ ሰመጡ ጭፍሮች ተይዞ እንደተመረመረ በመስቀል እንደሰቀሉት ሁ እንደተቀበረና መቃብሩን እንዳስጠበቁ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ሪ ሁ የተነሳ ፅለት ለማርያም መግደላዊትና ለሁለተኛይቱ ማርያም እንደ ታየ ጠባቂዎቹ ገንዘብ ተቀበለው ስለ ትንሣኤው የሐሰት ወሬ እንዳወሩ ኢየሱስ ለ ዱ ደቀ መዛሙርት የሰጠው የመጨረሻው ትአዛዝ የማርቆስ ወንጌል ጸሐፊው የሁለተኛው ወንጌል ጸሐፊ ቅ ማርቆስ ነው ቅማርቆስ ይህንን ወንጌል የጻፈው ራሱ በሚያውቀው መሠረት ብቻ ሳይሆን ከቅዱስ ጴጥሮስ በሰማውም መሠረት መሆኑን የሚገልጹ ትውፊቶች አሉ ከእነዚህ መካከል ሁለቱን እንጠቅሳለን አውሳብዬስ በቤተ ክርስቲያን ታሪኩ ውስጥ የጠቀሰው የፓፒያስ ቃል ነው እርሱም አንዲህ ይላል የየጴጥሮስ ትርጁማን የነበረው ማርቆስ የክርስቶስን አባባሎችም ሆነ ሥራዎች የሚያስታውሰውን ሁሉ ትክክል ጽፎ አስቀምጧጣል ጴጥሮስን ተከትሏል እንዳልኩት ከእርሱ ትምህርት የሚያስፈልገውን እየወሰደ የጌታን ነገር ጽፎ አጠናቅቋል » ብሏል አውሳብ የቤክታሪክ ጽሐፈ ስንክሳር ላይ የተመዘገበው ታሪክ ነው ይኸውም ሀ የቅጴጥሮስን ታሪክ በሚተርክበት ክፍል « ወነገሮ ለማርቆስ ወተርጉመ ሎቱ ወንጌለ ወአጽሐፎ» ይላል ስንክሳር ሐምሌ ለ የቅ ማርቆስን ታሪክ በሚተርክበት ክፍል ደግሞ ወኮነ ሎቱ ረድኦ ወበህየ ጸሐፈ ወንጌል ዘተርጉመ ሎቱ ጴጥሮስ ወሰበከ ቦቱ ሀገረ ሮሜ » ይላል ስንክሳር ያዝያ ከዚህ የምንረዳው ማርቆስ ወንጌሉን የጻፈው ራሱ ባስታወሰው መሠረት እና ከቅዱስ ጴጥሮስ ባገኘው ሠረት መሆኑን ነው ይህን አቀናጅቶ ሲጽፍ የመንፈስ ቅዱስ መሪነት ያልተለየው መሆኑ ግልጽ የታመሃ ነው ስሙ የዚህ ወንጌል ጸሐፊ ሁለት ስሞች አሉት አንዱ « ዮሐንስ» ሊሆን ሌላው ደግሞ « ማርቆስ ነው ይህንን በሚከተሉት ጥቅሶች እንረዳለን ዮሐንስ » ተብሎ የተጠራበት ክፍል ዮሐሃ ማርቆስ» ተብሎ የታጠራበት ክፍል የሐዋ ጢሞ ጴጥ ዮሐንስ የቀድሞ ስሙ ማርቆስ ደግሞ በኋላ የተሰጠው ስሙ እንደሆነ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ» ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ «ተብሎ በተጻፈው የማርቆስ የስም አጠራር ልንረዳ እንችላለን የዚህ ዓይነቱን አጠራር ሦስት ጊዜ እናገኛለን እነርሱም የሐዋ የሐዋ የሐዋ ናቸው ዮሐንስ» አይሁዳዊ ስሙ ሲሆን «ማርቆስ» ደግሞ ሮማዊ ስሙ እንደሆነ ብዙ መዝገበ ቃላቶች ይናረራሉ ያን ዘመን ብዙዎች አይሁዳዊያን ከአይሁዳዊ ስማቸው በተጨማሪ ሮማዊ ወይም ግሪካዊ ስም ነበራቸው ለምሳሌ የሐዋ ማር ተመልክት በዚሁ ዓይነት ቅማርቆስ እነዚህ ሁለት ች ሊኖሩት እንደቻሉ እንገነዘባለን ሆኖም ለስብከተ ወንጌል ከተለየ ከተሰማራ ጀምሮ በአብዛኛው የተጠራበት ስሙ «ማርቆስ» የተባለው ስሙ ነው ማርቆስ ማለት «ታላቅ መዶሻ» ማለት እንደሆነ ኢንተርፕሬተርስ ባይብል ዲክሽነሪ የተባለው መዝገበ ቃላት ይተረጉማል ትርጓሜ ወንጌል ግን ማርቆስ ማለት « ካህን ልኡክ» ማለት እንደሆነ ይገልጣል ያም ሆነ ይህ ማርቆስ ከቱም ወንገላት አጠር ያለውን ወንጌል የጻፈልን ወንጌላዊ ነው ታሪኩንም ከሐዲስ ኪዳን ሕፍትና ከቤክ ትውፊት እአናገኛለን ይህም አንደሚከተለው ይቀርባል ቤተሰቡ በሐዋ ላይ የቅዱስ ማርቆስ እናት በኢየሩሳሌም የነበሩት ክርስቲያኖች ቤቷን እንዲጸልዩበት ሰጥታ የነበረችው። » የሚላት « ሮምን» እንደሆነ ብዙዎች ሊቃውንት ይናገራሉ ስለዚህ ቅዱስ ማርቆስ በሮም ሳላ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር እንደነበር በጥቅሉ እንረዳለን በተለይም « ልጄ ማርቆስ» የሚለው የጴጥሮስ አጠራር ማርቆስ ከጳውሎስ ጋር ብዙ የሠራ ቢሆንም ከጴጥሮስ ጋር ሳይለይ አብሮ ይኖር የነበረ መሆኑን ያስገነዝባል ያስተማረበት አገር ቅዱስ ማርቆስ ስላስተማረበት አገር የሚከተሉትን ታሪካዊና ትውፊታዊ መረጃዎችን እናገኛለን የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ አውሳብዬስ ዘቂሣርያ ቅዱስ ማርቆስ በሮም ወንጌሉን ከጻፈ በኋላ ወደ እስክንድርያ ሔዶ እንደሰበከ እና የእስክንድርያ የመጀመሪያ ጳጳስ አንደሆነ ጽፏል