Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ከሀቢ ከ ቧ ከቦ በ ከ ነነ ላበአከ ከዐሀከ ዐሀከቧ ዐ ጤፀሂፀከከ ቪፀኗፀርከ ዝክረ ሕግ ዓም።
ከሀቢ ከ ቧ ከቦ በ ከ ር እበበከበበ ከሃ ሺኛ ከበ ከርከ ከህ ከዐ ኘ ላ ላሀ ከ ከ ዩኗፐዉ ርኣ ቨዣ እበእፕእላዐእሏ ርዐእፒክጀእኣርጀ ዐ ዝዐመሏእ ህ እዐህበከ ላበ ላከኮ ዐአኣ ሄ እ በህ ዐ ሀኪ ሀ ላበ ላከከ በፎዌርፍቨሃ ለበበ ላከ ከ ከ የመንግሥት ለውጥ በኋላ የምሥራቅ ጎጃም ገበሬዎች የገጠሟቸው ፖለቲካዊ ግጥሞች ደር ጌቴ ገላዬ ፀርርሃርርሀሃከርበ የአፍሪቃ እና የኢትዮጵያ ጥናቶች ተቋም ሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን ጭማቴቄ ጽሑፍ ለከከር ይህ የጥናት ወረቀት በኢትዮጵያ ከ ዓም የመንግሥት ለውጥ ወዲህ የምሥራቅ ጎጃም ገበሬዎች የገጠሟቸውን ያዜሟቸውንና ያንጎራጎሯቸውን ፖለቲካዊ ግጥሞች ይመለከታል የግጥሞቹ ዋነኛ ጭብጥ በወቅታዊ የገጠር አስተዳደርና በገበሬዎች ማኅበራዊ ሕይወት ላይ የሚያተኩር ሲሆን በመንግሥት ባለሥልጣናት በአገር አንድነት ጥያቄና በተለይም ደግሞ በቅርቡ በ ዓም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተካሄደውን የገጠር መሬት ሽግሸግ ፖሊሲ አፈጻጸምና ሸግሽጉ ያስከተለውን ተጽዕእኖ ይቃኛል በተጨማሪም ባንድ በኩል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገጠሩ ማኅበረሰብ ዘንድ እየተባባሰ የመጣውን መንግሥትን የመጠራጠር የእርስበርስ ጥላቻና ተቃውሞ በሌላ በኩል ደግሞ የምግብ እጥረት የምርት ማሽቆልቆል ድህነት ስደትና በሰላም አብሮ የመኖር ተስፋ መጨለም ያሳሰባቸው የጎጃም ገበሬዎች ብቸኛ ሀብታቸው በሆነው ዘይቤያዊና ቅኔ ለበስ አማርኛ ቃልግጥም ለከር ፀዐርከኘ ስሜትን የሚኮረኩሩና ልብን የሚነኩ መልእክቶች እንደሚሜሰነዝሩ በምሳሌ በተደገፉ ግጥሞች ትንታኔ ያቀርባል የገበሬዎቹ ሥነልቦናዊ አስተሳሰብ ባህላዊ ዕውቀትና ስለ አካባቢ ያላቸው ጥልቅ ግንዛቤ ስለ ባህላዊ ዳኝነትና አስተዳደር ስለ ልማትና መሬት አያያዝ ወዘተ የሚያቀርቧቸው ሐሳቦች የሚገለጹበት አንዱ መንገድ ለዘመናት ባካበቱት የሥነቃል ፎቧዘር ቅርስ አማካኝነት በመሆኑ በማኅበራዊ ሳይንስና በገጠር ልማት ተመራማሪዎች በሥነትምህርት በሥነሰብእና በሥነቃል ምሁራን እንዲሁም በመንግሥት ፖሊሲ አውጭዎች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በጥንቃቄ መሰብሰብና በጥልቀት መጠናት እንዳለበት ይህ የጥናት ወረቀት ያመለክታል መግቢያ ይህ አጭር የጥናት ወረቀት ያማርኛ ቃልግጥሞችን ትንታኔ ያቀርባል ግጥሞቹን የሰበሰብኋቸው ምሥራቅ ጎጃም ውስጥ ከልዩ ልዩ የገጠር ቀበሌ መስተዳድሮች ሲሆን ከ የመንግሥት ለውጥ ወዲህ የገበሬዎች ወቅታዊ ማኅበራዊ አስተዳደራዊ ፖለቲካዊና ልማታዊ ጉዳዮች በአማርኛ ቃላዊ ግጥሞች እንዴት እንደተንፀባረቁ ከማኅበራዊ ሥነሰብእ እና ከሥነቃል አኳያ ለማጥናት በ በ በ እና በ ዓም የመስክ ጥናትና ምርምር ባደረግሁባቸው ጊዜያት ነበር ሥነቃላዊ ግጥሞቹ በ ዓም ካዘጋጀሁት የድኅረ ምረቃ ቲስስ እና በ ዓም ካጠናቀቅሁት የፒ ኤች ዲ የጥናትና ምርምር ሥራዬ ውስጥ የተወሰዱ እጅግ ጥቂቶች ናቸው። መሬቴንም ውሰድ ደጄንም እረሰው የምኖርበትን ቤቴን አታፍርሰው ወይ አልተጣላን አልተደባደብን ሰተት ብለው መጥተው ቤት አፍርሱ አሉን እኸሉንም እንኩ ልጃችንን እንኩ የሬሳችንን መውጫ ቤታችንን አትንኩ ግጥሞቹ በደርግ ዘመን ልዩ ልዩ ሹመት ተሰጥቷቸው የመንግሥትን ትእዛዝና መመሪያ አስፈጻሚ ለነበሩ የቀበሌ ገበሬ ማኅበራት ባለሥልጣናት ተቃውሞ የተገጠሙ ናቸው መንደሩ ባድማው አድባሩ የአያት ቅድማያቶቹ መናፍስት ይጠብቁኛል ብሎ የሚያምነውን ገበሬ ሳያማክሩትና ቀጠሮ ሳይሰጡት ለመንደር ምሥረታና ለሰፈራ ብለው ቤቱን በግዳጅ ላፈረሱበት የደርግ ካድሬዎች የሰጠው ምላሽ ነበር በግጥሞቹ ውስጥ በሚያሳዝን ሁኔታ የተገለጸው የገበሬው ቤት መፍረስ ብቻ አይደለም በተከታታይ የደረሰበትን አሰቃቂ በደል ማለትም የመሬቱን መነጠቅ የልጆቹን ወደ ጦር ሜዳ መወሰድና የልፋቱ ውጤት የሆነውን ምርቱን በኃይል መዘረፉንም በቁጭት ይናገራል በግልጽ ከ በኋላ በምሥራቅ ጎጃም ገበሬዎች የተገጠሙ ፖለቲካዊ ግጥሞች በደርግ ሶሻሊስታዊ አገዝ የተማረሩትና የተሰላቹት የጎጃም ገበሬዎች የፖለቲካ ለውጥን መምጣት በጉጉት ነበር የሚጠብቁት አካባቢው በኢሕአዴግ ቁጥጥር ሥር ከሆነበት ከየካቲት ዓም ጀምሮ የጎጃምን ሕዝብ ሲዘርፉትና ሲያሰቃዩት የነበሩት የደርግ ሹማምንት የኢሠፓ አባላትና የቀበሌ ባለሥልጣናት የቻሉትን ያህል የሕዝብ ገንዘብና ንብረት ዘርፈው ወደ አዲስ አበባና ወደ ዓባይ በረሃ ይፈረጥጣሉ በኋላ በግንቦት ወር ኢሕአዴግ መላ ሀገሪቱን ሲቆጣጠርም በደርግ መንግሥት መውደቅና በፖለቲካ ለውጡ የተደሰቱት የጎጃም ገበሬዎች ስሜታቸውን እንደሚከተለው ነበር በግጥም የገለጹት ደስ ይበልህ ጎጃም ድፍን ኢትዮጵያ ያ ቀማኛ መንግሥት ገባ ምድረ ትቢያ ደርግን በማሸነፍ ጊዜያዊ ሰላምና መረጋጋት ያመጣላቸውን የኢሕአዴግ መንግሥትና በተለይም ደግሞ የትግራይን ተጋዳዮች ተጋዳላዮች እንዲህ በማለት ነበር በግጥም ያወደሷቸው ተጥየ ነበረ እንደ አሮጌ ቁና ብድግ አርጎ አነሣኝ ኢሕአዴግ መጣና ትግሬ ተንቀሳቅሶ ኢሕአዴግ ባይመጣ ትንሽ ቀርቶን ነበር ነፍሳችን ልትወጣ ኢሕአዴግ ባይመጣ ባይሰማ ወሬ ይታረድ ነበረ ጭቁን እንደ በሬ ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ እንደወጣ በእርግጥ ገበሬዎች ድርጅቱንና መንግሥትን በአንስታይ ጾታ ነበር የሚጠሩት መሪዎቹ ለጎጃም ገበሬ በመጀመሪያ ቃል የገቡለትና የሰጡት ጊዜያዊ እፎይታ የሚከተሉት ጉዳዮች ነበሩ ኛ ሕዝቡ ራሱ ጊዚያዊ ሰላምና መረጋጋት ኮሚቴዎችን በነፃና በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲመርጥ ኛ በደርግ ዘመን በኃይል ይተገበሩ የነበሩ የመሬት ድልድል የኮታ የግብርና የልዩ ልዩ መዋጮዎች እንዲነሥ ያምራቾችና ያገለልግሎሉት የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሙሉ በሙሉ እንዲፈርሱና ገበሬዎች በሰፈራና በመንደር ምሥረታ ትእዛዝ የሠሯቸውን አዳዲስ ቤቶች አፍርሰው እፈለጉት ቦታ ላይ እንዲሠሩ ኛ በግዳጅ ለጦርነት መመልመል እንደማይኖር ወላጆች ልጆቻቸውን ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሄዋን ሳይደርሱ እንደፈለጉ እንዲድሩ ኛ ባካባቢያቸው የሚንቀሳቀሱትን ሌቦችና ሽፍቶች ለማጥፋት የኢሕአዴግ ታጋዮች በተለይም ክፍለ ሕዝብና የኮር አባል የሚባሉት አዳዲስ ካድሬዎች ከጎናቸው እንደሚቆሙ አረጋገጡላቸው። መንግሥቱ ወደቀ የማታ የማታ እየዋለ እያደረ ቀናት በሳምንታት ሳምንታት በወራት ወራት በዓመታት እየተቆጠሩ ሲሄዱ የጎጃም ገበሬዎች ለተለያዩ ፖለቲካዊ አስተዳደራዊ ልማታዊና ግብርናዊ መመሪያዎችና ትእዛዝች ሐሳባቸውንና ስሜታቸውን በአዳዲስ ግጥሞች ማንፀባረቅ ብቻ ሳይሆን በደርግ ዘመን የተገጠሙትንም እያስታወሱ ማዜም ይጀምራሉ ለምሳሌ በ እና በ በየቀበሌው መጠነኛ የሆነ የመሬት ክፍፍል ተደርጎ ነበር የመሬት ክፍፍሉ ባብዛኛው ባገር ሸማግሌዎች የተከናወነ ቢሆንም ሥልጣን ላይ የወጡትና አዳዲስ ሹመት የተሰጣቸው የኢሕአዴግ ተመራጮች እላይ ከተጠቀሱት የኮር አባላት በተጨማሪ ሞቢሳይዜሽን ካድሬ ምኒሻና ታጣቂ በሚባሉት ነበር የተካሄደው ቀስ በቀስም በደርግ ዘመን ይደረግ እንደነበረው ለሹማምንቱ ጉቦ መስጠት ድግስ ማብላትና ማጠጣት በድብቅም በይፋም ሲከናወኑ መታየት ይጀምራሉ በንዲህ ዓይነቱ አድሎአዊ የመሬት ክፍፍል ጊዜ ለኮሚቴዎቹ ጉቦ መስጠትና መጋበዝ አቅም ያነሰውና ከኮሚቴዎቹ ዝምድና የሌለው ምስኪን ገበሬ ብሶቱንና ቁጭቱን እንዲህ በማለት ነበር ያንጎራጎረው ኮሚቴም እጅአለ እኔም እጅ አጠረኝ እፎካካው መሬት አምዘግዝጎ ጣለኝ ለሊቀመንበሩ አንድ ባውንድ አጥቼ ለኮሚቴዎቹ አንድ ጠርሙስ አጥቼ ተማዞሪያው መሬት ቀረሁ ተለይቼ እኔ ተኮሚቴ አበልጅ ብናሣ ይሰጠኝ ነበረ ተድበሉ ማሳ ተሰባት ኮሚቴ አበልጅ አጥቼ አለ በቆሎ እሸት ከረሙ ልጆቼ በደርግ ጊዜ የኮሚቴዎች ቁጥር አሥራ አምስት ነበር ከለውጡ በኋላ ግን ቁጥራቸው ወደ ሰባት ዝቅ ብሏል በመጀመሪያው ስንኝ የተገለጸው የመሬት ዓይነት ፎካካ የሚለው ቃል ለም ያልሆነ ወይም ጠፍ መሬት ለማለት ነው እንዲሁም በሁለተኛው ግጥም ውስጥ ባውንድ የሚል ቃል ይገኛል በአካባቢው አማርኛ ወይም ዘዬ ባውንድ የሴቶች ሻሽ ወይም የራስ ማሰሪያ ማለት ቢሆንም እዚህ ላይ ግን አሥር ብር የሚል ትርጓሜ እንዳለው መረዳት ያስፈልጋል ገጣሚው በሁለተኛውና በሦስተኛው ግጥሞች የተጠቀመባቸው ማዞሪያ እና ድበል የተሰኙት ቃላት ባካባቢው አነጋገር ውሃ ገብ ወይም ለም መሬት የሚል ትርጉም አላቸው የሚከተለው ግጥም በደርግ ዘመን ምሥራቅ ጎጃም ውስጥ ለነበረ አንድ የገበሬ ባለሥልጣን የተገጠመ ነው ግጥሙን ራሱ የገበሬ ባለሥልጣኑ እንደገጠመው በማስመሰል የተሰናዳ ሲሆን በወቅቱ ለኢሕአዴግ ዋና ጸሐፊና ለሽግግሩ መንግሥት ፕሬዚደንት ለነበሩት ለአቶ መለስ ዜናዊ የቀረበ የይቅርታ ይደረግልኝ ዓይነት ምፀታዊ አቤቱታ ነው እግረ መንገዱን ግን በደርግ አገዛዝ ዘመን በሕዝብ ሳይ ያደረሰውን ምዝበራና በደል ሳይደብቅ ይናገራል ይህ ዓይነቱ ስላቃዊ አቀራረብ ትልቁ የግጥም ባሕርይና የገጣሚም ችሉታ መሆኑን ልብ ይሷል ዋሽቼ እንዳልበላ ኢሠፓ ፈረሰ አርሼ እንዳልበላ እጄ ለሰለሰ ሰርቄም እንዳልኖር ኢሕአዴግ ደረሰ አረ። ዓም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተደረገውን የገጠር መሬት ሸግሽግ ፖሊሲ አፈጻጸምና በተለይ የሽግሽግ ፖሊሲው በገበሬው ሕይወት ላይ ያስከተለውን አሉታዊ ገጽታ ይመለከታሉ የ የመሬት ሽግሽግ ፖሊሲ የኢሕአዴግ ሹሞችና የገበሬዎች እሮሮ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በሚከተሉት ሥራዎቹ እንዳጠናውና ሌሎች ምሁራን በተለይ ተፈሪ ይግረመው እና ኢገ እንዳስተዋሉት በ በአማራ ክልል ብቻ የተደረገው ይኸው የመሬት ሽግሽግ ፖሊሲ ገበሬዎችን በሦስት ጎራ ከፋፍሏቸዋል ቅሪት ፊዩዳል ቢሮክራት እና ጭቁን ወይም ድሃ አርሶ አደር በማለት ከመሬት ሽግሽጉ ቀደም ሲል በዚሁ ክልል ምናልባት በሌሎች ክልሎችም ሊሆን ይችላል የገጠር ቀበሌዎችንና ወረዳዎችን ማሽጋሸግ በሚል መመሪያ ያካባቢው ሕዝብ ፍላጎትና ሐሳብ ሳይጠየቅ የኢሕአዴግ ካድሬዎች የቀበሌ ባለሥልጣናትና የግብርና ሠራተኞች ወረዳዎችን ቀበሌዎችንና መንደሮችን ከአንዱ ወደ ሌላው በማጠፍ መጠሪያ ስሞችን ሳይቀር እንደፈለጋቸው ለዋውጠዋል ከሁሉም በላይ ግን ያላግባብ የጦር መሣሪያ ይዛችኋል ወይም ለመንግሥት ሳታስታውቁ መሣሪያ ደብቃችኋል ተብለው የተንገላቱ የተገረፉና የታሰሩ ገበሬዎች ቁጥር በጣም ብዙ ነው ከመሬት ሽግሽጉ በኋላ መሬት የተወሰደባቸው የጎጃም ገበሬዎች በደላቸውንና አቤቱታቸውን ለማሰማት መንግሥት አለ ፍትህርትእ አለ ብለው ወደሚያስቡት ወደ አዲስ አበባ ከተማ በእግር ተጉዘው ነበር እዚያ እንደደረሱም በፖሊስ ተከበው ተርበውና ተጠምተው ለሳምንታት ከተንገላቱ በኋላ የመሬት ሽግሽጉን አዋጅ ያጸደቀውና ያስፈጸመው የክልልላቸሁ የአማራ መንግሥት ስለሆነ ወደ ባሕር ዳር ሄዳችሁ አቤቱታችሁን መናገር ትችላላችሁ የሚል መልስ ከመንግሥት ተወካይ ይነገራቸዋል ብዙዎቹ ገበሬዎች ወደ መንደራቸው ሲመለሱ በኢሕአዴግ ካድሬዎችና ታጣቂዎች እየተፈለጉና እየተያዙ ተደብድበዋል ለእስራትም ተዳርገዋል ወደ ግጥሞቹ እንመለስና የመጀመሪያው ግጥም መሬቱ የተወሰደበት ገበሬ ያቅራራው ነው ገጣሚው ከመንግሥት አገዛዝ ከመሬት ሥሪት ከግብር እና ከመዋጮ ጋር የተያያዙ ሦስት ታሪካዊ እውነታዎችና የመንግሥት አገዛዞች ያነጻጽራል የመጀመሪያው ግጥም በአጴው ዘመነ የአማራ ክልል ልሳን በሆኑት ዝክረ ሕግ በኩር እና ማኀቶት ላይ በግልጽ እንደሰፈረው ቀደም ሲል በገበሬው ዘንድ ተሰምተው የማይታወቁት ቅሪት ፊዩዳልና ቢሮክራት ሰፋ ያለ ትርጓሜና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል ቅሪት ፊዩዳል ከአጴጹ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በመሬት ከበርቴነትና በባላባትነት ለምና ሰፊ የእርሻ መሬት በሕገ ወጥ መንገድ ይዘው የሚገኙትንና በደርግ ጊዜ መሬታቸው ያልተወስደባቸውን ገበሬዎች ይ መለከታል ቢሮክራት የተባሉት ደግሞ በደርግ አገዛዝ ዘመን በቀበሌ ተመራጭነታቸው ብዙ መሬት በሕገ ወጥ መን ገድ ከሌሎች ነጥቀው የወሰዱትን ከ ጀምሮ በየጊዜው መሬት ሲከፋፈል ተጠቃሚ የነበሩትንና በልዩ ልዩ ኮሚ ቴዎችተመርጠው ደርግን ያገለገሉ ገበሬዎች የሚመለከት ነው ጭቁን ወይም ድሃ አርሶ አደር የሚባሉት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥትም ሆነ በደርግ ጊዜ ምንም መሬት ያልነበራቸው ወጣቶች ባል የሌላቸው ሴት አር ሶ አደሮችና በተለይም የኢሕአዴግ መንግሥት ደጋፊዎችና ሹሞች ናቸው የመሬት ሽግሽጉን ፖሊሲ አስፈጻሚና ዋነኛ ደጋፊም እነዚሁ ጭቁን አርሶ አደሮች ናቸው ይህን በተመለከተ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአማራ ክልል ወረዳዎችን የማጠፍና የማሸጋሸግ ተግባር አፈጻጸም መመሪያ ባሕር ዳር ነሐሴ ዓም ገጾች እና የቀበሌ ማሸጋሸግ ተግባር አፈጻጸም ተግባር መመ ሪያ ባሕር ዳር ጥቅምት ገጾች ይመልከቱ መንግሥት የነበረውን የአሥራት ክፍያ እና በደርግ አገዛዝ የነበረውን እህል በግዳጅ የመነጠቅን ወይም ኮታን አረፍሁ ብሎና ተስፋ አድርጎ የነበረው ገበሬ በዘመነ ኢሕአዴግ የኮር አባል የሚባል ካድሬና ከበፊቶቹ የባሰ ቀማኛ መጥቶ መሬቱን በመጫኛ ሰፍሮ እንደወሰደበት ምሬቱን ይገልጻል ሁለተኛው ግጥም ደግሞ ይኸው የኮር አባል የሚባለው የኢሕአዴግ ባለሥልጣን የገጠሩን ሕዝብ እንዴት እንዳሰቃየው ገጣሚው ባካባቢው ከሚገኝና ኮርች ከሚባል እሾኻማ እንጨት ጋር በማነጻጸር በተለዋጭ ዘይቤ ያመሳስለዋል የኮር አባላት በመሬት ሽግሽጉ ወቅት ገበሬውን በማንገላታት እርስ በርስ በማጋጨትና መሬቱን በመውሰድ ለኢሕአዴግ መንግሥት ታማኝነታቸውን ያስመሰከሩ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው እነዚሁ የኮር አባላትም ለአገሩ መፍረስ ተጠያቁዎች እንደሆኑ ግጥሞቹ ያመለክታሉ አሥራት ቀረ ብዬ አርፌ ስተኛ ኮታ ቀረ ብዬ አርፌ ስተኛ የኮር አባል መጣ የባሰው ቀማኛ መሬቴን ወሰደው ሰፍሮ በመጫኛ ጣሊያን አልመጣብን ተኩስ አልተተኮሰ ወይ ወራሪ አልመጣ ችግር አልደረሰ። ኢሕአዴግን ዝንታለም ያኑረው የሚከተሉት አራት ግጥሞች በመሬት ሽግሽጉ ጊዜ ቅሪት ፊዩዳልና ቢሮክራት ተብለው የተከፈሉትን ገበሬዎች ይተቻሉ ግጥሞቹን የገጠሟቸው ጭቁን ወይም ድህ አርሶ አደር የተባሉትና ከመሬት ደልዳይ ኮሚቴዎችና ከኢሕአዴግ ካድሬዎች ጋር የመሬት ሸግሽጉን ፖሊሲ ያስፈጸሙ ግለሰቦች እንደሆኑ ያነጋገርኋቸው ገበሬዎች አስረድተውኛል ቅሪት ፊዩዳልና ቢሮክራት የተባሉ ገበሬዎች መሬታቸውን መነጠቅ ብቻ ሳይሆን የሌሎችን ገበሬዎች መሬት ተጠምደው ወይም ተከራይተው እንዳያርሱ ተከልክለዋል በእድር በእቁብ በሰንበቴና በማኀበር ከኀብረተሰቡ እንዲገለሉና አንገታቸውን ደፍተው እንዲቀመጡ ከአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት መመሪያ ተሰጥቷቸል በተጨማሪም በማናቸውም የቀበሌ ስብሰባ ላይ እንዳይገኙ ጥብቅ ክትትልና ተጽኖ ተደርጎባቸዋል አንዳንዶቹ አገር ጥለው ተሰደዋል ብዙዎቹ ደግሞ በሽተኛ ሆነዋልጹ አንገታቸውን ደፍተው የ ደኀና ቀንን መምጣት የሚጠብቁም አሉ ግጥሞቹ ቅሪት ፊዩዳልና ቢሮክራት የተባሉትን ገበሬዎች ብቻ ሳይሆን ልጆቻቸውንና ቤተሰባቸውንም ይቃወማሉ ይተቻሉ አረ። ቢሮክራት አረ። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በተለይ የጌቴን ከ ር ና የተፈሪን ጥናቶች ይመልከቱ የቢሮክራት ልጅ ሣር ብላ እንደ በሬ መሬትህ ተሰጥቷል ለድሃው ገበሬ ፊዩዳል ብትለፈልፍ ላንቃህ እስቲከፈት ተእንግዲህ አይገኝ አሻልማ መሬት የምሥራቅ ጎጃም ገበሬዎች የደረሰባቸው ግፍና በደል በመሬት ሽግሽግ ፖሊሲው ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የገጠር ልማትና ግብርና ነክ ተግባራት ተሰማርተው ገበሬውን ይረዳሉ ዘመናዊ የምርት ቴክኖሎጅን ለገበሬው ያስተዋውቃሉ ያስተምራሉ ተብለው በመንግሥት የተመደቡትን የግብርና ባለሞያዎችም በግጥማቸው ያማርራሉ የሚከተለው ግጥም እንደሚያመለክተው ቀደም ሲል ማዳበሪያ በማከፋፈል የሚታወቁት የግብርና ሠራተኞች ከኢሕአዴግ ካድሬዎች ጋር በመመሳጠር ምሥራቅ ጎጃም ውስጥ የሚገኘውን የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ሕዝብ ለስቃይ እንደዳረጉት በቀጥታ ይቃወማል የግብርና አለቆች ድሮ እምናውቃቸው ማዳበሪያ ማደል ነበረ ሥራቸው አሁን ተመሳጥረው ተኢሕአዴግ ጋራ እናርጅና እናውጋን አሳዩት መከራ በ ዓም የኢትዮጵያ መንግሥት ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ትኩረት በመስጠት የተቀናጀ የገጠር ልማት ለማካሄድ አዳዲስና ምርጥ ዘሮችን ገብስና ስንዴ ለምሥራቅ ጎጃም ገበሬዎች በብድር ሰጥቶ ነበር። ነገሩ በየቀበሌው ከሚሰጠው የአቅም ግምባታ ስልጠናና ቅስቀሳ ጋር ተያይዞ የመጣ ይመስላል የኮር አባል ሞቢላይዜሽን ካድሬ ታጣቂ ምኒሻና ክፍለ ሕዝብ የሚባሉት የኢሕአዴግ የፖለቲካ ሹማምንት የጎጃምን ገበሬዎች ሳይቀር የራስን ዕድል በራስ ስለመወሰን ስለ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ስለ ክልል ፖለቲካ ወዘተ በየጊዜው ይሰብኳቸዋል ከአገራቸው ከጎጃም ይልቅ ስለ ትግራይ ሕዝብ ጀግንነት ታጋይነትና አሸናፊነት አማራ የሚባለው ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ በሌላው የኢትዮጵያ ብሔረሰብ ላይ ስሳደረሰው የበደል ታሪክም ይነገሯቸዋል ከደርግ ሶሻሊስታዊ አገዝዝ ውድቀት በኋላ ኢትዮጵያን በዘርና በጎሣ የከፋፈለውን የኢሕአዴግ መንግሥት በገጠሩ የጎጃም ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ባማራው ላይ እያደረሰ ያለውን ፖለቲካዊ ተጽእኖም ይቃወማሉ ገበሬዎቹ ብዙ ከተመለከቱና ካስተዋሉ በኋላ የሚከተሉትን ብስል ፖለቲካዊ ግጥሞች ያዜማሉ ግጥሞቹ በሽግግሩ መንግሥት ወቅት በሠርግ በፉከራ በቀረርቶና በጤፍ አጨዳ ላይ በስፋት የሚደመጡና የሚዜሙ ነበሩ ግጥሞቹ ለትግራይ ሕዝብ የሚደረገውን አድልዎ ይተቻሉ በአማራው ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውንም በደል ያነሣሉ ሲከፋፋን ጊዜ ብናንጎራጉር እነዚያ ነፍጠኞች እንባል ጀመር ወይ አገሬ ጎጃም አጋሙ ግራሩ ሁሉንም ቆረጡት ለማገር እያሉ መቀሌ ታደሰ ከተማውም ሰፋ ትግሬ ብቻ ነወይ ላገሩ የለፋ። በመጨረሻም ገበሬዎቹ ከዘመቻ ከጦርነት ከረሃብ ከቸነፈር ወዘተ ተመክሮአቸው በመነሣትና ያለፈ ታሪካቸውን በማስታወስ እውነታ ያለውን አንድ ታሪካዊ ነቁጥ ይጠቅሳሉ ከጥንት ጀምሮ የመከራው መምጫ ከየት እንደሆነና ለችግሩም ተጠያቂዎች እነማን እንደሆኑ በግጥማቸው በግልጽ ያወሳሉ እንዲህ ብለው በቅሎ ግዙ ግዙ ግራጫ ግራጫ ወትሮም ተትግሬ ነው የመከራው መምጫ እኛ መች ፈለግነው የትግራይን ጠጅ እየበጠበጡ ያፋጁናል እንጅ ማጠቃለያ በሀገራችን የገበሬዎች ቃላዊ ቅርስ ከር እና ባህላዊ ዕውቀት በበዐፀበህ ዩክክኳ በቸልተኝነትና በምሁራን እጥረት ለባህል ለትምህርት ለታሪክ ለልዩ ልዩ ግብርናነክ ፖሊሲዎች ለልማትና ለዕድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በወጉ አልተጠናም ስለዚህ የገጠሩ ሕዝብ ቃላዊ ቅርስና ባህላዊ ዕውቀት ባፋጣኝ የጥናትና የምርምር ርእስ መሆን ይገባዋል ከምሥራቅጃም ገበሬዎች በተሰበሰቡ ፖለቲካዊ ግጥሞች ጥናት ላይ ተመሥርቶ የሚከተሉትን የማጠቃለያ ነጥቦች ማቅረብ አስፈላጊ ነው ግጥሞቹ በ የደረገውን የመንግሥት ለውጥና ከዚያ በኋላ የተከሰቱትን ወቅትዊና አካባቢያዊ ግጭቶች እንዲሁም ግብርናነክ ፖሊሲዎች ይመለከታሉ በተለይም በ የተደረገውን የገጠር መሬት ሽግሸግ ፖሊሲ በመቃወም የኢሕ አዴግ ካድሬዎች በገበሬዎች ላይ ያደረሱትን በደል በምሬት ይተቻሉ ገበሬዎቹም ሆን ተብሎ በሦስት ጎራ ማለትም ቅሪት ፊዩዳል ቢሮክራትና ጭቁን ወይም ድሃ አርሶ አደር ተብለው መከፈላቸው በገጠሩ ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋትንና የርስ በርስ ግጭትን አስከትሏል አንዳንዶ ችንም ለስደት ዳርጓል ገበሬዎቹ በግጥሞቻቸው ያነሣቸው ማኀበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና አስተድዳደራዊ ችግሮች በመጀመሪያ ደረጃ የመንግሥት ፖሊሲ አውጭዎችንና የገጠር ልማት ባለሞያዎችን ሊያሳስቡና አዎንታዊ ምላሽ ሊያገኙ ይገባልነ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የግብርና የገጠር ልማት የባህል የሥነ ትምህርት የሥነሰብእ የታሪክና የሥነቃል ምሁራን ሙያዊ ተቀናጅቶ በሚጠይቀው የምርምር ዘዴ ከሃ ሀከ የቃል ቅርስ ጥናትና ምርምር ላይ ትኩረት ማድረግና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል አገራችን ላለችበት የተወሳሰቡ ማኀበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች አንዱ ገጽታ የገጠሩን ሕዝብ ቀርቦ ካለማወቅ ኑሮውን ተጋርቶ ካለመኖር ሐሳቡን በጥሞና ካለመስማትና በተለይም ደግሞ ባህላዊና አገርበቀል ዕውቀቱን ተረድቶ በእሱው ፍላጎት ላይ የተመሠረተ እሱኑ ያሳተፈ የአስተዳደር የልማትና የግብርና ርሕ አለመነደፉ እንደሆነ በስፋት ይታመናል የጎጃም ገበሬዎች በብሶት ግጥሞቻቸው ያነሣችው አንኳር የፖለቲካ የገጠር አስተዳደርና የመሬትነክ ችግሮችም ይህንኑ እውነታ የሚ ያመላክቱ ናቸው ዋቢ መጻሕፍት ልከህ ዲከአበ ኾ ከከ ሀ ህበ ከ ዥኩር ኮገበር ሀቧጸ ዐ ጀከሀከ ከበፀኗ ቫ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዓም።