Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
በማለት የነቢያትን ቃል ተናገረዮሐ ሐዋርያው ናትናኤልስምዖን ወንጌልን በሶሪያ በባቢሎን በግብጽና ሊቢያ እየተዘዋወረ አስተምሯልማቴ ዐ በመጨረሻም በግብጽ ሲያስተምር ሕዝቡ በትምህርቱ አምነው በመብዛታቸው አረማውያኑ ስለቀኑበት ለግብጹ ንጉሥ እንድርያኖስ ከስሰው በሠራዊት በማስያዝ በንጉሠ ትእዛዝ ሐምሌ ዐ ቀን በሰይፍ አስገደሉትስንክሳር ሐምሌ ሩ ቅዱስ ጳውሎስ ነው እርሱም ለአቴና መንበር ቅዱስ ዲዮናስዮስን ሊቀጳጳስ አድርጎ ሾመው በመጀመሪያው መክዘ የአቴና መንበር ወደ ሮም መጠቃለል በመጀመሩ እየቀዘቀዘ መጥቶ ነበር። የቤተክርስቲያን ታሪክ በአለም መድረክ የታላቁ አምለካ ምስክሮች እንዳልሆኑ ሥራዎች ይገኙባቸዋል እንደ ይሀዋ ምስክሮች ወይም አርዮሳውያን አባባል ይሐዋ ሁሉን የሚችል አምላክ ሲሆን ለምትፈተረው አዲሲቱ ዓለም ንጉሥ ይሆን ዘንድ የታጨ ነው ይሉታል ትምህርታቸውንም በማርዘም ክርስቶስ ማለት የመጀመሪያው መልአክ ሚካኤል ተባለው ነው ብለው ያምናሉ ያስተምራሉ ምዕራፍ ሰባት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ጉባኤ የተመሰረተው በዐኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነውቀድሞ ቤተክርስቲያን ስትመሰረት ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይኖር ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን ሐዋርያት ሌሎችም ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት አመሰራረቷን ዓላማዋን አጠቃላይ ሁኔታ በስፋት አስተምረው ነበር ቢያስተምሩም ቅሉ ከጊዜ በኋላ በክርስቲያኖች መካከል በየወቅቱ መለያየት ይፈጠር ነበር።
የቤተክርስቲያን ታሪክ በአለም መድረክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ ምዕራፍ አንድ የቤተክርስቲያን ታሪክ መግቢያ የቤተክርስቲያን ትርጉም እና ስያሜ ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል ከግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጓሜውም ማደር ወገን ነገድ ዘር ጉባኤ ማኅበር ቤተሰብ ማለት ነው ቤተክርስቲያ ለሚለው ቃል ሶስት ዋና ዋና ትርጉሞች በሃይማኖት ትምህርት ይሰጠዋል በመጀመሪያ ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች ማደሪያ የክርስቲያኖች ቤት የሚል ትርጉም በመስጠት ቤቱን መሰብሰቢያውን ሕንፃውን ያመለክታል ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ስለበደላቸው ምህረት ለመለመን ሕይወት የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በተለይም ደግሞ ለኃጢያት ሥርየት የተሰዋውን የክርስቶስን ሥጋና ደም ለመቀበል የሚሰባሰቡበት ቤት ቤተክርስቲያን ተብሎ ይጠራል ከጌታ ትንሳኤ በኋላ ደቀመዛሙርቱ በኢየሩሳሌም ከተማ የማርቆስን እናት የማርያምን ቤት እንደ ቤተክርስቲያን ይጠቀሙበት ነበር የመጀመሪያዋ ሕንፃ ቤተክርስቲያን የተሰራችው በፊልጵስዩስ ከተማ ነው አሁን ግን በዓለም ሁሉ ታንፃለች ው በሌላም በኩል ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል እያንዳንዱን ክርስቲያን ሊያመለክት ይችላል ይህም ቤተ ማለት ወገንን በሚያመለክትበት ጊዜ ነው ቤተ ያዕቆብ ቤተ ሌዊ ቤተ እስራኤል ወዘተ እንደሚባለው ሁሉ የክርስቶስ ወገን የሆኑ ክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ በጥምቀትም የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ስጦታን ስለሚያገኙ የተቀደሱና የተከበሩ ናቸው ዳግም ኃጢአትን ሠርተው ራሳቸውን እስካላደፋ ድረስ ንጹህ ማደሪያው ናቸውና ቤተክርስቲያን ይባላሉ ው በመጨረሻም ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች አንድነት ጉባኤ ወይም ማኅበር ማለት ነው ጌታ ስለይቅርታ ሲያስተምር ወንድምህ ቢበድልህ ሔደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው ባይሰማህ ግን አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ እነርሱንም ባይሰማ ለቤተክርስቲያን ንገራት ደግሞም ቤተክርስቲያንን ባይሰማት እንኳ እንደ አረመኔና ቀራጭ ይሁንልህ በማለት ገልጂል ማቴ እዚህ ላይ ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል የክርስቲያኖችን ጉባኤ እንደሚያመለክት ግልጽ ነው ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል በመጀመሪያ የተጠቀመበት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ በቅዱስ ወንጌል እንመለከታለን ማቴ ተገፀ ምእመናን ደቀመዛሙርትን ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያን የተባሉት በአንፆኪያ ቢሆንም ቤተክርስቲያን የሚለው ስያሜ ቀድሞ በጌታችን የተሰጠን ስለሆነ አምላካዊ ስጦታችን ነውና እንጠብቀዋለን ቤተክርስቲያን በባህርይዋ አንዲት ብትሆንም ማንነቷን ለመግለጥና ለማስተዋወቅ እንዲሁም ከአገልግሎቷ አንፃር የተለያዩ መጠሪያዎች አሏት ሐዋርያትም በዚሁ መንገድ በተለያየ ስም እንደጠሯት በአጭሩ እንመለከታለን ሃፆ ቤተክርስቲያን ዘክርስቶስ ዘእግዚአብሔር ይህ ስያሜ የተሰጣት ቅዱስ ጳውሎስ እንደጻፈው የቤተክርስቲያን ራሷ ገዥዋ አዳጀ ክርስቶስ ነው ኤፌ ገ ገላገሩ ገተሰ ተ ገጢሞ ተሰ ሃፆ ማኅደረ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ማደሪያን እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑና በቸርነቱ ያድርበትና ሕዝቡን ይጎበኝበት ዘንድ በቤተክርስቲያን የሚገለጥና ፀጋውን የሚሰጥ በመሆኑ ኢሳ ገ ኤፌ ገቆሮ ሩ ሃፆሦ መዝገበ ፀጋ የፀጋው ግምጃ ቤትን ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ስጦታዎች የሚታደልበት ቦታ ስለሆነ ነው ዕብ ገቆሮ ሃፆ ቤተ ጸሎት የጸሎት ቤትን ክርስቲያኖች ሁሉ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ምስጢራቸውንም ከእርሱ ጋር የሚወያዩባት ቤት ቤተክርስቲያን ናት ኢሳ ዜና ያሩገ ፆ ምስካዬ ኅዙናን የነዳያን መጠጊያን ቤተክርስቲያን የተቸገሩ ሁሉ የሚረዱባት ቤት በመሆኗ ሉቃ የቤተክርስቲያን ባሕርይ ሩ አንዲት ናት ቅዱስ ጳውሎስ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሰራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ ኣንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት አንድ አካልና አንድ መንፈስ እያለ የገለጣት ቤተክርስቲያንን ነው ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ራስ አንድ ነው እርሱም ክርስቶስ ነው ኤፌ ሩ ሰዎች የተለያየ ሐሳብ የተለያየ ምኞትና ፈቃድ ሊኖራቸው ቢችልም ቤተክርስቲያን ግን የአንድ ክርስቶስ አካሉ ናትና አንዲት ናት ሃፀፀ ። የቤተክርስቲያን ታሪክ በአለም መድረክ ለተከታዮቻቸው በቃልም በኑሮም በመጻሕፍትም አውርሰው በተጋድሎ ዐረፉ ቀ የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ታሪክ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ትውልዳቸው ከአሥራ ሁለቱ ነገደ እሥራኤል ነው ጴጥሮስና ወንድሙ እንድርያስ አባታቸው ከነገደ ሮቤል ሲሆን እናታቸው ደግሞ ከነገደ ስምኦን ናት ያዕቆብ ወንድሙ ዮሐንስ አባታቸው ከነገደ ይሁዳ ሲሆን እናታቸው ደግሞ ከነገደ ሌዊ ናት ፊልጾስ ከነገደ ዛብን በርተሎሚዎስ ከነገደ ንፍታሌም ቶማስ ከነገደ አሴር ማቴዎስ ከነገደ ይሳኮር ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ከነገደ ጋድ ስምኦን ቀነናዊ በኋላ ናትናኤል የተባለውን ከነገደ ብንያም ታዲዎስ የተባው ልብድዮስ ከነገደ ዮሴፍ በይሁዳ ምትክ የገባው ማትያስ ከነገደ ዳን ናቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስምዖንኬፋን ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳ ነው የአባቱ ስም ዮና ይባላል ጌታን ከመከተሉ በፊት ከአምስት አመት ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ሲሆን በጎልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሳ አጥማጅ ነበር ማር ገፀ ለደቀመዝሙርነት ሲመረጥ ዕድሜው ዓመት እንደነበር ይነገራል የመጀመሪያው ስሙ ስምዖን ሲሆን ጌታችን ጴጥሮስ ብሎታል በላቲን ቋንቋ አለት በአረማይክ ኬፋ በግዕዝ ኩኩሕ ማለት ነው ማቴ ሩ የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ ተሰጥቶታል ቅዱስ ጴጥሮስ በፍልስጥኤም በልዳ በኢዮጴ በቂሳርያ በሶርያ በጳንጦን በገላትያ በቀጳደቅያ በቢታንያ በሮሜና በተለያዩ ሀገሮች እየተዘዋወረ አስተምሮ አሳምኗል ሐዋ ተ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም ንጉሠ ነገሥት ኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግስት በክርስቲያኖች ላይ በተነሳው ስደትና መከራ በመስቀል ተሰቅሎ በሰማዕትነት አረፈ በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው የቤተክርስቲያን ጸሐፊ ቅዱስ ጴጥሮስ በቫቲካን ኮረብታ ጳውሎስ ደግሞ በሮም በአስቲያ መንገድ መቀበራቸውን መስክሯል ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም የእነዚህን ታላቅ የቤተክርስቲያን መሠረቶች የሆኑ ቅዱሳን አባቶች የዕረፍታቸውን መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ሐምሌ ቀን ተከብራለች ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ዮሐንስ ሀገሩ ገሊላ አውራጃ ሲሆን ከወንድሙ ከቅዱስ ያዕቆብና ከአባቱ ከዘብዴዎስ ጋር ዓሳ ያጠምድ ነበር ማር ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ እመቤታችንን እንዲያገለግላት አደራ የተሰጠው ለዮሐንስ ነው ዮሐ ሩ ጌታ ይወደው የነበረው ዮሐንስ በፍልስጥኤምና በሌሎች ቦታዎች ክርስትና እንዲስፋፋ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በመተባበር አስተምሯል ሐዋ ፀ ከኢየሩሳሌም ወደ ኤፈሶን በመሄድ በታናጂ እስያ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት በማስተማር ሲያገለግል ቆይቶ በድምጥያኖስ ዘመነ መንግስት ወደ ደሴተ ፍጥሞ ተሰዶ በግዞት ሳለ ራዕየ ዮሐንስን ጽፏል ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስን ቅዱስ ያዕቆብ የዮሐንስ ወንድም ሲሆን የመጀመሪያ ሥራው ከአባቱ ጋር ዓሳ ማጥመድ ነበር ማር ያዕቆብ በኢየሩሳሌም ውስጥ በተመሠረተችው ቤተክርስቲያን መሪ ሆኖ በማስተማር ከፍ ያለ አገልግሎትን አበርክቷል በስፔን ሀገርም እንደሰበከ በቤተክርስቲያን የታሪክ መዛግብት ይነገራል የክርስትናን ትምህርት በስፋት በማስተማሩ በአይሁድ ዘንድ እንደ ወንጀለኛ ይቆጠር ነበር በዚህም ምክንያት ሄሮድስ አግሪጳ አይሁድን ለማስደሰት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በ ዓም አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ በሰማዕትነት ዐረፈ ሐዋ ቅዱስ ያዕቆብ የኖረውም ያረፈውም በኢየሩሳሌም ከተማ ነው ከገቱ ሐዋርያት መካከል መጀመሪያ ሰማዕትነትን የተቀበለ ሲሆን ይህም በሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፈለት ብቸኛ ሐዋርያ ነው ራ እነዚህ እስካሁን ከላይ ያየናቸው ሶስት ሐዋርያት ማለትም ጴጥሮስ ዮሐንስና ያዕቆብ አዕማደ ሐዋርያት የምስጢር ሐዋርያትን ይባላሉ ገላ ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ሃፀዐፀ ከፀ ርዐበገዐቋበሃ በቋከበገፀውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህረት ቤት ትምህርት ክፍል። የቤተክርስቲያን ታሪክ በአለም መድረክ ቅዱስ እንድርያስ የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ሲሆን ትውልዱም በቤተሳይዳ ነው በዓሳ ማጥመድ ተግባር ላይ ሳለ በጌታ ቃል በመጀመሪያ የተጠራ ነው ዮሐ ተጓ ጌታን ከመከተሉ በፊት የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር ነበር ዮሐ ገ ቅዱስ እንድርያስ መጀመሪያ የስብከት ሥራውን በፍልስጥኤም ጀመረ የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ የነበረው አውሳብዮስ እንደገለጠው እንድርያስ በሩስያ ወንጌልን ሰብኳል ቀጥሎም በቢታንያ በገላትያ በሩማንያ በመቄዶንያ በታናሽ እስያ በግሪክ አገሮች አስተምሯል የቁስጥንጥንያን ቤተክርስቲያን የመሰረተና የቁስጥንጥንያ የመጀመሪያ ሊቀጳጳስ መሆኑ በቤተክርስቲያን ታሪክ ይነገራል በመጨረሻም ግሪክ ውስጥ ምትሩ ለምትባለዋ ሀገር ሲያስተምር በጣዖት አምላኪዎች እጅ ረ የሚመስል ቅርጽ ባለው መስቀል ተሰቅሎ በድንጋይ ተወግሮ ታህሳስ ቀን በዐ ዓም በሰማዕትነት አርፏል ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጾስ ቅዱስ ፊልጾስ ሀገሩ ቤተሳይዳ ነው ዮሐ ሩገ ጌታ ተከተለኝ ባለው ጊዜ ወዲያውኑ ጥሪውን በመቀበል ጌታን ከመከተሉም በተጨማሪ ናትናኤልን ወደጌታ ያቀረበ የጠራን እርሱ ነው የሐ ሩ ጌታችንን ለማየት የፈለጉት ከአህዛብ ወገን የነበሩት ግሪኮች ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርበው የተማሩት በፊልዖጾስና በእንድርያስ አቅራቢነት ነበር ዮሐ ሐዋርያው ወንጌልን በታናሽ እስያ ውስጥ በምትገኘው በፍርግያ አስተምሯል በመጨረሻም በታናሽ እስያ ሲያስተምሩ በተቃዋሚዎች እጅ ተሰቅሎ ዐርፏል ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዲዲሞስ ሐዋርያው ቶማስ በፋርስና በሕንድ አስተምሯል ሕንድ የደረሰው በ ዓም ገደማ ነው ጌታ ከሙታን እንደተነሳ ለሐዋርያት በተገለጠበት ጊዜ ቶማስ ስላልነበረ ከሞት መነሳቱን ሐዋርያት ሲነግሩት ሳላይ አላምንም አላቸው ጌታ ሁሉም ባለበት እንደገና ተገልጦ ቶማስ በጣቱ የጌታን የተወጋ ጎኑን የተቸነከረውን እጅና እግሩን ዳስሶ አምኗል ጌታዬ አምላኬ ብሎም መስክሯል ዮሐ ዐ መምልኪያነ ጣኦት በ ዓም የቅዱስ ቶማስን ቆዳውን ገፈው ስልቻ በመስራት በሰውነቱ ላይ ጨው ነስንሰው በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሉት ታሪክ ይመሰክራል ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ገጽ ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ጌታን ከተከተለ በኋላ የወንጌልን ትምህርት በአረብ በሕንድ በአርመንያና እንዲሁም በአካባቢዋ አስተምሯል የአርመን መንበር ያቋቋመው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ነው በተአምራቱና በትምህርቱ ብዙ ክርስቲያኖችን በማፍራቱ በቅናት ሰዎች ተነስተውበት መስከረም አንድ ቀን አሸዋ በተሞላ ከረጢት ውስጥ ከተው ከነሕይወቱ ባህር ውስጥ ጣሉት በዚያም ዐረፈ በነገውም ክርስቲያኖች ምእመናን ከባህር አውጥተው እንደቀበሩት የቤተክርስቲያን የታሪክ መዛግብት ይናገራሉ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስሌዊን ቅዱስ ማቴዎስ የመጀመሪያ ስሙ ሌዊ ነው ማር ሩገ ማቴዎስ የሚለውን ስም ያወጣለት ጌታ ነው ማቴዎስ የቀድሞ ሥራው ቀራጭ ግብር ሰብሳቢ ነበር ማቴ ፅሩፀ የቀረጥ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ጌታ ጠጋ ብሎ ተከተለኝ አለው ወዲያው በቤቱ ታላቅ ግብዣ ለጌታ አድርጎ ጓደኞቹ የነበሩትን ቀራጮችን ወደጌታ አቅርቦ ካገናኛቸው በኋላ ሁሉንም ትቶ ተከተለው ሉቃ በዚህም አንዳንዶች ማቴዎስን የቁም ተዝካሩን አውጥቶ ጌታን የተከተለ ሐዋርያ ይሉታል ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ለስብከት ሲሰማራ በዕጣ የደረሰችው ሀገር ምድረ ፍልስጥኤም ስትሆን ቀጥሎ በኢትዮጵያ በፋርስ በባቢሎን አካባቢ እንደሰበከ ይነገራል ገድለ ሐዋርያት ገጽ ዐገ ቅዱስ ማቴዎስ የአይሁድና የአረማውያንን ትምህርት እየተቋቋመ ድውያን ሲፈውስ አጋንንትን ሲያወጣ ልዩ ልዩ ተአምራትን ሲያደርግ ዝናው በከተማ ሁሉ በመዳረሱ በዚህ የተናደዱ መኳንንት የሞት ፍርድ ፈረዱበት ጥቅምት ገ ቀን አንገቱን በሰይፍ ተሰይፎ ዐረፈ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ሃፀዐፀ ከፀ ርዐበገዐቋበሃ በቋከበገፀውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህረት ቤት ትምህርት ክፍል። የቤተክርስቲያን ታሪክ በአለም መድረክ ተናገረው ጳውሎስም የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ከነገረው በኋላ ደማስቆ እንዲገባ አስታወቀው ሐዋ ፀገ ሐናንያም ወደርሱ ተልኮ በወደቀ ጊዜ የተጋረደበትን ካይኑ እንደቅርፊት እንዲወድቅ ካረገ በኋላ አጥምቆና አስተምሮ ለአገልግሎት ዝግጁ አደረገው ቅዱስ ጳውሎስም አረብ ሀገር ሄዶ ሶስት ዓመት ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ተመልሶ መስበክ ጀመረ አይሁድ በቅናት ተነሳስተው ሊገሉት ሲያሳድዱት የደማስቆ ክርስቲያኖች ከከተማዋ ቅጽር በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ካደረጋቸው ጉዞዎች የመጀመሪያው ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ከተመለሰ በኋላ በልዑል እግዚአብሔር ጥሪ በአሕዛብ ሀገር ወንጌልን ለመስበክ ከበርናባስ ጋር ወጡ ሐዋ በዚህ ጉዞአቸው በጠቅላላ ወደ ሺህ ኪሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዘዋል ጉዞው የተከናወነው በ ዓም አካባቢ ሲሆን ከ የማያንሱ ሀገሮች ተጎብኝተዋል ሩፍ ሁለተኛው ጉዞ በ ዓም ገደማ ከሲላስ ጋር ያደረገው ጉዞ ነው በጉዞው ከገፀ የማያንሱ ከተሞች የተጎበኙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ገላትያ ጢሮስና ኤፌሶን ቆሮንቶስ ልስጥራ ኢየሩሳሌም አንጾኪያ ይገኙበታል ደቀመዝሙሩን ጢሞቴዎስን ያገኘው በዚህ ጉዞው በልስጥራ ከተማ ሊያስተምሩ ነው ሩፍ ሶስተኛውን ጉዞ ያደረገው በኔ ዓም ሲሆን ብዙ ሀገሮችን በጉዞው አካትቷል በዚህ ጉዞው ከልዩ ልዩ ሀገር ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ዕርዳታ ለኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ይዞ ሲመለስ በኢየሩሳሌም የፋሲካ በዓል ስለነበር ከየሀገሩ የመጡ አይሁድ ቅዱስ ጳውሎስን ተቃወሙት ተቃውሞውን ለመግታት በአይሁድ ህግ በቤተመቅደስ የመንጻት ስርዓት መፈጸም ጀመሩ ነገር ግን ከአህዛብ ወገን የነበረውን ደቀመዝሙሩን ጢሞቴዎስን ወደ መቅደስ ያስገባው መስሏቸው ተቃውሟቸው በረታ በዚህ የተነሳ ከተማዋ ታወከች ሐዋ በሁከቱ የተነሳ ሐዋርያው ጳውሎስ በ ዓም ለሮም እስር ተዳርጓል ሁለት ዓመት በቁም እስር ቆይቶ ከሮማ ህግ ጋር የሚቃወም ምንም ዓይነት ወንጀል ስላልተገኘበት በነጻ ተለቅቋል ከዚህ በኋላ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ያልተመዘገበውን ጉዞውንም ያደረገው በመታሰሩ ያዘኑትን ክርስቲያኖች ለማጽናናትና የጀመራቸውን ሥራዎች ፍጻሜ ለማየት ነው በመጨረሻም በኔሮን ቄሳር ዘመን የሮም ከተማ ስትቃጠል ይህንን ያደረጉት ክርስቲያኖች ናቸው በማለት በክርስቲያኖች ላይ የሞት አዋጅ ታውጆ ስለነበር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኒቆጳልዮን ከተማ ሲያስተምር በ ዓም ተይዞ ዓመት ከ ወር በጨለማ ቤት በእስር ከቆየ በኋላ በሮም ከተማ ከኦስትያ መንገድ አንገቱን ተሰይፎ በ ዓም ሐምሌ ቀን በሰማዕትነት አርፏል የሐዋርያት መንበርና ሀገረ ስብከት ሀን የኢየሩሳሌም መንበር ክርስትና መጀመሪያ የተሰበከው በኢየሩሳሌምና በአካባቢዋ ስለነበር የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ከተማዋን በማዕከልነት ይጠቀሙባት ነበር የኢየሩሳሌሙ መንበር የመጀመሪያ ፓትርያርክ ቅዱስ ያዕቆብ የጌታችን ወንድም የተባለውን ሲሆን በ ዓም በሰማዕትነት ሲያርፍ ወንድሙ ስምዖን በመንበሩ ተተካ እርሱም በ ዓም በኢየሩሳሌም ከተማ በሰማዕትነት አርፎአል ጌታችን በትንቢት እንደተናረገው ማቴ በዐ ዓም ሮማዊ ንጉስ ጥጦስ ሺ ሠራዊት አዝምቶ ከተማዋን በመውረር ከተማዋን ሰብሮ ገብቶ በዚያን ጊዜ በሮማውያን አገዛዝ ላይ አምፀው የነበሩትን አይሁድ ግማሾቹን ሲፈጃቸው የቀሩትን ደግሞ በባርነት ሸጣቸው ከተማዋንም አፈረሳት በዚህም የተነሳ የኢየሩሳሌም መንበር በመጠኑም ቢሆን ቀዝቅዞ ነበር ለን የአንጾኪያ መንበር አንጾኪያ ለሮም አስተዳደር ሶስተኛ ከተማ የነበረች የሶርያ ከተማ ነች በዚህች ቦታ ቀድመው ወንጌልን የሰበኩት ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ ሲሆኑ ቅዱስ ጴጥሮስም ሰብኮባታል በከተማዋ አይሁድም አህዛብም ነበሩባት የጌታ ደቀመዛሙርት ክርስቲያን የሚለውን ስም ያገኙት በዚህች ከተማ ነው ሐዋ ሩ ለመጀመሪያዋ የሐዋርያት ሲኖዶስ ሃፀዐፀ ከፀ ርዐበገዐቋበሃ በቋከበገፀውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህረት ቤት ትምህርት ክፍል። የቤተክርስቲያን ታሪክ በአለም መድረክ ስለ እራሱ አመጣጥም ሲገልጽ በሰማርያ እንደ አብ በይሁዳ እንደ ወልድ በአህዛብ ዘንድ እንደ መንፈስ ቅዱስ ሆቼ የታየሁና የተገለጥኩ መሲ ክርስቶ እኔ ነኝ እያለ የምንታዌ የሁለትነትን ትምህርት ያስተምር ነበር ስለ ዓለም አፈጣጠርም ሲናገር ይህ ዓለም የተፈጠረው ሰው በስህተቱ ከፈጣሪው ከተጣላ በኋላ ነው ይላል ሁለት አማልክት አሉ ብሎ ስለሚያምን ይህ ዓለም የተፈጠረው በዝቅተኛውርበተዋራጁን አምላክ ነው ይላል ስምዖን መሠሪ በ ዓም በሮም ውስጥ ሞቷል አሟሟቱም እኔ ክርስቶስ ነኝ እያለ የክርስቶስን እድገት በማስመሰል በምትሃት ወደላይ ከፍ እያለ ሲሄድ ቅዱስ ጴጥሮስ በትምህርተ መስቀል ቢያማትብ ወደ ላይ ያነሱት አጋንንት ስለራቁ ወድቆ እንደሞተ የቤተክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል መርቅያን በታናሻ እስያ ግዛት ውስጥ የተወለደ ሲሆን አባቱም ኤጴስ ቆይስ ነበር መርቅያን በልጅነቱ ወራት በቤተክርስቲያን በፈፀመው ጥፋት ከቤተክርስቲያን አባረውታል በዐ ዓም ወደ ሮም ግዛት በመምጣት ለድሆች ምጽዋትን በመስጠት ተቀባይነትን አገኘ እንዲሁም ከመናፍቃን ጋር እየተከራከርኩ ነው በሚል ሽፋን የራሱን ንፋቄ ይዘራ ስለነበር ከቤተክርስቲያን በድጋሚ ተባሯል የመርቅያን አስተሳሰብና አስተምህሮ ው መርቅያን ሁለት አማልክትርክፉና ደግን የሚለውን ሃሳብ ይደግፋል ከግኖስቲኮች የሚለይበት ነገር ቢኖር ክፍ አምላክ ከደጉ አምላክ የተከፈለ አይደለም ው መርቅያን በክፋት የሚጠራውና የሚያማርረው የእስራኤልን አምላክ ነው ክፉ አምላክ በብሉይ ኪዳን ሲሠራ ሲቀጣ የኖረ ጨካኝ ዳኛ ነው ምህረትና ርህራሄ የለውም ይላል ደጉ አምላክ ግን ክርስቶስ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ ማንም የማያውቀው ተሰውሮ የኖረ ክርስቶስ ስለ እርሱ መጥቶ አስተማረ ሐዲስ ኪዳንንም ሠራ ህዝቡንም ከክፉ አምላክ አላቀቀ ብሎ ያስምራል ው የክርስቶስ ሥጋ መልበስ ምትሀት እንጂ አማናዊ አይደለም ብሎ ያስብ ነበር ሠ ክርስቶስ በመስቀል የተቀበለው መከራ በምትሃት ስለሆነ እርሱን አላገኘም ባይ ነው ው መርቅያን ዷጺሚና ታራሚ ስለሆነ የሚከተሉትን ጾምን እንዲያዘወትሩ አጥብቆ ያስተምር ነበር ይህም አስተምህሮ ቶሎ ከሥጋ ለመላቀቅና ከዚህ ዓለም ፈጣሪ ለመላቀቅ ነው የብሉይ ኪዳንን ህግ አብዝቶ ስለሚጠላ በቀዳሚት ሠንበት የጾምና የሀዘን ቀን እዲሆን አኳል ው ጋብቻንም አብዝቶ ይቃወም ነበር የሚያጠምቃቸውም ያላገቡትንና ከሴት ርቀው ንጽህና ተብቀው የሚገኙትን ነው ቆሩ ሁለቱ የትርጓሜ ትምህርት ቤቶች ቅዱሳት ሐዋርያት ከጌታ የተቀበሉት የተማሩትን በሚገባ ለማስተላላፍ ከረዳቸው ነገር አንዱ ትምህርት ቤት ማቋቋማቸው ነበር በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የሚታወቀው የመጀመሪያው ትምህርት ቤት በዐ ዓም በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ የተመሰረተው የእስክንድርያ ትምህርት ቤት ነው የትምህርት ቤቱ ዓላማም አዳዲስ አማኞች በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት በማሰልጠንና ከዚያም ሲወጡ ወገኖቻቸውን ለማስተማር የሚያስችላቸውን እውቀት እንዲያውቁ ማድረግ ነው በኃኛውና በኛው ክፍለ ዘመን ከመንፈሳዊ እውቀት ባሻገር ሁለገብ ዕውቀትና ፍልስፍናም ጭምር ይማሩ ነበር ሁለተኛው ትምህርት ቤት በሶርያ ዋና ከተማ በነበረው በአንጸኪ ተመሠረተ ይህን ትምህርት ቤት የመሠረተው ሉቂያኖስ የተባለው ሰው ነው ትምህርት ቤቱም የተመሠረተው በኛው ምዕተ ዓመት አጋማሽ ሲሆን በዚህ ትምህርት ቤት ብዙ ፈላስፎች ገብተው ተምረዋል በዚህ ጊዜ የፍልስፍናው አስተሳሰብ የክርስትናውን እምነትና ትምህርት በክሎታል በዚህ ትምህርት ቤት ፍልስፍና በጣም ነግሶ ነበር ማለት ይቻላል ው የእስክንድር የትርጓሜ ትምህርት ቤት በዚህች ከተማ ብዙ የግሪክና የግብፅ ፈላስፎች የጥበብ ሰዎች ስለነበሩ ክርስቲያኖችም እምነታቸውን ለማስተዋወቅና የጥበብና የፍልስፍና ሰዎችን ለመምረጥ ሲሉ ትምህርት ቤቱን በእስክንድርያ መስርተዋል ብዙ ታላላቅ ፈላስፎችና የፍልስፍና ሃፀዐፀ ከፀ ርዐበገዐቋበሃ በቋከበገፀውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህረት ቤት ትምህርት ክፍል። የቤተክርስቲያን ታሪክ በአለም መድረክ አምላክ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ የሚሆን ሁሉ በእርሱ የሆነ ታመመ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛው ቀን የተነሳ ወደ ሰማይ አረገ ህያዋንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ ዳግመኛ የሚመጣ የሚሉት ናቸው ጉባኤ ቁስጥንጥንያ ጉባኤው የተካሄደው በፀገ ዓም በቁስጥንጥንያ ነው ምክንያት የሆነ መቅዶኒዮስ መንፈስ ቅዱስ ሕጹጽ ነው በማለት ባስተማረው ትምህርት ነው ይህ ክህደት ሲነሳ የቁስጥንጥንያ ንጉስ የነበረው ቴዎዶስዮስ ቀዳማዊ ይህ የቤተክርስቲያን ችግር በጉባኤ እንዲፈታ ባስተላለፈው መልእክት መሠረት ሊቃውንት ተሰብስበዋል በዚህ ጉባኤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የተወያዩባቸው መሠረታዊ ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው መቅዶንዮስና ትምህርቱን ለማውገዝ አቡሊናርዮስንና ትምህርቱን በምሥጢረ ሥጋዌ ቃል እግዚአብሔር ሰው በሆነ ጊዜ ሥጋን እንጂ ነፍስን አልተዋሃደም የሚለውን ክህደትን ለማውገዝ ወልድ የተዋሃደው የአዳምን ሥጋ አይደለም ሌላ በቅድምና የነበረ ሥጋ ነው እንጂ የሚሉ መናፍቃንን ለማውገዝ በኒቅያ ጉባኤ ላይ በተረቀቀው ጸሎተ ሃይማኖት ላይ የተጨመሩ ቱን የሃይማኖት ቀኖናዎችን ማርቀቅ በዚህ ጉባኤ ላይ መቅዶንዮስ መንፈስ ቅዱስ ሕፁጽ ፍጡር ነው ያለበትን ምክንያት ሲጠየቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አላቀረበም ከዚህም በኋላ ጉባኤው በኢሳይያስ በማቴዎስ በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንድነትንና ሦስትነን በማስረዳት ቢነገረው ከኑፋቄው አልመለስም በማለቱ ዐው ሊቃውንት የክህደት ትምህርቱንና እርሱን አውግዘው ለይተውታል ሌላው ጉባኤው የአቡሊናርዮስን በምሥጢረ ሥጋዌ ቃል እግዚአብሔር ሰው በሆነ ጊዜ ሥጋን እንጂ ነፍስን አልተዋሃደም የሚለውን የክህደት ትምህርት አውግዘዋል ለዚህም በዮሐንስ ላይ ቃል ሥጋ ሆነ የሚለውን በመጥቀስ በትክክል የቃልና የሥጋን ውህደትና መጽሐፍ ቅዱሳዊነት ሊቃውንት አስረድተዋል ቅዱስ ጎርጎሪየስ ዘኢንዝናዙም ሰው ማለት ነፍስና ሥጋ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን እንጂ ነፍስ አልነሳም ከተባለ ያዳነው ሥጋን እንጂ ነፋስን አይደለም ብሎ በመመለስ የአቡሊናርዮስን ክህደት ተናግሯል ከዚህም በማያያዝ ጉባኤው በኒቅያ ጉባኤ አንቀጸ ሃይማኖት ከተጠቀሱት ተጨማሪ አንቀጾችን አስቀምጧል እነርሱም በጌታ በአዳኝ ከአብ በሠረፀ ከአብና ከወልድ ጋር በነቢያት በተናገረ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እንስገድለት እናመስግነው በሁሉ ባለች በሐዋርያት ጉባኤ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን ለኃጥያት ማስተሰርያ በምትሆን በአንዲት ጥምቀት እናምናለን የሙታንን ትንሳኤ ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት እንጠባበቃን ለዘለዓለሙ አሜን ጉባኤ ኤፌሶን ይህ ጉባኤ ሦስተኛው ዓለማቀፍ ጉባኤ ሲሆን ለጉባኤው መሰባሰብ ምክንያት የሆነው የንስጥሮስ የክህደት ትምህርት ነው በምሥጢረ ሥጋዌ ክርስቶስን በሁለት ከፍሎ አንዱን የዳዊት ልጅ ሁለተኛውን የእግዚብሔር ልጅ ነው ብሎ ያምንና ያስተምር ነበር ስለዚህ እመቤታችን የወለደችው የዳዊትን ልጅ እንጂ የእግዚብሔርን ልጅ አይደለም በማለት ያስተምር ነበር ንስጥሮስ ለክህደት ትምህርቱ የተጠቀመበት ዮሐ ቃል ሥጋ ሆነ የሚለውን መለወጥን ያስከትላል ያለውን ቃል በሥጋ አደረ ብሎ እንዲመቸው አድርጎ በመተርጎም መሪ ጥቅሱ ነበረ ለንሥጥሮስ ለክህደት ትምህርቱ በሚገባ ምላሽ የሰጠው የእስክንድርያው ሊቀጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ ነው ታላቁ አባት ቅዱስ ቄርሎስ የቃልና የሥጋን ተዋህዶ በማስረዳት የውላጤንና የኅድረትን ትምህርት ክህደቱን አጋልጧል የንስጥሮስን ትምህርት በመጀመሪያ የተቃወመችው የእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ነች የሚባለው በቅዱስ ቄርሎስ አማካኝነት ነው ምዕራፍ አምስት ሃፀዐፀ ከፀ ርዐበገዐቋበሃ በቋከበገፀውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህረት ቤት ትምህርት ክፍል። የቤተክርስቲያን ታሪክ በአለም መድረክ በደቡብ አፍሪካ በዩኤስ አሜሪካ በካናዳ በአውስትራሊያ በኬንያ ወዘተ አብያተ ክርስቲያናት መሥርታ ወንጌልን ታስተምራለች ው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክርስትናን በመንግስት ደረጃ የተቀበለው በኛው መቶ ክዘመን ቢሆንም በ ዓም ክርስትናን ቀድማ የተቀበለች መሆኗ የታወቀ ነው የተቀበለችውም በጅሮንድ በጃንደረባው አማካኝነት ነው እርሱም ከፊሊጾስ የተማረውን የክርስትና ትምህርት ለወገኖቹ አስምቷል የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ አውሳብዮስ ጃንደረባው ለወገኖቹ ለኢትዮጵያ ሰዎች ሐዋርያ ሆነ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሐዋርያትን ጉባኤያትና ኒቂያ ቁስጥንጥንያ ኤፌሶንን ውሳኔዎቻቸውን ትቀበላለች ሌሎች ጉባኤዎችን አትቀበልም የታቦታትን የጽላትንን የስዕልን ክብር የቅዱሳንን በአጸደ ሥጋና ነፍስ ማማለድ ታምናለች ታስተምራለች ኡ የሶርያ የአንፆኪያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ በቅዱስ ጴጥሮስ እና በእነ ቅዱስ አግናጥዮስ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የተመሰረተችው የሶርያ የዕቆባዊትን ቤተ ክርስቲያን ከእስክንድርያ ከኢትዮጵያ ከአርመንና ከሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አርንታልን አብያተ ክርስቲያናት ጋር ቦሦስቱ ጉባኤያት በኒቂያ በቁስንጥንጥንያና በኤፌሶንን የትምህርተ ሃይማኖት ውሳኔዎች ታምናለች በኒቂያ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ የአርዮስን የክህደት ትምህርት በጥብቅ የተቃወመው ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ የአንጾኪያ ጳጳስ ነው የአንጾኪያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እንደ እስክንድር ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው ለሚነሱት መናፍቃን መልስ ስትሰጥ የቆየች ናት ው የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስንል በደቡብ ህንድ የሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ የማላባርየኬሬላን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ማለት ነው ሐዋርያት ዕጣ ሲጣጣሉ ለቶማስ የደረሰችው ሕንድ እንደሆነች መሥራቹም ሐዋርያው ቶማስ እንደሆነ የሕንድ ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች። ከፀ ርዐበገዐከሃ በቋበገፎውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህረት ቤት ትምህርት ክፍል።