ገድሉ ሐዋርያትንና ስንክሳር ደግሞ ቅዱስ ማርቆስ ከበርናባስ ዕፅረፍት በኋላ ወደሮም ወደ ጴጥሮስ እንደሔደና በሮም ወንጌሉን ከጻፈ በኋላ ወደ እስክንድርያ ሔዶ አንያኖስ ከተባለ ጫማ ሰፊ ፊሐቂ እና ከቤተሰቡ ጀምሮ ለብዙ ሕዝብ ወንጌልን እንደሰበከ እና ከእስክንድርያም ውጭ በዚያው አካባቢ ባሉ አምስት የአፍሪቃ ሀገሮች እየተዘዋወረ ለ ዓመታት ያህል እንዳስተማረ መዝግበዋል ገድለሐዋስንክሳር ሚያዝያ ዕረፍቱ ወንጌላዊው ማርቆስ ከቱ አገሮች ተመልሶ ወደ እስክንድርያ ከመጣ በጊላ ፋሲካን ትንሣኤ ሲያከብር ሳለ በዚያው ዕለት « ሰራጵዮስ» የተባለውን የጣዖታቸውን በዓል ያከብሩ በነበሩት በግብጽ አረማውያን ተያበዘ በበሬም እየተጐተተ ከተሰቃየ በኋላ በማግስቱ ሚያዝያ ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ አረማውያኑ በድኑን ሊያቃጥሉት ሲሉ በዕለቱ መብረቅና ነፋስ ያለበት በረዶ የተላቀለበት ኃይለኛ ዝናብ ስለዘነበ ባለመቻላቸው ክርስቲያኖች ወስደው ሰቤክ ቀበሩት ይህን ታሪክ ገድለ ሐዋርያትና ስንክሳር እንዲሁም የጥንት ቤተክታሪክ ያስረዳሉ ይህም የሆነው በ ዓም ነው ሁ ምሳሌው የማርቆስ ምሳሌው ገጸ አንበሳ» ነው ማርቆስ በገጸ አንበሳ የተመሰለበት ምክንያት አንበሳ ኑሮው በበረፃ ነው በዚያ ሆኖ ሲጮህ ድምጹ በሩቅ ይሰማል ማርቆስም ወንጌሉን ሲጻፍ «በበረፃ የሚጮህ ሰው ድምጸ» የተባሲ የመጥምቁ የዮሐንስ ሥራና ትምህርት በማስቀደም ስለሚጀምር ነው ማር አንበሳ ለላህም ጌታው ነው ይሰብረዋል ማርቆስም አምልኮተ ላህምን ከምድረ ግብጽ ስላጠፋ ነውየትርዓጓሜ ወንጌል መግቢያ የተጻፈበት ቦታ ቋንቋና ዘመን የማርቆስ ወንጌል የተጻፈበት ቦታ ሮም ሲሆን የተጻፈበትም ቋንቋ ሮማይስጥ ላቲን ነው ዘመኑም በኛ ትውፊት እንደተገለጠው ጌታ ባረገ ኛው ዓመት ተፈጽሞ ኛው ዓመት ሲጀመር ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ ባራተኛው ዓመት ነው ይህም በዓመተ ምሕረት ሲታሰብ ከጌታ ዕርገት ሰፊት ዓመት ከጌታ ዕርገት በኋላ ዓመት ስለዚህ በ ዓም ተጽፏል ማለት ነው የማርቆስ ወንጌል ስተጻፈበት ቦታ ቋንቋና ዘመን ከዚህ ላይ የተገለጠውን የሚያስረዱ ታሪካዊና ትውፊታዊ መረጃዎችን ቀጥሎ እናቀርባን ከቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ የማርቆስ ወንጌል የተጻፈበት ቦታ ጣሊያን እንደሆነ ሲገልጥ አውሳብዮስ ዘቂሣርያ ደግሞ የተጻበት ቋንቋ የጣልያን የላቲን ቋንቋ እንደሆነ በጽሑፎቻቸው አስረድተዋል የትርጓሜ ወንጌል መግቢያ ታሪክ የማርቆስ ወንጌል ስለተጻፈበት አገር ሲናገር ጹ« ማርቆስ በግብጽ በሮምም ይላል» ብሉ ይገልጣሉ ስለተጻፈበት ቋንቋ ልሳን ደግሞ ማርቆስ በሮማይስጥ » ሲል በሮማይስጥ እንደሆነ ይናገራል ስለመዋዕለ ጽሕፈቱ ስለተጻፈበት ዘመን ደግሞ « ማርቆስ ጌታ ካረገ አሥራ አንድ ቢሉ ሲፈጸም አሥራ ሁለት ቢሉ ሲጀመር ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በአራተኛው አመት» ይላል የማርቆስ ወንጌል የትርጓሜው መደምደሚያ መርገፍ ደግሞ ወንጌሉ ስለተጻፈበት ቦታ ቋንቋና ዘመን ሲናገር እንዲህ ይላል « መልዓ ጽሕፈተ ብሥራቱ ለማርቆስ ሐዋርያ አሐዱ እም ሰብአ ወክልኤቱ አርድአት ወኮነ ዘጸሐፎ በሀገረ ሮሜ በልሳነሮም ዘአፍርንጊ አምድኅረ ዕርገቱ ለእግዚእነ ሰዐሥርቱ ወአሐዱ ዓመት ወበራብዕት ዓመት ምንግሥቱ ለቀላውዴዎስ ቄሣር» ይላል ይህም መረጃ የማርቆስ ወንጌል የተጻፈሰት አገር «። ሀገረ ሮሜ ቋንቋው « ልሳ ነሮም» ዘመኑም ከጌታ ዕርገት በላ በኛው ዓመት እንደሆነ ይገልጻል ዘመናውያን የሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት ደግሞ የማርቆስ ወንጌል ከሌሎቹ ወንጌላት ቀደም ብሎ በ ዓም ገደማ እንደተጻፈ ይናገራሉ የተጻፈላቸው ሰዎች ማርቆስ በሮም ውስጥ ሆኖ ወንጌሉን የጻፈላቸው ለራሳቸው ለሮማዉያን ነው ለሮማውያን እንደጻፈ የሚያሳዩ መረጃዎች በወንጌሉ ውስጥ ይገኛሉ እነርሱም አንዳንድ የላቲን ቃላት በውስጡ ይገኛሉ በጽሑፉ ውስጥ ያስገባቸውንም አንዳንድ የአራማይክ ቃላት ይተረጉምላቸዋል ጌታን ሊሰቅሉት በወሰዱት ጊዜ በመንገድ ላይ አግኝተውት መስቀሉን እንዲሸከም ያስገደዱት ስምዖን ቀሬናዊ የአሌክሳንድሮስና የሩፎስ አባት መሆኑን ይገልጣል ከእነዚህ የስምዖን ቀሬናዊ ልጆች አንዱ ሩፎስ ሩፎን የተባለው በሮሜ እንደ ነበር ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ውስጥ ባቀረበለት ሰላምታ ይታወቃል ሮሜ ስለዚህ ማርቆስ« የክሌክሳንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው » አንባቢዎች እንደሚያውቋቸው አድርጉ ሲጽፍ የጻፈው ለሮማዉያን መሆኑን እንገነዘባለን የተጻፈበት ዓላማ የማርቀስ ወንጌሉን ስናጠና ልንረዳ እንደምንችለው ወንጌሉ የሚከተሉት ሁለት ዓላማዎች አሉት ኢየሱስ እርሱ « የሰው ልጅ» « ክርስቶስ» ብቻ ሳይሆን « የእግዚአብሔር ልጅ» «ጌታ» መኾኑን ለሮማውያን ለማስረዳት ነው ይህም ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር « የእግዚአብሔር ልጅ» የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ ብሉ በሰጠው ርእስ ይታወቃል በሌሎችም ክፍሎች የእግዚአብሔር ልጅነቱንና ጌትነቱን በተደጋጋሚ ይገልጣል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማስተማር ዘመኑ ካስተማረው ትምህርት ይልቅ ያደረጋቸውን ታምራት እያብራራ በመግለጥ የጌታን የኃይል ሥራውን ማሳወቅ ነው ዐ ካረገ በኋላም ጌታ ከደቀመዛሙረቱ ጋር በምልክትና በድንቅ በታምራት አብሮ ይሠራ እንደነበር በዚህ ወንጌል ተመዝርቧል የወንጌሉ ጥናት የማርቆስ ወንጌል በይዞታውና በአከፋፈሉ ይጠናል በወንጌሉ ያሉት ምዕራፎች ሲሆኑ ቁጥሮቹ ደግሞ ናቸው ከሓቱም ወንጌላት አጭሩ ይህ ወንንል ነው ይዞታው የማርቆስ ወንጌል ይዞታው በማስተማር ዘመኑ ብቻ የተፈጸሙ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ ትምህርትና ታምራት ነው በዚህ አቀራረቡም ከሌሎቹ ወንገላት ይለያል የማቴዎስና የሉቃስ ወንጌላት የጌታን ነገር ሲጽፉ ከሕፃንነት ታሪኩ ይጀምራሉ የዮሐንስ ወንጌል ደግሞ ከቀዳማዊነቱ ጀምሮ ይጽፋል የማርቆስ ወንጌል ግን የሚጀምረው ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥራ አና ከጌታ ጥምቀት ነው ከዚያም አያይዞ እስከ ዕርገቱ ድረስ ያለውን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ነገር ይዚል የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ በማርቆስ ወንጌል የሚገኙት የጌታ ታሪኮች ብዙዎች ሰማቴዎስና በሉቃስ ወንጌሳት ትይዩ ክፍል አላቸው ነገር ግን ከእነዚሁ ታሪኮች ውስጥ በማርቆስ ወንጌል ብቻ በተለይ የተገለጡትን ቀጥሉ አንመለከታለን በምድረ በዳ ቀን በሰይጣን ሲፈተን ከአራዊት ጋር እንደነበር ተልጧል ታምራት ማድረግ ከጀመረ በላ ወደምድረ በዳ ሊጸልይ ፄዶ ላላ ሕዝቡ ምን ያህል ይፈልጉት እንደነበር ተገልጧል ቀራጩ ሌዊ የእልፍዮስ ልጅ መሆኑ ተገልጧል አሥራ ሁለቱን ጠርቶ ሁለት ሁለቱን እንደላከቸውና አነርሱም ብዙ ድውዮችን ዘይት ቀብተው እንደፈወሱ ተገልጧል በመጥምቁ ዮሐንስ አሟሟት ታሪክ ውስጥ የተብራሩ ነገሮች አሉ በረጅም ተራራ ላይ ክብሩን ሲገልጥ የነበረው የልብሱን ንጣት በተለየ ሁኔታ ተገልጧል የዘብዴዎስ ልጆች በግራውና በቀኙ መቀመጥን የጠየቁት ራሳቸው እንደሆኑ ተገልጧል የሆሳዕና መዝሙር በተለየ አንገላለጥ ቀርቧል ጌታ በተያዘ ጊዜ ነጠላውን ትቶ ራቁቱን ስለሸሽው ጐበዝ ተመዝግቧል በጌታ ላይ ሊመሰክሩበት የቀረቡት የሐሰት ምሥክሮች ምስክርነታቸው አለመስማማት ተገልጧል ጴጥሮስ ጊዜ ጌታን የካደው ዶሮ ጊዜ ሳይጮህ መሆኑ ተገልጧል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተፈረደበት በኋላ የተሰባሰቡበት ቦታ «ፕራይቶሪዮን» እንደሚባል ተገልጦል ሰምዖን ቀሬናዊ የአክሌክሳንድሮስና የሩፎን አባት መሆኑ ተገልጧል ኢየሱስ ከተነሳ በኋላ ቅዱሱን ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ በአጃቸው እአንዳደላከ ተመዝግቧል የጌታ የመጨረሻዎቹ ቃላት የተለዩ ናቸው ወደ ሰማይ ዐርጐ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡና ከዚያ በኋላ ደቀ መዛሙርት በየሥፍራው ሲሰብኩ አብራቸው ይሠራ እንደነበር ተገልጧል ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸው ትምህርቶች ማርቆስ የጌታን ትምህርቶች የማቴዎስንና የሉቃስን ያህል አልመዘገበም የመዘገባቸውም ብዙዎች በማቴዎስና በሉቃስ ወንጌላት ትይዩ ክፍል ያላቸውና ተመሳሳይ ትምህርቶች ናቸው ጥቂቶቹ ግን በተለየ አገላለጥ የቀረቡ አሉ እነዚህን ልዩ አገላለጥ ያላቸውን ትምህርቶች ብቻ አንደሚከተለው እናቀርባለን ሀ በቀጥታ ራሱ ካስተማራቸው ትምህርቶች በማቴዎስና በሉቃስ ወንጌላት ከተመዘገቡት የምሳሌ ትምህርቶች ውስጥ የማይገኝ አንድ ምሳሌ በዚህ ወንጌል ተመዝግቧል ለ ከሚቀርቡለት ጥያቄዎች በመነሳት ካስተማራቸው ትምህርቶች ፈሪሳውያንና ጻፎች የጌታ ደቀ መዛሙርት እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ሲበሉ አይተው ባቀረቡት ጥያቄ ተነስቶ የሰጠው ትምህርት በማቴዎስ ወንጌል ከተመዘገበው ይልቅ በዚህ ወንጌል ተብራርቶ ተገልጧል ሃ ዮሐንስ በሰው አጋንንትን ሲያወጣ ያዩትን ሰው እንደከለከሉት ለጌታ በነገረው ጊዜ ያስተማረው ትምህርት በሉቃስ ወንጌል ከተገለጠው ይልቅ በዚህ ወንጌል በሰፊው ተብራርቶ ተገልጧል ከጸጻፎች አንዱ ፊተኛይቱ ትእዛዝ የትኛይቱ እንደሆነች ጠይቆት ያስተማረው ትምህርት በማቴዎስ ወንጌል ከተመዘገበው ጋር ሲተያይ በዚህ ወንጌል ውስጥ በተለየ አገላለጥ ቀርቧል ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረጋቸው ታምራት የማርቆስ ወንጌል አብዛኛው ክፍል የተያዘው ጌታ ያደረጋቸውን ታምራት በመግለጥ ነው ማርቆስ በአጻጸፉ ከጌታ ታሪክና ትምህርት ይልቅ ባደረጋቸው ታምራት ላይ ያተኩራል የመዘገባቸው ታምራት ምልክቶች አብዛኞች በማቴዎስና በሉቃስ ወንጌላት ውስጥም የተመዘገቡ ናቸው ነገር ግን ከማቴዎስና ከሉቃስ አመዘጋገብ ይልቅ በዚህ በማርቆስ ወንጌል ውስጥ በሰፊው ተብራርቶዋል በዚህ ወንጌል ብቻ የሚገኙም አሉ በማርቆስ ወንጌል ውስጥ ጌታ ብዙ ታምራትን አደረጉ እንደነበር በየሥፍራው ተገልጧል ሙሉ ታሪካቸው የተመዘገበላቸው ግን አሥራ ዘጠኝ ናቸው የወንጌሉ ዋና ይዞታም የጌታን ታምራት በመግለጥ ላይ ያተኮረ ስለሆነ እነዚህን አሥራ ዘጠኝ ታምራት እዚህ ላይ እናጠናለን በቅፍርናሆም ምኩራብ ሲያስተምር የጮኸውን ርኩስ መንፈስ በቃሉ አወጣ በስምዖን በእንድርያስ ቤት ገብቶ የስምዖን አማት እጂን ይዞ ከንዳድ ፈወሳት ለምጻሙን ሰው አጁን ዘርግቶ ሰመዳሰስ ከለምጹ አነጻው ሰቅፍርናሆም በቤት ሆኖ ለብዙ ሕዝብ ቃሉን በመናገር ላይ ሳለ አራት ሰዎች ተሸክመው ያመጡትንና የቤቱን ጣራ ነድለው ያወረዱትን ሽባ በቃሉ ፈወሰው በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ በዚያ የነበረውን እጁ የሰለለችውን ሰው በቃሉ አዳነው በምሽት በታንኳ ሲሄዱ የተነሣውን ማዕበል ነፋሱን ገሥጾ አቆመው በጌርጌሴኖን ለጌዎን የነበሩበትን ሰው አዳነው ከ ዓመት ጀምሮ ደም ይፈሳት የነበረች ሴት ልብሱን ዳሰሳ ከርሱ በወጣ ኃይል ተፈወሰች የምኩራብን አለቃ የኢያኢሮስን ልጅ እቤቱ ድረስ ሄዶ ከሞት አስነሳለት በምድረ በዳ በምሽት እንጀራና ዓሣ አበረክቶ ከሺህ ሕዝብ ሰላይ መግቦ የተረፈው ቅርጫት ተነሣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቤተሳይዳ በታንኳ ሲሄዱ ያስጨነቃቸውን ነፋስ በባሕር ላይ አየሄደ መጥቶ አቆመው በጢሮስና በሲዶና ጋኔን ያደረበትን ያንዲት ሲሮፊንቄያዊት ልጅ አዳነ ሰገሊላ ባሕር ኣካባቢ ደንቆሮና ኮልታፋ የነበረውን ሰው « ኤፍታህ» ብሎ ፈወሰው በምድረ በዳ እንጀራና ጥቂት ዓሣ አበርክቶ ከ ሺህ ሕዝብ በላይ ከመገበ በላ የተረፈው ቅርጫት ተነሣ በቤተሳይዳ ወደ አርሱ ያመጡለትን አንድ ዕውር በዓይኑ ላይ ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት ዓይኑን አበራለት ደቀ መዛሙርቱ ሊያወጡት ያልቻሉትን ዲዳ ደንቆሮም መንፈስ በትእዛዝ አወጣው በኢያርኮ የፅውሩ የበርጤሜዎስን ዓይን አበራለት ከቅጠል በቀር ፍሬ ያላገኘበትን በለስ ሲረግማት ደረቀች በመስቀል ሲሰቀል ከ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከታች ከሁለት ተቀደደ አስተውሉ ከላይ ከተዘረዘሩት የጌታ ታምራት ውስጥ በማርቆስ ወንጌል ብቻ የሚገኙት ታምራት ሁለት ታምራት ናቸው እነርሱም በተራ ቁጥር እና በተራ ቁጥር የተገለጡት ታምራት ናቸው አከፋፈሉ ቱን የማርቆስ ወንጌል ምዕራፋት በ ዐበይት ክፍሎች እንከፍላቸዋለን ጸሐፊው ለወንጌሉ የሰጠው ርእስ ጌታ ወንጌልን ማስተማር ከመጀመሩ በፊት ጥቂት ቀደም ብሎ ያደረጋቸው ነገሮች ው ው ው የመጥምቁ ዮሐንስ ሥራዎች ኢየሱስ ከገሊላና ናዝሬት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጥቶ በክ ብ ቁ በምድረ በዳ ከሰይጣን እየተፈተነ ቀን እንደሰነበተ ጌታ በገሊላና በአካባቢዋ የሰራው ሥራና ያስተማረው ትምህርት ው ው ው ዮሐንስ አልፎ ከተሰጠ በላ ንስሐን እየሰበከ ትምህርቱን መጀመሩ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ ቱን ደቀ መዛሙርት እንደጠራ በቅፍርናሆምና በአካባቢው አያስተማረ ያደረጋቸው ታምራትና የሠራቸው ሌሎች ሥራዎች በባሕር ዳር በታንኳ ተቀምጦ በምሳሌዎች ያስተማረው ትምህርት በገዛ አገሩና በመንደሮቹ እያስተማረ ሲዞር ሐዋርያትን ሥልጣን አቶ ሊሰብኩ እንደላካቸው በምድረ በዳ በገሊላ ባሕር በጌንሳሬጥ በጢሮስና በሲዶና በቤተሳይዳ እያስተማረ ያደረጋቸው ታምራት ከፊልደስ ቄሣርያ ወደ ቅፍርናሆም እየመጣ ያደረገውና ያስተማረው ጌታ ወደ ይሁዳ አገር መጥቶ ያደረገውና ያስተማረው ው ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት ሳይጀምር በሌላው የይሁዳ ክፍል ያደረገውና ያስተማረው ነገር ወደ ኢየሩሳሌም በመውጣት ላይ ሳለ የተደረጉ ነገሮች በቢታንያ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሕዝቡ ሆሳዕና ብሎ እንደተቀበለው ወደ ኢየሩሳሌም ከገባ ጀምሮ እስከተያዘ ድረስ ያደረገውና ያስተማረው የጌታ የስቅለቱ ታሪክ በይሁዳ መሪነት በመጡ ሰዎች እንደተያበክ በሊቀ ካህናቱ ግቢ በአይሁድ ሸንጐ ፊት በሐሰት እንደተመሰከረበት በሏጴላጦስ ፊት እንደተመረመረና እንደተፈረደበት በመስቀል ተሰቅሎ እንደሞተ የአርማትያሱ ዮሴፍ ከመስቀል አውርዶ እንደቀበረው የጌታ የትነሣኤወና የዕርገቱ ታሪክ የተነሳ ዕለት ለተከታዮቹ በየሥፍራው እንደተገለጠ ጌታ ለደቀመዛሙርቱ የተናገራቸው የመጨረሻዎቹ ቃላት የጌታ ዕርገቱ የሉቃስ ወንጌል ጸሐፊው የሦስተኛው ወንጌል ጸሐፊ ቅዱስ ሉቃስ ነው ይህንንም ኤሬኒያስ የተባለው የቤተ ክርስቲያን አባት አስታውቋል ከዚህም ሌላ በጥንታዉያን ጽሑፎች ሁሉ የዚህ ወንጌል ጸሐፊ ሉቃስ መሆኑ ተረጋግጧል በግእዙ ሐኪ ለዚህ ወንጌል የተሰጠው ርእስም ይህን ሲገልጥ «ብሥራተ ሉቃስ ወንገላዊ አሐዱ እምሰብአ ወክልኤቱ አርድእት ማለት ከሰባ ሁለቱ አንዱ የሆነው የወነወጌላዊው ሉቃስ ብሥራት ይላል ስሙ ሉቃስ የሚለው ስም። በማለት ይገልጣል በመልእክታቱ ውስጥ የምናያቸው መረጃዎች ይህንንው በበለጠ የሚያረጋግጡ ናቸው በመልእክታት ከመልእክታት ውስጥ ስለ ሉቃስ የሚያስረዱን ሦስት ጥቅሶች ናቸው እነርሱም በቁላ ላይ « የተወደደው ባለመድኃኒቱ ሉቃስ ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችል » ይላል በፊልሞ ላይ « በክርስቶስ ኢየሱስ ከእኔ ጋር የታሰረ ኤጳፍራ አብረውኝም የሚሠሩ ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዴማስም ሉቃስም ሰላምታ ያቀርቡልሃል» ይላል ማስገንዘቢያ የቄላስያስና የፊልሞና መልእክታት ጳውሎስ በመጀመሪያ የሮም አሥርቱ ጊዜ በሮም ሆኖ የጻፋቸው መልእክታት መሆናቸው ታውቋል ስለዚህ ሉቃስ በዚያ ጊዜ ስማቸው ከተገለጠው ከሌሎቹ የጳውሎስ ደቀመዛሙርት ጋር ሆኖ በሮም ውስጥ የወንጌልን ሥራ አብሮ ይሠራ እንደነበር ከጥቅሶቹ እንገነዘባለን በጢሞ ላይ « ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና ወደ ተሰሎንቄም ሄዲል ቲኪቆስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልንጥያ ፄጻል ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ» ይላል መስገንዘቢያ ኛ የጢሞቴዎስ መልእክት ደግሞ ጳውሉስ ለሁለተኛ ጊዜ በሮም ታሥሮ ሳለ የጻፋት መልእክት ናት ያን ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ የወንጌል ሩጫውን ጨርሶ ዕለተ ሞቱን የሚጠባበቅበት ጊዜ ነበር ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ በየምክንያቱ ወደ ሌሎች ቦታዎች ፄደዋል እሥራቱና መከራው ከመቼውም ይልቅ በጸናበት በዚያ ጊዜ ከእርሱ ጋር የነበረው ሉቃስ ብቻ ነበር ስለዚህም ሉቃስ ለቅዱስ ጳውሎስ የነበረው ቀረቤታ ምን ያህል እንደነበረና እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ከእርሱ ሳይለይ ያገለገለው ታማኝ ደቀ መዝሙሩ እንደነበር ከጥቅሱ እንገነዘባለን ያስተማረበት ሀገር ሉቃስ ስላስተማረበት ሀገር የምንረዳው ከትውፊታውያን መጻሕፍት በምናገኘው ታሪክ ነው እነዚህም ታሪኮች ሉቃስ ጳውሎስን ከመከተሉ በፊትና ከጳውሎስ ዕረፍት በላ በየትኞቹ አገሮች እንዳስተማረ ይነግሩናል በሉቃስ ወንጌል ትርጓሜ መግቢያ ላይ ሐዋርያት ዓለምን ዕጣ በዕጣ ብለው ተካፍለው ለማስተማር በሚወጡበት ጊዜ ሉቃስ ዮሐንስን ተከትሎ በመሔድ ዮሐንስ በዕጣ ከደረሰችው ከምድረ ጽርአ ከፍሎ በሰጠው በመቄዶንያ ገብቶ ስለ ክርስቶስ እንዳስተማረ ይናገራል ይህም ቅጳውሎስን ከመከተሉ በፊት መሆኑ ነው ገድለ ሐዋርያት ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት ከሞተ በኋላ ሉቃስ ከሞት ተርፎ በሮሜ ዳርቻ ባሉ አገሮች ያስተምር እንደነበር ሲገልጥ « ወኔሮንኒ ንጉሥ ዘይሰመይ ቄሣር አኃዞ ለጳውሎስ ወመተሮ ርእሶ ሀገረ ሮምያ ወሉቃስ ቅዱስ ተርፈ እምገጸ ንጉሥ ወተሰወረ ወኮነ ይሰብክ ውስተ ኩሎ በሐውርተ አህጉር ዘውስተ ይእቲ አጽናፍ» ይላል ስንክሳር ደግሞ በበኩሉ« ወይሰብክ ሉቃስ በሀገረ ሮሜ» ይላል ስለዚህ ቅዱስ ሉቃስ በፊት በመቄዶንያ በኋላም በሮምና በዳርቻዎቿ እየተዘዋወረ የክርስቶስን ወንጌል አስተምሮ እንደነበር እንገነዘባለን ዕረፍቱ ኔሮን ቄሣር ባስነሳው ስደትና መከራ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በሞቱ ጊዜ የብዙ ክርስቲያኖች እልቂት ተፈጽሞ ነበር ሉቃስ ግን ከኔሮን ቄሣር ተሰውሮ ወንጌልን በመስበክ ላይ ነበር በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተለያየ ታምራት እያደረገ ብዙ ሕዝብ ሲያሳምን ያዩ ካህናተ ጣዖት ወደ ኔሮን ቄሣር ሄደው « በሥራዩ ብዙ ሕዝብ እያሳሳተ ነው» ብለው ከሰሱት ከዚያም ተይዞ በኔሮን ቄሣር ፊት ቀረበ ንጉሥ ኔሮንም « እስከ መቼ አንተ ሰዎችን በሥራህ ታስታለህ» ባለው ጊዜ «አኔ መሠርይ አይደለሁም የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ መልክተኛ ነኝ እንጂ» ብሎ መለሰለት በዚህን ጊዜ ኔሮን ተቆጥቶ እጁን አእንዲቆርጡት አዘዘና መጻሕፍት የሚጽፍባትን ቀኝ አጁን አስቆረጠው ሉቃስ ግን ጸሎት አደረገና የተቄረጠችውን እጁን ቀጥሎ የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይል አሳየው የጭፍሮቹን አለቃ ጨምሮ ነፍሳት ይህን አይተው በክርስቶስ አመኑ በዚህ ጊዜ ኔሮን በጣም ተቆጣና አነዚህ ሰዎችና ቅዱስ ሉቃስን በሰይፍ እስከገደላቸው ሉቃስን በሰይፍ ሊገድሉ ከመጡት ጭፍሮች አንዱ አንድ ዓይኑ ታውሮ ነበር ገና ወደ ሉቃስ ሲቀርብ የታወረ ዓይነ በራለት። በዚህ ተገርሞ በእግሩ ሥር ወድቆ ሉቃስን ይቅርታ ጠየቀውና ንስሐ ገባ ሌላው ጭፍራ ግን ይህን ያመነውን ሰው እና ሉቃስን በሰይፍ መትቶ ገደላቸው በዚህ ዓይነት ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ በድኑንም ወደ ባሕር ጣሉት ነገር ግን እግዚአብሔር ሞገድን አስነስቶ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው አንድ አማኝም አግኝቶ ገነዘውና ቀበረው በማለት ገድለ ሐዋርያት እና ስንክሳር ይተርካሉ ስንክ ጥቅ ሉቃስ የሞተው በ ዓመቱ ሲሆን