Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
እየሱስ አዳኝ ነው። መግቢያ ቁርስ በስጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ በኩል እጅግ አስፈላጊ ነው። ኢሳ ሽ ብ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛው ቦታ መሄድ ትክክለኛውንም ጉዳይ መፈጸም መልካም ነው። በላዩም ላይ የወረደው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። እንደ ኤርምያስ ሕዝቅኤልም ካህንም ነቢይም ነበር። እኔም የእስራኤል አምላክ ክብር ከምስራቅ ሲመጣ አየሁ ድምጹም እንደ ባሕር ሞገድ ድምጽ ነበር ምድሪቱም ከክብሩ የተነሳ ታበራ ነበር። ዳንኤል ከይሁዳ አገር ተማርኮ ወደ ባቢሎን የተወሰደ ጎልማሳ ነበር። ሆሴዕ ብሩክ የአምላክ ነቢይ ነበር ባለቤቱ ግን ምሳሌም ይሁን እውነት ለብልግና ራሷን አሳልፋ የሰጠች ወራዳ ሴት ነበረች «ከመልካም ሽኮ መልካም ስም ይበልጣል» እንደሚባለው ሕይወቷ በምግባረ ሰናይ የተሞላ ስለነበረ ሁሉም አልቀው ይመለከቷት ነበር። ማመን ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥለውም የሚጠቅም መሆኑን ለማስረዳት ይህንን ግሩምና ድንቅ የሆነ ምክር ሰጣቸው ወንድሞቼ ሆይ የምንለያየበት ጊዜ ደረሰ ፊታችሁን እንደገና ማየት እችል እንደሆነ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ጭራሽ እሱ ካስተማረው ንቅንቅ ከማለት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉሌ ይህ የሚያሳዝን ሁኔታ ነው። እነ ሉተርና እነ ካልቪን አሁን ቢኖሩ ኖሮ ከዚህ ቀደም ብርሃን እንደተቀበሉ አሁንም ደግሞ ተጨማሪ ብርሃን ይቀበሉ ነበር ምሳሌ ቫ እንዲህ ይላል የጻድቃን ብርሃን እንደ ንጋት ብርሃነን ነው ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ ይበራል ክርስቶስ ጌታም ብዜ ነገር አለኝ የምነግራችሁ ዛሬ ግን አትችሉም ትሸከሙት ዘንድ ያም የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። ብሏል ዮሐ ዛ ሕይወት ራሱን የቻለ ትቤት ነው። እግዜርን በማይፈሩ ልጃገረዶች ተደፈሩ ለስልጣን የሚጋፉ ክብራቸውንም ተገፈፉ ጌታ አምላክን ስለረሱ ቅዳሜ ሰንበትን ስላረከሱ ሕጉንም ስለጣሱ ሊገለፅ የማይቻል ሊወራ መጣባቸው ታላቅ መከራ ኢየሩሳሌም ውበትን አጥታ በሰይፍ በስደት ተቀጥታ ሆነች እንደ ባልቴት መብትና ክብር የሌላት ሕዝቦች ተሰደው አለቁ ጠላቶች ፈነደቁ በከተማዋ ላይ ሳቄ። መልካሙ የጽዮን ሜዳ ሆኖ ቀረ ምድረ በዳ ዓመጽና ክፋት ትዕቢትና ኃጢአት ለየሩሳሌምም አልበጃት ተመርዛ ከዳር እስከመሃል ተፈርዶባት በአምላክ ቃል ወረደች ወደ ሲኦል። አንድ ለእናቷ ማንም ሳይነግረኝ እኔ እራሴው ደርሼበታለሁ ያውም እናቴ ወሮ የሺእመቤት ወኪዳን ለልጂ ልጅ ለዶር ያሬድ ጥላሁን ልዩ ፍቅር እንደነበራት ነበር። ከዚህ የተነሳ በበለጠ እናቴን እንዳመሰግን አደረገኝ ለእኔም ለምትወደው ልጂ እንደ ጸለየች ስገነዘብ ልዩ የደስታ ስሜት ተሰማኝጓ ልናደርግ የሚገባ ነገር ካለ ለሌሎች መጸለይ ነው። የኔ አስቴር የኔ ፍቅር ይሀ ቀን እንዲከበር እንኳን አደረስሽ እግዚአብሔር። ከላይ የተጻፈው ከሁለት ዓመታት በፊት የጤንነት እክል ገጥሞን በነበረ ወቅት ነው። ለእኔም ያዘዘልኝ ስለ እኔ ግድ የሚላቸው ብዙ ስዎች በሕይወቱ ትልልቅ ሚና የተጫወቱ ስላሉና ስለነበሩ አምላኬን ሺ ጊዜ አመሰግነዋለሁ። ገና በሕጻንነቴ ከእናቴ ሌላ እናት እትዬ ዐጸደ ደስታ የምትባል ነበረች አይታኝም አትጠግብም ነበር። እንዲሁም ካደግሁም በኋላ በሄድኩበት ቦታና በቆምኩብት ስፍራ የሚጠነቀቅልኝ ሰው አላጣም። ሆሳዕና መንገድ ላይ ከትልቅ መኪና ላይ ሶስት ሆነን በተገለበጥንበት ጊዜ ያዩ ሰዎች ምንም የምንተርፍ አልመሰላቸውም ነበር። መጽሐፉን ከዳር እስከ ዳር ያነበበውና ያረመው ኤርምያስ አሞሳ ነው። ሌላው አዲሱ አማረ ሊበን ነው። በችግር ጊዜ ወንድም ይወለዳል የሚባለውን አነጋገር ሕይወቴን በሙሉ ያየሁት ሕጠቅ ነው።
ሶስት ጊዜ ደግሞ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱስ ሁነ የሚል አለበት ዕብራውያን ያለ ቅድስና ማንም የእግዚአብሔርን ፊት ለማየት አይችልም» ይላል። ሁለት ጊዜ አምላክ ተስፋውን እንደጠበቀ ከተናገረው እንኳን ከምድር አንድም እንኳን ጠብ አላለም ብሎ ይነግረናል። ሁለተኛ ሳሙዔል ከዚህ ቀደም በስውር ነቢዩ ሳሙዔል ለንጉስነት የቀባውና ጎልያድንም በሰራዊት ጌታ ስም ያሸነፈኖ የገደለው ዳዊት በዚሀ መጽሐፍ በመጆመሪያ የይሁዳ ቀጥሎም የእስራኤል ንጉስ እንዲሆን በደስታና በእልልታ እንደ ተቀባ እናነባለን ምንም እንኳን ንጉስ ሳፆል እንደ አውሬ ሲያሳድደውና ሲያስቃየው ቢቆይም እንኳን ዳዊት ሳኦል ሲሞት ለእሱና ለዮናታን ሳኦልና ዮናታን በሕይወት እያሉ የሚዋደዱ የሚሰማሙ ነበሩ ሲሞቱም አልተለያዩም እያለ እንዳለቀሰላቸው ተመዝግቧል ዳዊት መንግስቱ በጸናለትና ሁሉ ነብ በተሳካለት ጊዜ የእግዚአብሔርን ውለታ እያሰላሰለ እነሆ እኔ ከዝግባ በተሰራ ቤተ መንግስት ውስጥ እኖራለሁ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ይኖራል እያለ ማሰብ ጆመረ ለእሱም ክብር የሚሆን ቤተመቅደስ ለመንገባት ቆርጦ ከልቡ ተነላ ይህንን የዳዊትን ቅን አሳብ አለመጠን እወደዋለሁ እግዚአብሔር ግን የተለየ አሳብ ነበረው አንተ ሳትሆን ከአንተ አብራክ የሚገኘው ልጅህ እሱ ነው የሚሰራልኝ አለው ይህንንም መለኮታዊ አስተያየት ዳዊት በምስጋና ነበር የተቀበለው እንዲህ እያለ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ። በኋላ በቀርሜሎስ ተራራ በእውነት እግዚአብሔር አምላክ እንደሆነ በገሃድ ታወቀ ሕዝቡም አምላክ እግዚኣብሔር እሱ እውነተኛ ነው እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ነው አሌ ሁለተኛ ነገስት በብሉይ ኪዳን ዘመን ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው በሀይወት እያሉ ወደ ስማይ ያረጉት የመጀመሪያው ሄኖክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኤልያስ ነበር። በዚህ በበደላቸው የተነሳ ታላቅ መከራ እንደሚመጣባቸው ነቢዩ ወዮ ለዚያ ቀን የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና ሁሉን ከሚችል አምላክ እንደ ጥፋት ይመጣል። ትንቢተ አሞጽ ምንም እንኳን በቁጣ ቢጀምር መደምደሚያው ብሩህ ከሆነ ተስፋ የተሞላ ነው እግዚአብሔር አምላክ ዓመጸኛውን ከመቅጣት ይልቅ የሚደሰተው ይቅር በማለትና በተድሏ ወደተሞላ ሕይወት ዘማምጣት ነው አምላክ የሚሰጣቸው ተስፋዎች ሁሉ አንደኛ እውነት ናኾው ሁለተኛ እሱ በፈለገበት መንገድና ጊዜ ይፈጸማሉ ተመልከቱ የመጨረሻው ምዕራፍ የሚለውን የወደቀውን የዳዊትን ድንኳን አነሳለሁ የተሰበረውን እጠግናለሁ ቀድሞ እንደነበረው አድርጌ እሰራዋለሁ። ኃጥአን በመጨረሻ ድምጥማጣቸው እንደሚጠፋ የኤሳውም ዘሮች ፅጣ ፋንታቸው ተመሳሳይ ነበር ቫ የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናል ከኤሳው ቤት የሚተርፍ አይኖርም እግዚአብሔር ተናግሯልና ዮናስ ነነዌ ወደሚባል ከተማ ከባድ የማስጠንቀቂያ መልእክት ይዞ እንዲሄድ ነቢዩ ዮናስ ታዘክ የመለኮት አስተሳሰብ ከእሱ አሳብ ጋር ስላልተስማማ የራሱን አቅጣጫ ቀየሰ ማዕበሉ መርክቧን ሲያንገላታት ተሳፋሪዎቹ ሁሉ ወደ አምላኮቻቸው ሲጮሁ ዮናስ ምቹ ቦታ መርጦ ዓለም ደህና ሰንብች» ብሎ እንቅልፉን ይለጥጥ ነበር ከእንቅልፉ ከቀሰቀሱት በኋላ ይህ ሁሉ የመጣው በእሱ ምክንያት ስለነበረ በራሱ ላይ ትልቅ ፍርድ ፈረደ ይህ ታላቅ ማዕበል በኔ ምክንያት እንደመጣባችሁ አውቃለሁ አንስታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ ባሕሩም ጸጥ ይላል አለ ቫ ተጥሎም በዓሳው ውስጥ እያለ ጸለየ ጸሎቱም ተሰማ ፍሴ በዛለች ጊዜ እግዚአብሔር ሆይ አንተን አሰብሁ ጸሎቴም ወዳንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደረሰች ከዓሳው ከተተፋ በኋላ አስቀድሞ የተሰጠውን መልእክት ለማሰማት በሄደበት ጊዜ ሕዝቡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ንጉሱም ሳይቀር ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው በጸሎትና በጾም ንሰሐ ገቡ ይህንንም አይቶ ቸሩ አምላክ ፊቱን ወደ እነሱ መለሰ። እግዚአብሔር የምሕረት አምላክ ነው ይህንን ሺ ጊዜ ብናገረው ደስ ይለኛል። እውነተኛውም ንጉስ እንደመጣ ለማሳመን አምሳ አምስት ጊዜ የእግዚአብሔር መንግስት ስላሳ ሁለት ጊዜ መንግስተ ሰማያት የሚለውን ቃል ይጠቀምበታል። ሉቃስ በተለይ የሚያተኩረው በክርስቶስ ሰብዓዊነት ላይ ነው ጌታችን ስማንያ ጊዜ ያህል የሰው ልጅ» ተብሎ ተጠርቷል ራሱንም በዚህ ቅጽል ብዜ ጊዜ ጠርቷል ትውልዱንም ሲዘረዝር ሉቃስ ጌታን ከመጀመሪያው ሰው ጋር ለማያያዝ የአዳም ልጅ የአግዚአብሔር ልጅ ይለዋል። ይህ ወንጌል የተጻፈበት ዋናው ዓላማ ክርስቶስ ልዑል አምላክ መሆኑን ለማሳየት እንደሆነ ገና ከመግቢያው ላይ ይታወቃል በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ እርሱም ከመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ። በዚህ መጽሐፍ መደምደሚያ ላይ አሜን የሚል ቃል አይገኝም ምክንያቱም ስራው ተጆመረ እንጅ አላበቃም የመንፈስ ቅዱስ ስራ አሁንም እየተካሄደ ነው ክርሰቶስ በክብር እሰከሚመለስበትም ጊዜ ይቀጥላል። ሐዋርያት ስራ የመንፈስ ቅዱስ ስራ» ትብሎ መጠራት አለበት ከጴጥሮስና ከጳውሎስ በስተቀር ስለሌሎቹ ግን ምንም ያሀል ከውስጡ አናገኝም መንፈስ ቅዱስ ግን ከስድሳ ጊዜ በላይ ተጠቅሷል። ጴጥሮስም ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁ እንዲሰረይላችሁ እያንዳንዳችሁ በየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ አላቸው የዚያ ለታ አምነው የተጠመቁ ቁጥራቸው ሶስት ሺ ያህል ነበር በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጆመረው እንቅስቃሴ ከኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ ከዚያም አልፎ ተርፎ ወደ ስማርያ ወደ ሮምም ተዳረስ የዚያን ጊዜ በረከቱን ከተቀበሉት አንዱ የአገራችን ተወላጅ ነበር ሰረገላው እንዲቆም አዘዘ ከዚያ ሁለቱ አብረው ወደ ውኃው ወረዱ ፊሊኦስም ጃንደረባውን አጠመቀው በዓለም ላይ ጌታ የጀመረውን ስራ ተረክቦ የሚያካሂድ መንፈስ ቅዱስ ነው ምንም ኃይል ሊቋቋመው አይችልም የጀመረውን በዓለም ሁሉ ይፈጽማል ሮሜ ጌታ ፍርዱን በምድር ላይ በፍጥነትና ለመጨረሻ ጊዜ ይፈጽማል። ተቃዋሚዎቹ «ሐዋርያ አይደለም» ብለው ሰለሚያሾፉበት ስለ ራሱ እንዲናገር ተፈተነ ከነገረን አንዱ ከሁሉም ብልጫ ያለው አምላክ ስለስጠው የላቀ ክብር ነበር ከአስራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሶስተኛው ሰማይ ድረስ የተጠነቀ በክርስቶስ አንድ ሰው አውቃለሁ የተነጠቀው በስጋ ይሁን ወይም ከስጋ ውጭ እኔ አላውቅም እግዚአብሔር ግን ያውቃል። አካላችን ምንም እንኳን በዚህ ምድር ቢሆንም እምነታችን መንጥቆ ወደ ሰማየ ሰማያት መሄድ አለበት እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሳችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉትን እሹ አሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊው ላይ አይሁን ካ ክርስቶስም ከላይ ነው የሚመጣው እሱ ሲመለስ ሕልማችን ሁሉ እውን ይሆናል ተስፋችን ወደ ማግኘት እምነታችን ወደ ማየት ይለወጣል በውርደትም ፈንታ ክብርን እንጎናጸፋለን ሕይወታችሁ የሆነው ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም በዚያን ጊዜ ከእርሱ ጋር በክብር ትካለጣላችሁ። ፅብራውያን ይሀ መልእክት እጅግ ታላቅና ጥልቅ በሆነ ግርማና ሞግስ ባለው ቃል ይጀምራል ዛ እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በተለያየ ጊዜና በልዩ ልዩ መንገድ በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ በዚህ በመጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በእርሱ በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ ከመጣ ጀምሮ ያለውን ገዜ የመጨረሻ ዘመን» ብሎ ይጠራዋል ዘመኑም ታይቶና ተሰምቶ ያልታየ ክብርና ፅድል ለሰብዓዊ ፍጥረት የተገለጠበት ዘመን ነው ክርስቶስ ልጅ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ምሳሌ» ተብሏል ዓለምን ደግፎ የያዘ እሱ ነው የኃጢአትን መንጻት ካስገኘኛ በኋላ በሰማይ በግርማው ቀኝ ተቀመጠ ከመጋረጃው በስተጀርባ ወዳለው ውስጠኛ መቅደስ ይገባል ይህም ስፍራ የሱስ ስለእኛ ቀድሞ የገባበት ነው ቫ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ እንዲሀ ያለ ሊቀ ካህናት አለን ቫ የመጀመሪያ ወላጆቻችን ከበደሉ በኋላ ክኤደን ገነት ተወገዱ ተመልሰውም እንዳይገቡ ኪሩቤል በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ ይዘው ቆመው ነበር በብሉይ ኪዳን «ራቁ አትቅረቡ» የሚል ጥብቅ ትእዛዝ እናገኛለን በክርስቶስ መስቀል የተነሳ ምሕረት ስለ ወረደ «ቅረቡ ግቡ» እየተባልን ተጋብዘናል እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ በየሱስ ደም ለመግባት ድፍረት አግኝተናል። ዓካ ዕብራውያን በተጨማሪ የሱስ ክርስቶስ ከሁሉ በላይ የላቀ ከነቢያት ከመላእክኮት ከሙሴ ከኢያሱ ክአሮን በላይ እንደሆነ ይነግረናል የተሻለ» የሚለው ቃል አስራ ሶስት ጊዜ ያሀል ተጠቅሶ ይገኛል ክርስቶስን በማመን ምንም የከሰርነው የለም ጭራሽም በልጽገናል። ሠሀጓ ምሕረትንና ፅርቅን በሚናገር ደም ላይ ደህንነታችን ተመስርቷል ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ ሀን ያፅቆብ በአምነት በጸጋ ድናችኋልና ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ በስራ አይደለም ምክንያቱም እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ስራ እንድንሰራ በክርስቶስ የሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር ስራዎች ነን። ዛ መልእክቱ ስለ እግዚአብሔር ሁለት ነገሮችን ይገልጻል እርሱ ብርሃንና ፍቅር መሆኑን እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእሱ ከቶ የለም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል። ፍቅር የሚለው ቃል አምስት ጊዜ ተጠቅሷል። በአርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ አንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ዮሐ ባ ክርስቶስም እራሱ ይህንን ጉዳይ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋልና በማለት በማያወላውል ቋንቋ አስተምሯል ዮሐ ይህንን በፍጹም እንዳንጠራጠር ዮሐንስም ከአንዴም ሁለቱ ደጋግሞ ይህንን እውነት ያስተጋባል የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ እንዲሁም ነን ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም ወዳጆች ሆይ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ እርስ በርሳችን እንዋደድ። እኛም መጽሐፍ ቅዱስንም ከዳር እሰከ ዳር አንብበን የሱስ ክርስቶስን ካላየንና ካላመንን ያንን የተቀደሰ መጽሐፍ አንብበነዋል ወይም አውቀናውል ለማለት አንችልም እንደ የሱስ ስም አይገኝም ይህ የተወደደ ስም ለመላእክት ደስታ ነው ለክርስቲያንም ተድላ ነው በመጽሕፍ ቅዱስ ውስጥ ከብሮ የሚገኝ እሱ ነው የተጻፈበትም ከእሱ ሊያስተዋውቀን ነው ገር ግን ኢየሱስ አርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምነ ዘንድ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችሏልና እነርሱን ትመረምራላችሁ እነርሱም ስለ እኒ የሚመሰክሩ ናቸው ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር እርሱ ስለ እፄ ጽፎአልና በዚያን ጊዜ አልሁ እነሆ መጣሁ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል ዮሐ መዝ ጴዐ ለመሆኑ እንደዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ገንኖ የሚገኘው የሱስ ክርስቶስ ማነው። ክርስቶስ ወደ ሰማይ አርጎ እንደገና እስከሚመለስበት ጊዜ ድረስ በምድር ላይ የእርሱ ወኪል የሆነ ጳጳሰ ወይን ንጉስ ወይም ሌላ ሰው የለም ወኪሉ አንድ ብቻ ነው እርሱም መንፈስ ቅዱስ እኔም አብን አለምናለሁ ለዘላለምም እናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችጊል እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይናገርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል ዮሐ ባ የመንፈስ ቅዱስ ስራና ውለታ እጅግ ብዙ ነው። አዲስ ዘር በልቤ የተዘራው ለመጀመሪያ ጊዜ በዚያ ዓርብ ምሽት ነበር ሌላም ጊዜ ደግሞ ከዚህ ቀደም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህን የነበሩ በኋላ ግን ያንን ትተው ፕሮቴስታንት የሆኑ አንድ ሰው ቤት ውስጥ ጥቂት ሰዎች ብቻ ተሰብስበን በነበርንበት በአንድ ወቅት ወንጌል ሲናገሩ ስማኋቸው። ምሳሌ የቀዘቀዘ ውኃ ለተጠማች ነፍስ ደስ እንደሚያሰኝ ከሩቅ አገር የመጣ መልካም ምስራች እንዲሁ ነው የየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለኔ እንዲህ ነው ኮ የመጨረሻዎቹ ሰባት ቃላት ክርስቶስ ተሰቅሎ የተናገራቸው አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ሉቃስ እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ። ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው ሉቃስ ሰው ካስተማረው መንፈስ ቅዱስ ያስተማረው ይበልጣል። ወደፊትም ሁለት ጊዜ ተፈጸመ የሚልበት ጊዜ ይመጣል። ለመጀመሪያ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በእጄ እንዲገባ ያደረገው ያ ውድ ወንድሜ ነበር ሳይገነዘበው ትልቅ ውለታ ነው የዋለልኝ እሱ የሰጠኝ መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወቴን ለወጠው ሰማያዊ በረከት አጎናጸፈኝ እምነቴንም ቀየረው የቅዱሳንን የመላእክትንና የሰማዕታትን አማላጅነት እርግፍ አድርጌ ትቼ እኔ ነኝ ሕይወትም እውነትም መንገድም ብሎ በተናገረው የሱስ ክርስቶስን ተጠማጠምኩ ስተኛበትም በነበረው መኝታ ቤት ግድግዳ ላይ የጌታ ስዕል ያለበት እንደዚህ የሚል ጽሑፍ ያለበት ሰቀልኩ መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ክንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና የሐዋ ስራ ኳ በክርስቶስ አምሄፔ ተጠመቅሁ። ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ የሠራዊት አምላክ ሆይ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሜትና የልብ ደስታ ሆነኝ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው ሥጋ ምንም አይጠቅምም እኔ የነገርሏችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው መዢ ካ ኤር ባ ዮሐ ይህ ቃል» የተባለው መጽሐፍ ቅዱስ ካይናችን ሊሰወርና ከእጃችን ሊርቅ አይገባም እግዚአብሔር ሰውን የሚያናግርበት ዋናው መንገድ በእሱ ነውና አንዳንዴም በሌላ መንገድ ያናግረናል። እግዚአብሔር ከአሁን የተሻለ ጊዜ አያውቅም። በሐዋርያት ስራ ላይ «አጋቦስ» የተባለ ነቢይ ወደ ኢየሩሳሌም ጳውሎስ ቢሄድ የሚደርስበትን መከራ ከነገረው በኋላ «ሰዎች እባክህ እንዳትሄድ» ብለው ሲለማመጡት ይህንን ታሪካዊ ንግግር ተናገረእኔ መታሰር ቀርቶ ስለ ጌታ የሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳን ዝግጁ ነኝ። ይህ ዓለምም በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ለማዳን የመጣው የሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ሁሉን የፈጠረ ጌታ ነው ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም ዓለም የተፈጠረው በእርሱ ቢሆንም እንኳ ዓለም አላወቀውም ዮሐ ። አንድ ልጅ «ቤት ማለት ምን ማለት ነው። የሱስም በቤት መቅደሰ ግቢ በሰሎሞን መመላለሻ ያልፍ ነበር ከዚህ በታች ያለውን ለማስተዋል የሚቻለው አስቀድሞ በእንግሊዘኛ የተጻፈውን መጽሐፈ መቃቢስ ቀዳማዊ ከምዕራፍ አንድ እስከ አራት በማንበብ ነው ግሩም አስደናቂ ታሪክ ነውና አደራ አንብቡት ቢነገር ቢወራ ቢተረክ ቢጻፍ ተዘርዝሮ አያልቅም የፋሺስቶች ግፍ ተብሎ እንደተጻፈ የሶርያው ጨካኝ ንጉስ አንጥያኮስ ኢሏሊፋነስ የተባለው በአይሁዶች ላይ የፈጸመው ከዚያ ጋር መመሳሰል ብቻ ሳይሆን ጭራሹንም ይብላል አገራቸውን ለመውሰድ ብቻ ሳይሆን እምነታቸውን ሁሉ ደምስሶ ቤተ መቅደሱን አርክሶ ቅዴዱስ ሰንበትን ሰርዞ ቅዱስ መጻሕፍትን አጥፍቶ ግዝረትን አስቀርቶ በሱ ፋንታ የአረመኔ እምነቱን ለመተካት ያልተቆጠበ ጥሪት ያደረገ ንንስ ነበር የሱ መርሐ ግብር ተሳክቶለት ቢሆን ኖሮ መድኅን ክርስቶስ ከአይሁዶች መካከል ለመወለድ ባልቻለና ለነፍሳችንም ቤዛ ባላገኛን ነበር ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ግብሩ እንቁላል ነበረ ይህን ጊዜ አበሻ ለኢትዮጵያ እሳቸውን ያስነሳ አምላክ በዚያ በአሰቃቂ ዘመን ማታትያስና ልጆቹን እነ ይሁዳ መቃቢስን አስነስቶ የዚያ የንጉስ ሰራዊት ተሸንፎ አይሁዶች እስከ አሁን ድረስ ኸኑካ እየተባለ የሚከበረውን ታላቅ የድል በዓል ለመቀዳጀት ቻሉ ሁልጊዜ ማሸነፍ ስራው የሆነ አምላክ እነሂያን የእምነት አርበኞች ተጠቅሞ ባርነት ጦርነትና ስቃይ ቀርቶ ነፃነት እልልታና ደስታ እንዲመጣ አደረገ በምድር በነበረበትም ጊዜ ጌታ ክርስቶስ በበዓሉ ላይ ተገኝቶ ነበር ዮሐ ይህም በዓል በየዓመቱ በዚህም አገር ጭምር ስለሚከበር ሄጄ ለማየትና የተደረገውን ታሪካዊ ድል በአንክሮ ለማሰብ እዓጓለሁ እንደዚህ ያለ ታሪክ መረሳት የለበትም ከእሱም የሚጠቅም ትምህርት መቅሰም አለብን ዮሐ እነሆ ያ ሰው ስጋ የለበሰውን አምላክ አዋርዶ ያለ ልክ ወላዋዩ ሏጴላጦስ ልቡ ፈርቶ ወዲህና ወዲያ አመንትቶ በሕዝቡ ጩኸት ተገፋፍቶ እነሆ ያ ሰው በማለት ምንም ሳይገኝበት ስሕተት አሳልፎ ሰጠው ለሞት እነሆ ያ ሰው የሌለበት ጉድለት ያልተገኘበት ኃጢአት ያ የሰማይ መስፍን ፍጹም ነበር ያለ እንከን እነሆ ያ ሰው ለኔ ሲል የተከሰሰው መራራን ጽዋ የቀመሰው የተሰደበ በሰው አፍ የተገረፈ በጅራፍ በቡጢ የተመታ እጅግ የተንገላታ እነሆ ያ ሰው ስለኔ የተከሰሰው የኔ ተስፋ የኔ አለኝታ የደህንነቴን ዋጋ የከፈለ በጎልጎታ በአውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቄጠርነው እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቁሰሉ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በአርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ሩስል እኛ ተፈወስን ኢሳ አላወቁም ነበር የሱስ ተነስቶ ከአንድ ስፍራ ሊሄድ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ከደቀመዛሙርቱ ጋራ አላወቁም ነበር ያ ቀን የስንብት ጊዜ መሆኑን አላወቁም ነበር ጌታ ሲያርግ ወደ ሰማይ እንደሚቀሩ በምድር ላይ አላወቁም ነበር ከእነሱ ጋር እንደገና እንደማይሄድ በምድር አቧራ መንገድ አላወቁም ነበር ያ ፅለት መሆኑን የመለያየት በድንቅ የተሞላ በትንግርት። ፓሰተር ተበጆም አብርሃም አንድ ልጁን ይስሐቅን ሊሰዋ ወደ ሞሪያ ተራራ ወጥቶ ሊሰዋ ሲል በእሱ ፈንታ የሚታረድ በግ እግዚአብሔር እንደሰጠና በዚያም የተነሳ ይስሐቅ በነጻ እንደተለቀቀ አስተማሩ የዚያን ጊዜ ነው የወንጌል ምስጢር የተገለጸለኝ ከሰማይ ብርሃን ከበራልኝ ቀን አንዱ ያ ቀን ነበር በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ በሞት ጥላ ምድር ላለው ብርሃን ወጣለት። «መብረቅ አንድ ቦታ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚመታው» ይባላል የአምላክ ቸርነት እንደዚህ ቢሆን ምን ይውጠን ነበር። ክርስቶስ እንኳን በመስቀል ተሰቅሎ አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ብሎ በጸለየበት ወቅት አብ ራሱን ከዓለም ጋር እያስታረቀ እዚያ ነበር እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆና ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና ቆሮ እግዚአብሔር አምላክ ዝም ብሎ ተመልካች አይደለም በችግራችን ሁሉ ተካፋይ ነው። ዮሴፍም ወንድሞቹን አሰናበታቸው እንዲህም አላቸው በመንገድ እርስ በርሳችሁ አትጣሉ ዝፍ ዱ በተከሰተው ባዩትና በስሙት ነገር አምላክን ከማመስገን ይልቅ ይንን ጉላ ብለው እንደሚነታረኩ ገብቶት ስለነበረ ይህንን ማስጠንቀቂያ ሰጣቸው በመንገድም ሆነ በቤት ወይም በሌላ ስፍራ በስምምነት ሰዎች ሲኖሩ ቅዱሳን መላአክትም እንኳን ከእነሱ ጋር ለመራመድና ለመኖር ይመኛሉ በሮሜ ያለው ቃል እንዲሀ ይመክረናል እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል እብድ ቢጨምት እስከ እኩለ ቀን ነው» እንደሚባለው ለጥቂት ጊዜ እንኳን ደሀና ቢመስሉ ቆየት ብለው ጠብ የሚጭሩ ሰዎች አለ እንደዚህ ካሉ ጋር ለመኖር ሌት ተቀን ትዕግስት ያስፈልጋል ሌላውን ለማስተካክል ባትችል የራስህን መንፈስ መግታት ይኖርብሃል። ውሻ የሚለውን ቃል ሰዎች ለስድብ ይጠቀሙበታል መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበትም ዘመን ውሻ እንዳሁኑ ጊዜ ክብር የተሰጠው ለማዳ እንሰሳ አልነበረም። እግዚአብሔር ያለው ተስፋ አለው እሱ የተስፋ አምላክ ነው። አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትተጠርባቸው ሉቃስ የሐዋ ስራ ክርስቶስ «አባታችን ሆይ» የሚለውን ጸሎት ሲያስተምር ይቅር ማለት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ሁለት ጊዜ ነው ደጋግሞ ያስተማረው። ኤር ይሀ ግሩም የአምላክ ተስፋ ነው ወላጆች ለልጆቻቸው መልካም እንደሚያስቡና መልካም ለማድረግ እንደሚጥሩ አምላክም በእሱ ለሚያምኑ ከዚያ የበለጠ ያስባል ያደርጋልም ለእኛ በየሱስ ክርስቶስ በማመናችን የተነሳ ልጆቹ ለሆንን ወደፊት ያለው ጊዜ ቀዝቃዛና ድቅድቅ ጨለማ አይደለም ፍጸሜው ያማረና በተስፋ ሞልቶ የተረፈ ጊዜ ይጠብቀናል። የኔ አስቴር የኔ ፍቅር ይሀ ቀን እንዲከበር እንኳን አደረስሽ እግዚአብሔር። ከጸዳለ ሽፋው ብዕር አገርም አየሁኝ ፅረፍትም አረፍኩኝ ከዚያም ከተል ብዬ መስራትም ጆመርኩኝ ትንሽ እንደቆየሁ ስራውን ስለምድ ምንም ሳላስበው ምቀኛ ብድግ ስራውን ለቀቅሁ ሳልወድ በግድ እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ጸሎቴን እያልኩ እንደገና ዕረፍቴን አሁንም ቀጠልኩ አንደ መልእክተኛ እንደምትበር ወፍ ስሟ አስቴር ይባላል ስራዋም ቅልጥፍጥፍ አጋጣሚ ሆኖ ሰዎችን ልትረዳ እኔም አገኘኋት እዚያው ሎማሊንዳ አመጣጤን ሁሉ ሳወራት በርጋታ እሷም እንዲህ አለች በሳቅ በፈገግታ መፍራት የለብሽም እነ ክሊፈርደን ጠይቂ በደንብ እያሰቡ ናቸው ስለ ቤትሽና ስላንቺም በደንብ ስልኳን ቅጭል አረኩ ተገናኙኝ ብዬ ሳይውሉ ሳያድሩ ሊገናኙኝ መጡ ካለሁበት ቦታ ነይ እንሂድ አሌኝ እጅግ ወደሚያምር አንድ የወይን ቦታ ልብሶቼን ጠቅልዬ ተከትዬ መጣሁ ፈንድቄ በርካታ ውድ ወዳጄ ሆይ ምስጋና ይድረስሽ ለዋልሺው ውለታ ይኸው እገኛለሁ ከአንግዊን ኮረብታ እንዲሁም ምስጋና ለፈጣሪ ጌታ ለኔ ለዋለለኝ ለሰጠኝ እርዳታ ወሮ ጸዳለ ሽፋው የእምነት ሴት ነች የአሜሪካንን ኑሮ በእምነት ታግላ እንዳሸነፈች በቅርብ የምናውቃት ሁሉ እንመሰክራለን ቤትሰቦቿን ለማምጣት ወደ አገራችን ሳትጓዝ በፊት ያነበብንላት ጥቅስ ኤር ላይ ይጥኛል አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እነሆ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረፃል ከአንተም የሚያትት ነገር የለም የሰማይ አምላክ ምድር ወርዶ ስለረዳት ሁሉ ነገር ተከናውኖላት በሰላም ተመለሰኝ። የኔ አስቴር የኔ ፍቅር ይህ ቀን እንዲከበር አንኳን አደረሰሽ እግዚአብሔር በፅድሜ ላይ ዕድሜ በሕይወትሽ ላይ ልምላሜ በዚያ ላይ ታክሎበት ጤንነትና ሀብት ፍስሐና ምቾት ሁሉን እንድትጠግቢ ያለ ልክ አብዝቶ ይባርክሽ የኛ አምላክ ሊመዘን የማይቻል በእውነት አይተሻል ፈተና በያይነት አሁንም የገጠመን መከራ አምላክ ስላለ ከኛ ጋራ እንገጥመዋለን ሳንፈራ ትሆኛለሽ አይዞሽ ደህና ምን አለ በይኝ እንደገና ዳግም ይመጣል ጥሩ ጤና በዚህ ቀን የተሰበሰቡት ሁሉ እንኳን አደረሰሽ እያሉ እልልታቸውን ያቀልጣሌ አንቺም አብሮ አደረሰን በማለት ተደሰቺ በዚህ ፅለት ስጪን ሰላምታ አሳይን ልዩ ፈገግታ እንዲከበር የኛ ጌታ ቤታችን ይሙላ በደስጋ «ታሞ የተነሳ እግዚአብሔርን ረሳ» ይባላል እኛ ግን ጌታ አምላክን ላለመርሳት ወስነናል።