እስከ ዓመቱ ድረስ ግን ሚስት ያላገባ ሰው እንደነበር ጥንታዊያን መረጃዎች ይገልጣሉ ምሳሌው ሁ ሉቃስ በገጸ ላሕም ይመሰላል የዚህም ምክንያቱ « አምጽኡ መግዝአ ላህም ወጥብለሑ ንብላዕ ወንትፌሳሕ ምስሌሁ» ብሉ ለክርስቶስ ምሳሌ የሚሆን የላህም የፊሪዳ ምሳሌ« ስለየጻፈ ነው ሉቃ የትርጓሜ ወንጌል የታሪክ ዓምድ አንዲሁም የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች ጸሐፍት የቱን ወንጌላት ምሳሌ ሀከ ሸቨጠጩ ሲገልጡ ሉቃስ በገጸ ላህም የተመሰለው በዚህም ምክንያት እንደሆነ አስረድተዋል የተጻፈበት ቦታ ቋንቋና ዘመን የሉቃስ ወንጌል ስለተጻፈበት ቦታና ዘመን የተለያየ አመለካከት አለ ይኸውም ዘመናውያን የሆኑ ሊቃውንት የሉቃስ ወንጌል ከሐዋርያት ሥራ አስቀድሞ የተጻፈ መሆኑ በሐሥ ስለተገለጠ ሐዋርያት ሥራ የተጻፈው ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ በሮም ለሁለት ዓመት ታሥሮ ከነበረበት ጊዜ ዓም በኋላ ወዲያውኑ መሆኑን ስለምንረዳ ወንጌሉ የተጻፈው ከዚህ ቀደም ብሎ ቅዱስ ውሎስ በቂሣርያ ታስሮ ሳለ በ ዓም ገደማ እንደሆነ ያስገነዝባሉ የጻፈውም በግሪክኛ ቋንቋ መሆኑን ያስረዳሉ መቅድመ ወንጌልና የትርጓሜ ወንጌል የታሪክ ዓምድ ደግሞ ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈበት አገር መቄዶንያ የጻፈበት ቋንቋ ልሳን ዮናኒ የተጻፈበት ዘመን ደግሞ ጌታ ካረገ ፃያ አንድ ዓመት ተፈጽሞ ፃዛያ ሁለተኛው ሲጀመር ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በአሥራ አራተኛው ዘመን እንደሆነ ይገልጣሉ ዘመኑን ወደ ዓመተ ምሕረት ስንለውጠውከጌታ ዕርገት በፊት ዓመት ከጌታ ዕርገት በላ ዓመት ድምር ዓም ይሆናል ስለተጻፈበት ቦታ ቋንቋና ዘመን ይህን ሁሉ አጠቃሎ የሚናገረው በሉቃስ ወንጌል ትርጓሜ መደምደሚያ ላይ የሚገኘው ቃል ነው እርሱም በግእዝ እንዲህ ይላል « መልዓ ጽሕፈተ ብሥራቱ ለሉቃስ ወንጌላዊ አሐዱ እምሰብአ ወክልኤቱ አርድእት ዘጸሐፎ በልሳነ ዮናኒ ለሰብአ ሀገረ መቄዶንያ እምድኅረ ዕርገቱ ለእግዚእነ ውስተ ሰማይ በአሥራ ወአሐዱ ዓመት ወበዐሠርቱ ወዐርባዕቱ ዓመተ መንግሥቱ ለአቅሌንድዮን ለቀላውዴዎስ ቄሣር» ከእነዚህ መረጃዎች እንደተመለከትነው የተጻፈበትን ቦታና ዘመን በተመለከተ በኛ ትውፊት የተገለጠውና በሌሎች ሊቃውንት የተነገረው አመለካከት የተለያየ ቢሆንም የተጻፈበትን ቋንቋ በተመለከተ ያለው አመለካከት ግን ተመሳሳይ ነው ምክንያቱም በኛ ትውፊት « ዩናኒ» የተባለው ቋንቋ « ኪኒ» የተባለው የግሪክኛ የጽርእ ዲያሌክት ስለሆነ ነው የተጻፈለት ሰው የሉቃስ ወንጌል የተጻፈለት ሰው «ቴዎፍሎስ» የተባለ በሮም ግዛት ሥር ያለ አንድ ባለሥልጣን ነበር ይህም በወንጌሉ መግቢያ ላይ ተገልጧል ቴዎፍሎስ ማለት መፍቀሬ እግዚአብሔር ማለት ነው ሉቃስ በስብከቱ አስተምሮ ያሳመነው ባለሥልጣን አንደኾነ በወንጌሉ መጀመሪያ ላይ ካሉት የመግቢያ ቃላት እንገነዘባለን አንዳንዶች ግን « ቴዎፍሎስ» የሚለው ይህ ስም የሚያመለከተው አንድን የታወቀ ሰውን ሳይሆን መጽሐፉን እንዲያነቡ የተጻፈላቸውን የአግዚአብሔር ወዳጆች ሁሉ ነው በማለት ይናገራሉፎ ነገር ግን አንድ የታወቀ ሰው መሆኑን የሚከተሉት ማስረጃዎች ይገልጣሉ « ቴዎፍሎስ » የሚለው ስም በዚያ ዘመን በግሪኮችና በአይሁዳውያን ዘንድ የግለሰቦች መጠሪያ ስም የተጸውኦ ስም ሆኖ የተለመደ ስም ነበር ስለዚህ ። ስለተማርከው ቃል አርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ » ይላል ስለዚህ የወንጌሉ ዓላማ ቴዎፍሎስ በቃል የተማረውን የክርስቶስን ነገር እርግጡን በጥልቀትበሚገባ እንዲያውቅ ለማድረግ ነው ዛሬም መጽሐፉን የሚያነቡ ሁሉ ስለክርስቶስ ታሪክና ሥራ በስፋትና በጥልቀት እንዲያውቁ ያደርጋል ከዚህ በመነሳት ሉቃስ ከጽንሰቱ እስከ እርገቱ የመዘገበው የጌታ ታሪክ ሲጠና ያተኮረባቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው ከድንግል ማርያም የተወለደው የሰው ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑና ጌታ መሆኑን የተለያዩ ማስረጃዎችን ምስክሮችን በማቅረብ ለቴዎፍሎስ ያስረዳል ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሲሆን በድህነት እንደተገለጠ በማስተማር ዘመኑም ድሆችን ይጉበኝና ይቀበል አንደነበር በመግለጥ ቴዎፍሎስም ክብሩን ለጌታ ሰመተው ከበታቹ ያሉትን ድሆችንና ግፉዐን ሰዎች እንዲቀበል ያስተምረዋል ስለ መዝሙርና ስለጸሎት የተለያዩ ማስረጃዎች በማቅረብ የስተምረዋል የወንጌሉ ጥናት ይዞታው አንደሌሎቹ ወንጌላት ሁሉ የሱቃስ ወንጌል ይዞታው የንታ የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክታምራትና ትምህርት መግለጥ ነው በዚህ ክፍል የምናጠናው በሉቃስ ወንጌል ብቻ የተመዘገቡትን ይሆናል የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ በሉቃስ ወንጌል ብቻ የተመዘገቡት የጌታ ታሪኮች ናቸው እነርሱምፁ መጥምቁ ዮሐንስ በተፀነሠ በኛው ወር ጌታ እንደተፀነሰ የመጥምቁ ዮሐንስ ልደትና እድገት ጌታ በበረት ሲወለድ እረኞች ስለ አርሱ የሰሙትንና ያዩትን እንደመሰከሩ በተወለደ በኛው ቀን ሲገረዝ ስሙ ኢየሱስ እንደተባለ በዐ ቀን ወደ ቤተ መቅደስ እንደተወሰደና ስምዖንና ሐና እንደመሰከሩለት በ ዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም እንደሄደሪ ከዮሴፍ እስከ ኣዳም ወደላ የተቆጠረ የጌታ ሐረገትውልድ ስምዖን ጴጥሮስና የዘብዴዎስ ልጆች መጠራት ጌታ በፈሪሳዊው ቤት ከማዕድ ተቀምጦ ሳለ ወደ አርሱ የመጣቸውን ኃጢአተኛ ኃጢአቷን እንዳስተስረየላት በገንዘባቸው ያገለግሉት የነበሩት ሴቶች ሰባ አርድእትን ሾሞ ሁለት ሁለት አድርጐ እንደላካቸው ማርታ ሰቤትዋ አንደተቀበለችው በኢያሪኮ በዘኬዎስ ቤት እንደዋለ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዞ ሊደርስ ሲቀርብ ከተማይቱን አይቶ እንዳለቀሰላት በተያዘ ጊዜ በገሊላው ገዥ በሄሮድስ ፊት እንደተጠየቀ ሊሰቅሉት ሲወስዱት ሙሾ የሚያወጡ ሴቶችና ብዙ ሕዝብ እንደተከተሉት ነ ጃጀበትንሳኤው ወደ ኤማሁስ ይሄዱ ለነበሩት ሁለት ደቀመዛሙርት ተገልጦ ብዙ እንዳነጋገራቸው ለዱና አብረዋቸው ለነበሩት ሲገለጥ መንፈስ እንደመሰላቸውና እንዴት እንዳሳመናቸው ከላይ ኃይልን እስኪለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ እንዳዘዛቸው ወደ ሰማይ ሲያርግ እየባረካቸው እንዳረገና እነርሱም ተመልሰው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ እንደኖሩ የኢየሱስ ክርስቶስ ታምራት በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ጌታ ብዙ ታምራትን አድርጐ አንደነበር በየሥፍራው ተመዝግቧል ነገር ግን በዚህ ወንጌል ሙሉ ታሪካቸው የተመዘገበላቸው ታምራት ናቸው ከእነዚህም ውስጥ በሉቃስ ወንጌል ብቻ የሚገኙት ናቸው እነርሱም ናይን በሚባል ከተማ የአንዲት መበለትን ልጅ ከሞት እንደ አስነሳ በሰንበት በአንድ ምኩራብ ሲያስተምር የ ዓመት ጉባጣ አቀና ዐ በሰንበት ቀን ከፈሪሳውያን አለቆች በአንዱ ቤት የተደረገውን ፈውስ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ባንዲት መንደር ለምጻሞችን አነጻ ሌሎቹን ታምራት በማርቆስ ወንጌል ጥናት ተመልከት የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ከሲኖፕቴክ ወንጌላት ውስጥ የሉቃስ ወንጌል እንደማቴዎስ ወንጌል ሁሉ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች በስፋት መዝግቦ የሚገኝ ወንጌል ነው ጌታ በቀጥታ ካስተማራቸውና በጥያቄዎች መነሻነት ካስተማራቸው ትምህርቶች ውስጥ ብዙ ትምህርቶች በሉቃስ ወንጌል ይገኛሉ ከእነዚህም ውስጥ በሉቃስ ወንጌል ብቻ የሚገኙት ናቸው።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Advertisement
Bottom banner

Download options | Convert to Pdf | Reading List | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact