Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
በዋነኛነት ወደ ሁሉም መንደር እንዲገባ ማስቻል ተገቢ ይሆናል ባለሃብቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም እንዲረዱ ማገዝና ማበረታታት ያስፈልጋል የከተማው አስተዳደር የእነዚህን አካላት ተሳትፎ ለማበረታታት በመሬትና በመሠረተ ልማት አቅርቦት ህ ፊፊ ህእ ከ እ እ ከ ከ ህህህህ ቭ ቭ የከተማ ልማት ፖሊሲ።
ጻ ኹፌ ከኤፌ ጨኤ ጋህ ኩጋ ኩጋ ኤዱ ሯሯሯ ው ው የከተማ ልማት ፖሊሲ መግቢያ የከተማ ልማት ተግባር ሁለገብ የልማት ሥራን ያካተተ ሲሆን ይህም የኢንዱስትሪ የንግድ የመሠረተ ልማት የኢኮኖሚና የማኅበራዊ የአገልግሎት ሥራዎችን ያጠቃለለ ሆኖ የነዚህን ሥራዎች ቅንጅትና ትስስርን የሚጠይቅ ነው በመሆኑም ሁሉም የልማት ሥራዎች ምን ዓይነት ዓላማና ግብ ይዘው ከሥራ ዘርፋቸው አቅጣጫ በተጨማሪ ወደ ጋራ ውጤት እና ወደ አንድ የልማት ዓላማ እንዴት እንደሚያመሩ የሚያመላክት ሁለገብና አጠቃላይ አቅጣጫ ሊኖራቸው ይገባል ስለሆነም ይህንን አቅጣጫ የያዘ የከተማ ልማት ፖሊሲ መንደፍ ያስፈልጋል የከተማ ልማት አቅጣጫና ፍጥነት የሚወሰነው በገጠር ልማት አቅጣጫና ፍጥነት በመሆኑ የገጠር ልማቱ ዕድገት በከተሞች ልማት አድገት ላይ የጐላ ተጽዕኖ አለው በተመሳሳይ ሁኔታም ከተሞች የገጠሩን ምርት በመቀበልና ለገጠሩ አስፈላጊ የሆነውን ግብአት በማቅረብ ጉልህ ሚና ያላቸው በመሆኑ ከተሞች ካላደጉ የገጠር ልማቱም የሚጓተትና የሚገታ ይሆናል ስለሆነም በገጠርና ከተማ ልማት ትስስር ብቻ የሁለቱ ልማትና የሀገር ቀጣይና ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ልማት የሚረጋገጥ ይሆናል ይህ የገጠርና ከተማ ልማት ትስስርም ከከተሞች የአርስ በእርስ ትስስር ጋር ተቀናጅቶ እንዲሄድ በማድረግ ልማቱን ለማፋጠን ያስችላል በመሆኑም የገጠርና ከተማ አንዲሁም የከተማና ከተማ ትስስርን አቅጣጫ የሚያሳይና በሁለገብ መልኩ የሚያረጋግጥ የከተማ ልማት ፖሊሲ ያስፈልጋል የከተማ ልማት ከመልካም አስተዳደር ውጭ የማይናኖና ሰብ ነው ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ሰፊ ዲሞክራሲ ሰፊ የሕዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትአስተማማኝ ሠላምና መረጋጋት እንዲሁም የሕግ የበላይነት ካልሠፈነ የከተማ ልማት ይገታል ስለሆነም የከተማ ልማትና የከተማ መልካም አስተዳደር ትስስርን በዋነኛነትም የከተማ መልካም አስተዳደር ልዩ ባህርያትንና መሠረታዊ አቅጣጫን የሚያሳይ የከተማ ልማት ፖሊሲ ያስፈልጋል ከዚህም በተጨማሪ ሀገራችን ከዓለም ኢኮኖሚያዊና አጠቃላይ ሁኔታ ጋር የተሳሰረ እንጂ የተነጠለ ሕልውናና ጉዞ ሊኖራት ስለማይችል የሀገራችን ከተሞች በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ እየሆኑ የሚያድጉበት የልማት አቅጣጫ ያስፈልጋቸዋል ይህንን መሠረት አድርጐ የሚዘጋጅ የከተማ ልማት ፖሊሲ አቅጣጫም ከተሞቻችን በአካባቢያቸው በአህጉርና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆን ይኖርበኖል ይህም ማለት ከተሞቻችን ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያበቃቸው መሠረተ ልማት አገልግሎሉት ኢንዱስትሪና መልካም አስተዳደር እንዲፈጥሩ ማስቻል ነው ስለሆነም ይህ የከተማ ልማት ፖሊሲ ሠነድ እነዚህን አቅጣጫዎች አስተሳስሮና አጉልቶ በማስቀመጥ እንዲሁም የከተማ ልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎቻችን የሚመሩበትን አጠቃላይ እና ሁለገብ የፖሊሲ አቅጣጫ በሚቀይስ መልኩ ተቀርጺጳል የከተማ ልማት ፖሊሲ ክፍል አንድ ጊ የኢትዮጵያ ከተሞች ችግሮችና የፖሊሲው አስፈላጊነት የከተሞቻችን መሠረታዊ ችግሮች የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሀገራችን መሠረታዊ ችግሮች እንደመሆናቸው መጠን የከተሞቻችን ዋነኛ ችግሮችም እነዚሁ እንደሆኑ ይታወቃል ቀደም ሲል በነበረው ሁኔታ የገጠር ልማት ባለመፋጠኑ ከተሞች የገበያ የአገልግሎትና የኢንዱስትሪ ማዕከል ሆነው የገጠሩን ልማት በመደገፍ ራሳቸውን ሊያሳድጉ ካለመቻላቸው በተጨማሪ እርስ በእርሳቸውና እንዲሁም ከገጠሩ ጋር ተሳስረው የልማት ማዕከል መሆን አልቻሉም ይህም በመሆኑ ከተሞቻችን በከፋ ድህነት ውስጥ ተዘፍቀው የተመጽዋችና የሥራ አጦች መኖሪያ ሆነው ቆይተዋል በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መርህ መሠረትም ያልተማከለ አስተዳደር ሳይዘረጋላቸው የአካባቢ ሥልጣን ሳይኖራቸውና ለሁሉም ነገር ከበላይ ናየኖ ዘዙ በመቆየታቸው የመልካም አስተዳደር የሕግ የበላይነት የግልጽነት የተጠያቂነትና የአሣታፊነት ሥርዓት ሳይሰፍንባቸው ቆይተዋል የከተሞቻችን መሠረታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዋነኛ መገለጫዎችም የሚከተሉት ናቸው የልማት ችግሮች ሀ ከተሞቻችን በቂ የመሠረተ ልማት አውታር የተዘረጋላቸው ባለመሆኑ አብዛኛዎቹ ከተሞቻችን ትርጉም ያለው የመጠጥ ውኃ የመንገድ የመብራትና የቴሌፎን አገልግሎት ያልነበራቸውና በርካታዎች ደግሞ በውሱን ደረጃ ቢኖራቸውም ሽፋኑ ጠባብ ጥራቱም ዝቅተኛ ሆኖ ቆይቷል በመሆኑም የከተሞቻችን የመሠረተ ልማት አቅርቦት የሕዝቡን ዕለታዊ ፍላጐትም ሆነ የባለሃብቱን ጥያቄ የሚመልስ ሆኖ አልተገኘም ለሊ ከተሞቻችን ጥራትና ስፋት ያለው የማህበራዊ አገልግሎት አላገኙም ነበር ከገጠር ይልቅ በከተማ የተሻለ ሽፋን ነበር ቢባልም የከተማ ማህበራዊ አገልግሎት በአብዛኛው ሽፋኑ ጠባብ ጥራቱም ዝቅተኛ ነው አገልግሎቱም በጥቂት ከተሞች ላይ ብቻ ሆኖ ትኩረቱ በበሽታ ማከምና በቀለም ትምህርት ላይ የታጠረ ሲሆን በሽታን ለመከላከልና መሠረታዊ ትምህርትን እንዲሁም የሙያ ሥልጠናን ለማስፋፋት ቅድሚያ የሚሰጥ አልነበረም ስለሆነም አብዛኛውን ሕዝብ የሚበክሉ የድህነትና የኋላቀርነት በሽታዎችን መመከት የተማረ ሥራ አጥና ያልተማረ ተመጽዋች በስፋት እንዳይኖር መከላከል የሚያስችል አልነበረም ሔጤ ከተሞቻችን ሰፊ የቤት እጥረትና የከተሞች ይሁን የሠፈሮች አርጅና ችግር አለባቸው ከሕዝብ አድገትና ከልማት ሥራ መስፋፋት ጋር የሚመጣጠን ለድሀው መካከለኛ ገቢ ላለውና ለባለሀብቱ የሚሆን ቤት በብዛት መሥራት የሚያስችል ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም የለማ መሬትም ሆነ የግንባታ አቅምና የፋይናንስ አቅርቦት ሥርዓት ሳይዘረጋ ቆይቷል ከዚህም በተጨማሪ ይህንን ለመለወጥ የሚያስችል የፖሊሲ የተቋማዊ አቅምና እንዲሁም የከተማ ልማት ፖሊሲ የተጠቃሚዎችና የመንግሥት ቅንጅት ለመፍጠር ምቹ ሁኔታ አልነበረም ስለሆነም ሰፊ የቤት አጥረት ከማጋጠሙም በላይ አስከፊ የከተሞችና የመንደሮች እርጅና ተንሰራፍቶ ቆይቷል አዳዲስ ሕገ ወጥና ሕጋዊ ቤቶች በተሰሩበትም በርካታዎቹ የመሬት አጠቃቀም ሕግ ያልተከተሉ ሥርዓት የለሽና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሆነዋል መ በከተሞች የመዝናኛ ቦታዎች እጥረትና የአካባቢ ብክለት ችግር ሰፊ ነው በከተሞቻችን ሥርዓት ያለው የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ አረንጓዴ የተከለለ ቦታ በየአካባቢው በቂ መዝናኛ ማዕከላት የሌለው አከታተም ነው ሰፍኖ የቆየው አብዛኞቹ ከተሞች በርካኖ ያረጁ ሠፈሮች ያሉባቸው ሲሆኑ በርካታዎቹ ደግሞ ሠፈሮቻቸው አርጅተው ሕገወጥ ግንባታና ደረጃቸውን ያልጠበቁ አዳዲስ ቤቶችም ተስፋፍተውባቸው ሥርዓት ያጡና የተበከሉ ናቸው በአመለካከትና በአሠራር ደረጃም የቤት ግንባታና የአካባቢ ጥበቃን ሥርዓት የማስያዝ እንዲሁም በቂና ተገቢ መዝናኛና አረንጓዴ ቦታ እንዲኖር የማድረግ ትኩረት አልነበረም ይህም በመሆኑ ወጣቶችና ታዳጊዎች አልባሌ ቦታ ሊውሉ ተገደዋል ሠ የከተሞቻችን አከታተም ከገጠር ጋር የጠነከረ ትስስር ያለው አልነበረም የኢኮኖሚ ፖሊሲያችን ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት ማምጣት ነው ቢልም የገጠርና ከተማ ልማትን አስተሳስረን በሁለገብ መልኩ ልማትን የማፋጠንና አፈጻጸሙን በአግባቡ የመዘርዘር ችግር ነበረብን ከሁሉም በላይ ግን ባለፉት ሥርዓቶች ለገጠር ልማትም ይሁን ለገጠርና ከተማ ልማት ትስስር ተገቢ ፖሊሲና ተጨባጭ ሥራ ያልነበረ በመሆኑ ከተሞች በድህነት ተዘፍቀው ቆይተዋል ከተሞቻችን የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ማፅከል ሊሆኑ ይቅርና በአግባቡ የተደራጁና ያደጉ የገበያ ማዕከላት መሆንም ባለመቻላቸው የገጠሩን ልማት በማፋጠን የራሳቸውንና የሀገር ልማትን የሚያፋጥኑ የልማት ማዕፅከላት ሳይሆኑ ቆይተዋል ረ የከተሞቻችን ፅድገት ያልተመጣጠነና እርስ በርስ የማይመጋገብ ነበር በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች መካከል እንዲሁም ከክልል ክልል ያሉ ከተሞች የአድገት ልዩነት ሰፊ ነው አዲስ አበባ በሕዝብ ብዛት በኢኮኖሚ እድገትና በተቋማዊ አቅም ከሌለቹ በጣም የተሻለች ብትሆንም የአገልግሎት አቅርቦት ሥርዓት ያለመዘርጋት የከተማ እርጅናና የድህነት ስፋትም በአዲስ አበባ የከፋ ነው የአርሶ አደር አካባቢ ከተሞች ከአርብቶ አደርና ከፊል አርሶ አደር አካባቢ ከተሞች የጐላ ልዩነት ቢኖራቸውም ብቃት ባለው የከተማ ኘላንና ለከተማ ተፈላጊ በሆነ ሁለገብ ደንብና መመሪያ የሚመሩ ሥርዓት ያላቸው ከተሞች አልሆኑም ከዚህም በተጨማሪ ከተሞች በንግድ በተዛማጅ ኢንዱስትሪዎችና አልግሎቶች አርስ በርስ ያላቸው ትስስር ደካማ ሆኖ ከመቆየቱም በላይ የተመጣጠነና ያልተማከለ የአከታተም አቅጣጫ አልነበራቸውም ይህ ባለፉት ሥርዓቶች ሊኖር የማይችል ሲሆን የማይኖርበት ምክንያትም ለዚህ መሠረት የሚሆንና ገጠርና ግብርናን መሠረት ያደረገ እንዲሁም ሁሉንም አካባቢና መላውን የሀገራችን ሕዝቦች ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርግ የልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ ስላልነበራቸው ነው ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ ከተቀየሰ ወዲህም የልማት ሥራው ካለፉት ሥርዓቶች የተሻለ ቢሆንም በሚገባው ፍጥነትና ስፋት ተግባራዊ ማድረጉ ላይ አጥረቶች ስለነበሩ እመርታ ሳይታይ ቆይቷል የከተማ ልማት ፖሊሲ ስለሆነም ከነዚህ የልማት ችግሮች የመነጨ አስከፊ ድህነትና ኋላቀርነት በከተሞች ተንሠራፍቶ ከመቆየቱም በተጨማሪ ከተሞቻችን እድገታቸው ዘገምታዊ የከተማነት ሥርዓትና ገጽታ የጐደላቸው ሆነዋል በመሆኑም ከተሞች የአካባቢያቸው የልማት ማዕከል ያልሆኑ ሥራ አጥነትና ተመጽዋችነት የሠፈነባቸው ያረጁ ሠፈሮች የበዙባቸውና መሠረታዊ የነዋሪዎችን ፍላጉት ማሟላት ያልቻሉ ሆነው ቀርተዋል ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተጀመረው ተስፋ ሰጪ ጅምር የከተሞች ልማት ሥራ በመሠረታዊነት ችግሩን ይፈታ ዘንድ የተሟላ ፖሊሲ መቀየስ ያስፈልጋል ሀ ሒ የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከተሞች ባልተማከለ አስተዳደር መርህ መሠረት በፖለቲካ በአስተዳደርና በሀብት ክፍፍል በቂና ተገቢ ነጻነት አልነበራቸውም ከተሞቻችን የበላይ አካል ታዛዥና ቅርንጫፍ የሚያደርጋቸው ሕግና አሠራር የነበራቸው ሲሆን የከተማ ነዋሪዎች የሥልጣን ባለቤት የሆነበትና በሕግ ተለይቶ የተሰጠ ፖለቲካዊ ሥልጣን አልነበራቸውም ከደርግ ውድቀት በኋላ የተሻለ ጅምር ቢኖርም እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ በቂና ሁለገብ ነጻነት ለከተሞች አልተረጋገጠም ነበር ከተሞች መብትና ግዴታውን የሚያውቅ የተደራጀና ሲቪል ሕብረተሰብን የሚያጠናክር የዲሞክራሲ አመለከከትና ባህል ያልዳበረባቸው ነበሩ በመሆኑም የተለያየ ፀረ ድሞክራሲያዊና ኋላቀር አመለካከትና ባህል የሠፈነባቸው ሆነው ቆይተዋል ከተሞቻችን አሣታፊ ልማትና አስተዳደር አልነበራቸውም ልማትና መልካም አስተዳደርን በሚመለከቱ መሠረታዊ ጉዳዮች ሕዝቡን በየደረጃውና በቀጣይነት ፃዛሣብ በማመንጨት በውሣኔ አሰጣጥና በአፈፃፀም የሚያሳትፍና ተጠቃሚ የሚያደርግ አሳታፊ ልማትና አስተዳደር አልነበራቸውም ከተሞቻችን ልማታዊ ባለሃብትን በቀጣይነት የሚደግፍና የሚመራ አመለካከትና አሠራር የነበረው አመራር አላገኙም ከተሞች ግልጽነት ተጠያቂነት የሕግ የበላይነት የሚያረጋግጥ ቀልጣፋ የከተማ ቢሮክራሲና ብቃት የነበረው ፖለቲካዊ አመራር አልነበራቸውም የከተማ ልዩ ባህሪና ተልዕኮን ያገናዘበ ተገቢ የአደረጃጀትና አሠራር ሥርዓት እንዲሁም የሠለጠነ የሰው ኃይል አልነበራቸውም ከተሞቻችን የራሳቸውን ገቢ የማሰባሰብና የመጠቀም ሥልጣን አልነበራቸውም ከተሞች በገቢ አጦት ጠኔ የተዘፈቁና ትርጉም ያለው የራሳቸው ገቢ የሌላቸው ከመሆናቸው በላይ ሊያገኙ የሚችሉትንም ገቢ በአግባቡ የመሰብሰብና የማስፋት እንዲሁም የሚያገኙትን ገቢና ድጐማ በቁጠባ የመጠቀም አመለካከትም ሆነ ሥርዓት አልነበራቸውም በአጠቃላይ የነዚህ ችግሮች ድምር ውጤት የሆነ የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር እጦት በከተሞች ለዘመናት ተንሰራፍቶ ቆይቷል አሁንም ቢሆን ገና አስተማማኝና ሥር ነቀል ለውጥ ያመጡበት ደረጃ ላይ አልደረሱም በመሆኑም ይህንን የሚቀርፍ ፖሊሲ መቅረጽ የግድ ይላል የከተማ ልማት ፖሊሲ የፖሊሲው አስፈላጊነት ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱትን መሠረታዊ የከተሞቻችን ችግሮች ለመፍታት የከተማ ልማትንና መልካም አስተዳደርን ሁለገብ አቅጣጫ የሚቀይስ የከተማ ልማት ፖሊሲ ያስፈልጋል የከተማ ልማት በሁለገብ መልኩ በምን አቅጣጫና ኖንዴት እንደሚካሄድ የሚወስን ፖሊሲ አለመኖር የችግሮቹ አንዱ ምንጭ በመሆኑ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያስችልና ከተሞች በሀገር ልማትና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚኖራቸውን ሚና የሚያስቀምጥ ፈጣንና ፍትሐዊ ልማት በከተሞች እንዴት እንደሚረጋገጥ የሚቀይስ ይህንን ተግባራዊ የሚያደርግ መልካም አስተዳደር ምን መሆን እንዳለበት የሚጠቁም የከተማ ልማት ፖሊሲ መቅረጽ ተገቢ ይሆናል በመሆኑም ይህ የከተማ ልማት ፖሊሲ ሠነድ የከተሞችን አጠቃላይ ሚና የሚጠቁም ያልተማከለና የተመጣጠነ አከታተምንና የገጠርና የከተማ እንዲሁም የከተማና ከተማ ትስስርን የሚያሳይ አቅጣጫ የያዘ ሆኖ ተቀርዷል የከተሞች ፈጣን ልማት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት በመሬት ልማት በቤት ልማት በመሠረተ ልማት በማህበራዊ አገልግሎትና በአካባቢ ልማት እንዴት እንደሚረጋገጥ ይቀይሳል የከተማ ኘላንን መሠረታዊ ይዘትና ጠቀሜታ ይጠቁማል የከተማ አስተዳደር እንዴት ልማታዊ አስተዳደር እንደሚሆንና መልካም አስተዳደር እንደሚያሰፍን አቅጣጫ ያስቀምጣል በዚህም መሠረት በከተሞች አሳታፊ ልማትና ቀልጣፋ ግልጽና ተጠያቂ አስተዳደር እንዴት እንደሚረጋገጥ ከመጠቆሙም በተጨማሪ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር የማስፈን እንዲሁም ልማኖ ዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥትና ሲቪል ማህበረሰብ የማጠናከር አቅጣጫ ቀይሳል የከተማ ልማት ፖሊሲ ክፍል ሁለት የፖሊሲው ራዕይ ዓላማ መነሻና መርሆዎች ራዕይ ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ልማትና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያረጋግጡ ለኑሮ አመቺና በኘላን የሚመሩ እንዲሆኑ በማድረግ የአካባቢያቸው የልማት ማዕከልና የዲሞክራሲ ተምሣሌት ሆነው ኖርስ በርስ ተሳስረውና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን በማረጋገጥ በልጽገው ማየት ዓላማ ከተሞች የልማት ማፅከል በመሆን ለገጠር ልማትና ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት የጐላ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ለማስቻል እና የከተማ ነዋሪዎች የሥልጣን ባለቤትና የልማት ተጠቃሚ በመሆን መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገሮች ሕዝቦች የደረሱበት የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ለማስቻል ናቸው የፖሊሲው መነሻዎች ፌዴራላዊ ሥርዓት የሀገራችን ፖለቲካዊ ሥርዓት ፌዴራላዊ በመሆኑ አከታተማችን በርካታ አውራ ከተሞችን የሚፈጥር ባልተማከለ አስተዳደር መርህ መሠረት ለከተሞች ሰፊ ሥልጣን የሚሰጥና ክልሎች ከተሞቻቸውን የመምራት ሰፊ ሥልጣን እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ይሆናል የልማት ስትራቴጂያችን ሀ የገጠርና ከተማ ልማት ትሥሥር የገጠር ልማት ለከተማ ልማት መሠረት በመሆን የከተማ ልማትን አቅጣጫና ፍጥነት ይወስናል ምክንያቱም የከተማ የኢንዱስትሪ የአገልግሎትና የገበያ እድገት መሠረቱ የገጠር ጉልበት የግብርና ምርትና የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ ነው በአንጻሩ ደግሞ የገጠር ልማት ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን በማድረግ በኩል ከተሞች ምትክ የለሽ ሚና አላቸው ምክንያቱም የገጠሩን ምርትና ትርፍ ጉልበት የሚቀበሉ የገበያና የኢንዱስትሪ ማዕከል የሚሆኑ እንዲሁም ለገጠሩም ለከተማውም ተፈላጊ አገልግሎት የሚያቀርቡ የአካባቢው የልማት ማዕከላት ከተሞች በመሆናቸው ነው ስለሆነም ይህንን መሠረት በማድረግ ፖሊሲው የከተማና ገጠር ተመጋጋቢነትንና ትስስርን የሚያጠናክር የሁለቱንም ተደጋጋፊ እድገትና ምትክ የለሽ ሚና የሚያጐለብት አቅጣጫ ቀይሷል የልማት ስትራቴጂያችን በመላው ሀገራችን የተመጣጠነ ልማት የሚያረጋግጥ በሁለም የሀገራችን አካባቢዎች የሚገኝ ጉልበትና የተፈጥሮ ሀብት በተለይም መሬትን አሟጦና ቆጥቦ በመጠቀም ሁሉንም አካባቢ የሚያለማ ስለሆነ በየአካባቢው የልማት ማዕከል የሚሆኑ ከተሞች የከተማ ልማት ፖሊሲ መፍጠርን የግድ ይላል ስለሆነም ለተመጣጠነና ያልተማከለ አከታተም መሠረት ይሆናል በመሆኑም ፖሊሲው ይህን የልማት ስትራቴጂያችንን መሠረት ያደረገ የተመጣጠነና ያልተማከለ አከታተም አቅጣጫን ቀይሷል ለ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂያችን የልማት ስትራቴጂአችንን መሠረት ያደረገው የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂያችን አበይት ከተሞችን የኢንዱስትሪ ማዕከል የሚያደርግና ትናንሽ ከተሞችም ሳይቀሩ የአካባቢውን የግብርና ምርትና ትርፍ ጉልበት በመጠቀም የግብርና ኢንዱስትሪ ማዕከላት አንዲሆኑ የሚያስችል አቅጣጫ ቀይሷል የከተማ ልማት ፖሊሲው ይህን መነሻ በማድረግ አበይት ከተሞች የአካባቢያቸው ምርት የተፈጥሮ ዛብትና ትርፍ ጉልበትን በመጠቀም የኢንዱስትሪ እና የልማት ማዕከል የመሆን ሚና የሚጫወቱበትን መንገድ ቀይሷል በተለይም መካከለኛና አውራ ከተሞች ለኢንዱስትሪ እድገት ተፈላጊ የሆነ ልማታዊ ባለፃብትና የሠለጠነ የሰው ኃይል እንዲሁም በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪ የሆነ መሠረተ ልማትና አገልግሎት የሚያቀርቡበትን መንገድ ይጠቁማል በአጠቃላይ የከተማ ልማት ፖሊሲያችን መነሻ ፃዛሣቦች በፖለቲካው መስክ ሀገራችን የምትከተለው ፌዴራላዊና ያልተማከለ አስተዳደር እንዲሁም በልማቱ መስክ የገጠርና ኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂዎቻችን ናቸው በመሆኑም ፖሊሲው ያልተማከለ አስተዳደርን በማጠናከርና የልማት ስትራቴጂዎቻችንን በማሳካት በኩል ጉልህ ሚና ያለው ከመሆኑም በላይ ከተሞቻችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማትን እንዲያረጋግጡ ያስችላል መርሆዎች ሀ ከተማና ገጠር እንዲሁም ከተሞች እርስ በርሣቸው ተመጋጋቢ በሆነና በቀጣይ ትስስር እንዲያድጉ ማድረግ ለ የተመጣጠነ የከተሞች እድገትን በመፍጠር የሁሉንም ከተሞች የእድገት ዕድል ማስፋት ሐ ያልተማከለ አከታተምን በማረጋገጥ በየደረጃው የተለያየ ኢኮኖሚያዊ ሚና ያላቸውን ከተሞች ተመጋጋቢ ሆነው እንዲያድጉ ማድረግ መ የከተማ ልማት ሥራ ማዕከሉ ድህነትን መቀነስ ብሎም ማስወገድ እንዲሆን ማድረግ ሠ ሕዝቡን በለማት ሥራ በሰፊው ማሳተፍ እና የልማቱ ባለቤት እንዲሁም ተጠቃሚ ማድረግ ሰፊና ቀጣይ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሕዝባዊ ንቅናቄ አንዲኖር ማድረግ በሕዝቡ ፍላጐትና አቅም ላይ የተመሠረተና በመንግሥት አመራርና ተሳትፎ በቅንጅት የሚካሄድ ልማት ማጠናከር ረ ከልማታዊ ባለሀብት ጋር ጠንካራ አጋርነት መፍጠር ሲ ያልተማከለ አስተዳደር በመዘርጋት ከተሞች ራሳቸውን የማስተዳደር ሰፊ ነጻነትና ሥልጣን እንዲኖራቸው ማስቻል የከተማ ልማት ፖሊሲ ክፍል ሦስት የከተሞች ሚና ለሀገራችን ልማትና ዲሞክራሲ የከተሞች ሚና ለሀገር ልማት ከተሞች የገጠር ልማትን የማፋጠን ምትክ የለሽ ሚና አላቸው የከተሞች ልማት አቅጣጫና ፍጥነት በገጠር ልማት የሚወሰን ቢሆንም ከተሞች የገበያ የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ማዕከል ሆነው ማደግ ካልቻሉ የገጠር ልማቱ መገታቱ አይቀርም ስለሆነም ከተሞች ይህን ሚና እንዲጫወቱ በማብቃት የገጠር ልማቱን ፍጥነትና ቀጣይነት እንዲያረጋግጡ ማድረግ ይቻላል ከተሞች የገበያ ማዕከል ይሆናሉ ከገጠር ከሌሎች ከተሞችና ከውጭ ሀገር የሚመጡና ወደእነዚህ አካባቢዎች የሚላኩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም የሌሎች ሸቀጦች ግብይት የሚደረገው በከተሞች ነው ከተሞች ለግብይት የሚያመች ብቃት ያለው መሠረተ ልማት የተለያየ አገልግሎትና ተቋማት እንዲኖራቸው ከተደረገ ይህንን የገበያ ማዕከልነት ሚና ይጫወታሉ ከዚህም በተጨማሪ ግብርናን ከኢንዱስትሪና ከአገልግሎት ጋር ከዛም አልፎ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን ኖርስ በርስ ያስተሳስራሉ ከተሞች የአገልግሎት ማዕከል ይሆናሉ መካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው አገልግሎቶች ለገጠርም ሆነ ለከተማ ሊያገለግሉ በሚያስችል መንገድ በከተሞች እንደሚያድጉ ይታወቃል የከተሞች እድገት በዚህ መንገድ ከተመራ አገልግሎቶች ከተሞችን ብቻ ሳይሆን የገጠሩን ሕዝብ ያገለግላሉ የገጠር አገልግሎቶችን ይደግፋሉ ከተሞች በብቁ አገልግሎታቸው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላሉ ከተሞች የኢንዱስትሪ ማዕከል ይሆናሉ የግብርና ኢንዱስትሪዎችም ሆነ ሌሎች ዘመናዊ ኢንዱስትሪዎች የሚስፋፉት በከተሞች ነው የግብርና ምርትና የተፈጥሮ ሀብት የኢንዱስትሪ ግብአት በመሆን አሴት እንዲጨምሩና የሀገር ኢንዱስትሪያዊ እድገት እንዲያፋጥኑ ምቹ ሁኔታ የሚፈጠረውም በከተሞች ነው ከዚህም በተጨማሪ ለኢንዱስትሪ አድገት ተፈላጊ መሠረተ ልማት አገልግሎትና የሠለጠነ የሰው ኃይል የሚያቀርቡት ከተሞች ናቸው የከተሞች ሚና በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባኖ የከተሞች እድገት የሕዝቦች ትሥሥርን ያጠናክራል ከተሞች ሲያድጉ ገጠርና ከተማን እንዲሁም ከተማና ከተማን ይበልጥ በማስተሳሰር በገጠርና በትናንሽ ከተሞች ያለውን ሕዝብ ያሰባስባሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስርንም ያጠናክራሉ ከአርሶ አደር የከተማ ልማት ፖሊሲ ኢኮኖሚ ወደ ዳበረ የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ኢኮኖሚ መሸጋገሪያ ማዕከላት በመሆን የሕዝቦች የጥቅም ትስስርን ያጠናክራሉ ስለሆነም ከተሞች የሕዝቦች ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ትስስር በመፍጠር ለጠንካራ ሕዝባዊ አንድነት መሠረት ይሆናሉ ከተሞች የዲሞክራሲ ተምሣሌት ይሆናሉ ከገጠር ይልቅ በከተሞች የዲሞክራሲ ባህልና አስተሳሰቦች የዲሞክራሲ ተቋማት የተሻለ ብዛትና ጥንካሬ ያላቸው ፖርቲዎችና መገናኛ ብዙኃን በብዛትና በፍጥነት ያብባሉ በመሆኑም ከተሞች የዲሞክራሲያዊና ሳይንሳዊ አስተሳሰብና ባህል የምርምርና የኪነጥበብ ማዕከላት በመሆን ያገለግላሉ ከተሞች ሲያድጉ ጠንካራ የዲሞክራሲና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ይፈጥራሉ ዲሞክራሲ በተበተነ የአርሶ አደር ኢኮኖሚ ከሚኖረው ጥንካሬና ዋስትና በዓይነቱ የተሻለ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ መሠረት የሚኖረው በከተሞች በሚፈጠር የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚ ነው በዚህ ሁኔኖ ዲሞክራሲን የሚያጐለብት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ይዳብራል የተማረ በቀላሉ ሊደራጅ የሚችል የሠለጠነ ሕዝብ ይበዛል ሕዝቡም መብትና ግዴታውን የሚያውቅ ይሆናል ስለሆነም በከተሞች ሕዝቡ ለሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ዘብ ለመቆም የተሻለ አቅም ይኖረዋል የከተማ ልማት ፖሊሲ ክፍል አራት ፋ ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት በከተሞች በአገራችን የከተሞች ልማት ፈጣን የሚሆነው የገጠር ልማትን መሠረት በማድረግ የገጠርና ከተማ አንዲሁም የከተማና ከተማ ትስስርን በማጠናከር ከተሞች በቀጣይነት የገበያ የአገልግሎትና የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆን ሲችሉ ብቻ ነውፊ ይህን ለማሳካት የሚያስችሉ የከተማ ልማት ዓበይት ሥራዎች አሉ እነሱም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማስፋፋት የቤት ልማት የሕዝብና የመልካም አስተዳደር አቅም ያቀናጀ የቀበሌ ልማት የመሬትና የመሠረተ ልማት አቅርቦት የትምህርትና ሥልጠና መስፋፋት የጤናና የመዝናኛ አገልግሎት መስፋፋት የኢንዱስትሪ ልማት የአካባቢ ጥበቃና የከተማ ኘላን ሥራዎች ናቸው ፈጣንና ፍትዛዊ ልማት በከተሞች ለማምጣትም እነዚህ ሥራዎች በተናጠል ሳይሆን በቅንጅት መሰራት ይኖርባቸዋል ለዚህም በፌዴራልና በክልል መንግሥታት የሚሰሩ አበይት የልማት ሥራዎችና በባለሀብቱ የሚሰሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው ከነዚህ ጋር የተቀናጁና በከተማ አስተዳደርና በከተማ ነዋሪዎች የሚሰሩ ሥራዎችን ማጠናከር የከተማ አስተደደሩ ዋነኛ ተልእኮ ይሆናል የከተማ ልማት ፈጣን ብቻ ሳይሆን ፍትሐዊና ቀጣይ እንዲሆንና አብዛኛውን የሕብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት ማእከል ያደረገ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከተማ ነዋሪዎች የሥራ እድልና የራሳቸው ቤት እንዲኖራቸው ትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም መከላከልን መሠረት የሚያደርግ መሠረታዊ የጤና አገልግሎት እንዲደርሳቸው የሚያስችል መሆን ይኖርበታል የመጠጥ ውዛመንገድመብራትና ቴሌም ደረጃ በደረጃ እንዲያገኙና የሀብታም እና የድሀ መኖሪያ ሳይለያይ በጋራ ተቀላቅለው መሠረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት በመጋራት የሚኖሩበት ሁኔታ የሚፈጥር ልማት መሆን አለበት በአጠቃላይ ተራው ሕዝብ የበይ ተመልካች ሳይሆን በቀጣይነት የሚያድግ ገቢና ንብረት ያለው እንዲሆን የሚያስችል ልማታዊ ባለሃብቱም ብቁ ተወዳዳሪ እየሆነ እንዲያድግ የሚረዳ መሆን አለበትሱ ይህን ለማሳካት የከተማ አስተዳደሮች ልማትን በመምራት በኩል ዋነኛ ትኩረት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት የከተማ መሬት አቅርቦትና አጠቃቀም በፕላን እና በልማታዊ መንገድ አንዲመራ ማድረግ የቁጠባ ቤት ማስፋፋትን ማእከሉ ያደረገ የቤት ልማትን ማፋጠንና ከባለሃብቱ ጋር በአጋርነት መሥራት አንዲሁም ሕዝቡን በተደራጀ መንገድ በቀጣይነት የልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን መምራት ይሆናል ፈ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት የከተማ ልማት ሥራችን ማዕከሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት መሆን ይኖርበናኖ ል ምክንያቱም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለከተማ ድህነት ቅነሳና ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣት ቁልፍ ሚና ስላላቸው እንዲሁም የአብዛኛውን ነዋሪ ተጠቃሚነት ስለሚያረጋግጡ ነው እንዲሁም ገጠርና ከተማን በኢኮኖሚ ለማስተሳሰር ልማታዊ ባለሃብትን እና የነገ የከተማ ልማት ፖሊሲ ኢንዲስትሪያሊስቶችን ለማፍራት የጐላ ሚና ስላላቸው ነው የከተማ ኢኮኖሚያዊ ትስስርንም ያጠናክራሉ ፋ ባለቤትና አስተባባሪ ሆኖ ድጋፍና አመራር የሚሰጥ ጠንካራ የአስተዳደሩ ፈፃሚ ተቋም መፍጠር ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጥ ልማታዊ ድጋፍና አመራር ሁለገብ ሆኖ ሁሉንም ችግሮቻቸውን ለይቶና አስተሳስሮ በአንድ ማእከል በቀጣይነት የሚፈታ መሆን አለበት አደረጀጀቱ እንደየአካባቢው የሚለያይ ይሆናል ይህን ሁለገብ የአንድ ማአከል ድጋፍ የሚሰጥና የሚያስተባብር ከፌዴራል እስከ ከተማ የተዘረጋው የአስተዳደሩ ፈፃሚ አካል በአግባቡ የተደራጀና አቅም ያለው መሆን ይኖርበኖ ል ፈፃሚ ተቋሙ ራሱ የሚሰጠውን ድጋፍ በቀጥታ እየሰጠ ሌሎች የሚሰጡትን ደግሞ እያስተባበረ የተሳካ ቀጣይ ድጋፍና አመራር እንዲሰጥ የሚያስችለው አደረጃጀት የሰለጠነ የሰው ኃይልዝርዝር የአሰራር መመሪያ ሊኖረው ይገባል በሂደትም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚታገዝ መሆን አለበት ተጠቃሚዎቹም ችግራቸውን በሚገባ ለመለየትና ተባብረውም ለመፍታት የሚረዳቸው የራሳቸው አደረጃደት በጋራ እና በየሥራ ዘርፋቸው በመፍጠር ከአስተዳደሩ ጋር በቅንጅት በማቀድና በመፈፀም ሊንቀሳቀሱ ይገባል ይህም በራሳቸው ፍላጐትና አቅም የተመሠረተ እና በነሱ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚፈፀም መሆን አለበት በተለይም ተቋማቱን የማስፋፋትና ተወዳዳሪ የማድረግ ወሳኝ ሚና የተጠቃሚዎች የራሳቸው ኃላፊነት መሆን ይኖርበኖ ል ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በተደራጀና ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚሰጥ የመንግሥት አመራርና ድጋፍ በገበያ ሕግጋት የሚመራና ተወዳዳሪነትን በሚያረጋግጥ እንዲሁም በልማታዊ መንገድ የሚፈፀም ይሆናል ዓላማውም ተቋማቱ በቀጣይነት በቁጥር እንዲበዙአዳዲሶች እንዲስፋፉ ነባሮች እንዲጠናከሩና በውድድር ጠንክረው የወጡትም ወደ ታዳጊ መካከለኛ ተቋማት እንዲሸጋገሩ ማድረግ ይሆናል የገበያ ችግራቸውን መፍታት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ትርፋማ ሆነው በቀጣይነት ሊያድጉ የሚችሉት በገበያ ተፈላጊ የሆነ ምርትና አገልግሎት በተወዳዳሪ ጥራትና ዋጋ በማቅረብ በሂደትም ብቁ ተወዳዳሪ መሆን ሲችሉ ብቻ ነው የመንግሥት ድጋፍ ዓላማም ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ስለሆነ የገበያ ችግራቸውን በሚከተሉት ድጋፎች መፍታት ከፌዴራል እስከ ከተሞች የተደራጀው የመንግስትና በየደረጃው ያለው የአስተዳደሩ ሚና ይሆናል ሀ በመንግሥት የልማት ሥራዎች ምርትና አገልግሎት አቅራቢ በመሆን እንዲሣተፉ ማስቻል ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከመንግሥት የልማት ሥራዎች ተጠቃሚ በመሆን ተወዳዳሪ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ እንዲችሉ በቅድሚያ ከፍያ በቀጥኖ ኮንትራትና በመሳሰሉት መንገዶች የገበያ ዕድል እና ቅድሚያ እንዲያገኙ ይደረጋል የከተማ ልማት ፖሊሲ ለሊ ከትልልቅ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር የአቅራቢነት ኮንትራት ትስስር እንዲፈጥሩ ማመቻቸት በጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት የሚቀርበውን ምርትና አገልግሎት መግዛት የሚችሉ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎችን በማፈላለግ ኩባንያዎች የሚፈልጉትን ምርት በተፈለገው መጠን ጥራትና ዋጋ እንዲያቀርቡላቸው የኮንትራት ሰምምነት እንዲያገኙ ማመቻቸት የአስተዳደሩ ሚና ይሆናልፊ በመሆኑም ኩባንያዎችን አፈላልጐ የማግኘትና የሚፈልጉትን የምርት ጥራት ደረጃና ዋጋ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በማሣወቅ ተቋማቱ በዚያው መሠረት ሠርተው እንዲያቀርቡ የማስማማት ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል ለኮንትራት አፈፃፀሙ ድጋፍ በመሰጠትና በሳብ ኮንትራት በማስተሳሰር ገበያቸውን ለማስፋት በሙያ ስልጠና እና በሎጅስቲክስ መደገፍ ይገባል ሔ ከውጭ ሀገር ኩባንያዎች ጋር በማስተሳሰር የውጭ ገበያ እንዲያገኙ ማገዝ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምርትን ሊገዙ የሚችሉ የውጭ ኩባንያዎችን ወይም የአነሱ ሸሪኮችን በማፈላለግና የሚፈልጉትን የምርት ዓይነት ጥራትና ዋጋም በማወቅ ከተቋማቱ ጋር የማስተሳሰር ድጋፍ መስጠት ያሰፈልጋል በተለይም ወደ ውጭ ገበያ መግባት ከባድ ስለሚሆን ገዥዎችን ፈልጐ ማግኘትና ተፈላጊውን ጊዜ ጥራትና ዋጋ ያሟላ ምርት የማቅረብ አቅም መፍጠር ሊቀናጅ ይገባል ለዚህም ወደ ውጭ ገበያ ለመግባት ሲባል መደረግ ያለበት የተለያየ የድጐማ ድጋፍም በተወሰነ ጊዜ እንደመሸጋገሪያ ማቅረብ ተገቢ ይሆናል በኮንትራት አፈፃፀም በመደገፍና በሳብ ኮንትራት በማስተሳሰር ማጠናከር ይገባል የገበያ መረጃ በአንድ ማዕከል እንዲያገኙና ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ ማመቻቸት ወቅታዊና ቀጣይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ገበያ መረጃ እንዲያገኙ ምርታቸውንም በኤግዚቢሽንና በተለያየ የማስተዋወቅ ዘዴ እንዲያስተዋውቁ ቀጣይነት ያለው እገዛ ማድረግ ተገቢ ይሆናል መሸጫ ቦታ እንዲያገኙ ማመቻቸት ደረጃውን የጠበቀ የመሸጫ እና የማምረቻ ቦታ ሰርቶ በማከራየት ተደራጅተውም ሆነ በተናጠል እንዲሰሩ በማገዝና በማበረታታት የመሸጫ ቦታ እና ማምረቻ ችግራቸውን መቅረፍ ተገቢ ይሆናል የአመራርና የክህሎት ችግራቸውን መፍታት የአመራር የኢንተርፕርነርሽፕና የሙያ ክህሎት ሥልጠናን የሚያስተሳስርና የሚያስፈጽም እንዲሁም ብቃት ባላቸው ባለሙያዎችና በዝርዝር መመሪያ በአግባቡ የተደራጀ የኢንዱስትሪ የኤክስቴንሽን ሥርዓት መዘርጋት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና እንዲሁም የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከላትን በማስፋፋት ዋናው ሥራቸው የሰለጠነና ሥራ ፈጣሪ የሰው ኃይል በቀጣይ ማፍራትና የቴክኖሎጂ ማሻሻል ሥራ የከተማ ልማት ፖሊሲ ሒ ሒ ማካሄድ እንዲሆን ማድረግና በዚህም ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት መስፋፋት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን የሚሰጡበት ሥርዓት ዘርግተው እንዲተገብሩ ማስቻል ለአዲስ ሠልጣኞች ከሚሰጥ መደበኛ ሥልጠና በተጨማሪ በየጊዜውና በቀጣይነት የኢንተርፕርነርሽፕ የአመራርና የክህሎት ሥልጠና መሰጠት እንዲሁም ነባር የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ባለቤቶችና ሠራተኞች የማያቋረጥ አጫጭር የተግባር ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ይህን ለማድረግ የሚያስችልም የሥርዓተ ትምህርት የማስተማሪያ መሣሪያና ብቃት ያላቸው አሠልጣኞች በማሠልጠኛ ማዕከላቱ እንዲኖሩ እና የኢንዱስትሪ የኤክስቴንሽን ሥርዓቱ ውጤትን መሠረት ባደረገ መልኩ እንዲፈጽም ማጠናከር ሥልጠናዎች በዝርዝር ጥናት ላይ ተመስርተው ተጨባጭና የየወቅቱን የአመራርና የክህሎት ችግር በመለየት ፍላጐት መርና ችግር ፈቺ አንዲሆኑ ማድረግ ይህን ማድረግ የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የፍላጐት ጥናትና የሥልጠና ይዘትና ስልት ለውጥ በማድረግ መተግበር ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት እርስ በርሰ እንዲማማሩና የተቀናጀ ሥልጠና እንዲያገኙ ያመች ዘንድ በየአካባቢው በሚዘጋጅላቸው ወይም አራሣቸው በሚሠሩት የማምረቻ ቦታ እንዲሰባሰቡ ማድረግ በሥልጠና ረገድ ለተሰባሰቡት ቅድሚያ መስጠት የካይዘን አሰራር እየተገበሩ በጥራትና በምርታማነት ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲያስመዘግቡ ማድረግ ለቀጣይ መሻሻል የሰራዊት ግንባታ ሥርዓቱን በመከተል ማስፈጸም በሥራ የጀማሪ ልምምድ አፐረንቲስሽኘ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እነዚህን አሠራሮች አጠናክሮ ተግባራዊ ማድረግ የፋይናንስ ችግራቸው እንዲፈቱ ማገዝ ለቀጣይ ብድርና ቀጣይነት ላለው ዕድገት የቁጠባ ባሕል እንዲያደብሩ ማደራጀት ማበረታታት ለአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ዝቅተኛ ብድር የሚሰጡ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት እንዲስፋፉ ማገዝ በአስተዳደሩም ሆነ በሌሎች እንዲመሠረቱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የማምረቻና የአገልግሎት መሣሪያ የሚያከራዩና በረዥም ጊዜ ክፍያ የሚሸጡ ኩባንያዎች እንዲመሠረቱ ማበረታታት እንዴት እንደሚደራጁና እንደሚደገፉ ደንብና መመሪያ ማውጣት የሙያ ብቃት ምስክር ወረቀት ላገኙና ተወዳዳሪነታቸውን በተግባር ላሳዩ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የብድር ዋስትና የሚሰጡ የከተማ አስተዳደር ወይም የክልል ልዩ ፈንድ ማቋቋም አበረታች የቅድመ ክፍያ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ የፋይናንስ ችግራቸውን ማቃለል የከተማ ልማት ፖሊሲ የማምረቻ ቦታና የመሠረተ ልማት ችግራቸውን መፍታት ሀ በቂ የመሠረተ ልማት አቅርቦት ያለው መሬት በማዘጋጀትና ከዚህ ውስጥ ቅድሚያ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ማምረቻ ቦታ የሚሆን በመለየት በተመጣጣኝ ዋጋ ለተቋማቱ ማከራየት ለ በተዘጋጀው መሬት ላይ አቅም በፈቀደ መጠን ማምረቻ የሚሆን ቤት ከነመሠረተ ልማቱ ሠርቶ አስተዳደሩ እንዲያከራያቸው ማድረግ ወይም የለማ መሬት ተከራይተው ራሣቸው በተፈለገው አማራጭ ዲዛይን ደረጃውን ጠብቀው እንዲሠሩ ማመቻቸት ሒ በእንደዚህ ዓይነት የማምረቻ ቦታ ተመሣሣይ ሥራ የሚሠሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተሰባስበው በስልጠና በብድርና በመሣርያ አገልግሎት ቅድምያ እንዲያገኙ በማድረግ ማበረታታት በመካከላቸው ሁለንተናዊ መደጋገፍ እንዲኖር ማስተባበር መ በአንድ ላይ መሰባሰብ ለማይችሉት ደግሞ በየቀበሌውና በየመንደሩ እንደ አመቺነቱ በተናጠል ኪስ ቦታ በመሰጠት በኪራይ እንዲጠቀሙበት ማድረግ ፋ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የመስሪያ ማሽን ያላቸው የክላስተር ማዕከላት ማደራጀት ሀ ለጀማሪዎች የኢንተርፕርነርሽፕ የአመራርና የሙያ ክህሎት ተግባራዊ ሥልጠና በመስጠትና የሙያ ብቃት በማረጋገጥ ራሣቸውን የሚችሉበት ደረጃ ላይ የሚያደርሰ ማዕከል አቅም በፈቀደ መጠን በተለይም በአበይትና በመካከለኛ ከተሞች መመሥረት ለሌ በነዚህ ማዕከላት አሰፈላጊውን መሣሪያና አሠልጣኝ በማቅረብ ሠልጣኞች የአገልግሎት ክፍያ ከፍለው የማሽን አገልግሎት የመስሪያ ቦታና ሥልጠናውን እንዲያገኙ ና በተግባር ሠርተው ፃብት ኖያፈሩና እየሸጡ ብቁ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ ማድረግ ሔ እነዚህ ማፅከላት በክልል መንግሥት ወይም በከተማ አስተዳደርና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ባለቤትነት በሚቋቋሙ ኩባንያዎች አማካይነት ሊተዳደሩና ሊለሙ ይችላሉ ዓላማቸው ትርፍ ማካበት ሣይሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን ማሰፋፋት ብቁ ተወዳዳሪ ማድረግ ብሎም ልማትን ማፋጠን ይሆናል ሲጠቃለል ፈጣን ቀጣይና ፍትሐዊ የከተማ ልማት የሚረጋገጠው ገጠርና ግብርናን መሠረት በማድረግ ከሱ ጋር ተመጋጋቢ ሆኖ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት ማስፋፋትን ማዕከሉ ያደረገ ሁለገብ የከተማ ልማት በማካሄድ ነው ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት እንዲስፋፉና ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በተለይም የከተማ አስተዳደሮች ለተቋማቱ ሁለገብና የተቀናጀ ድጋፍ መስጠት ይኖርባቸዋል ይህም ተግባራዊ የሚሆነው ሁለገብ ድጋፉን ባለቤትና አስተባባሪ ሆኖ የሚያሰፈጽም የአስተዳደሩ ፈጻሚ ተቋም ሲጠናከር የተቀናጀ ገበያ የማፈላለግ የሥልጠና የፋይናንስ የማምረቻ ቦታ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያና የተቋማቱ የመስሪያ ማሽን ያላቸው የክላስተር ማዕከላትን በማደራጀት ሁለገብ ጥረትና ድጋፍ በመሰጠት ነው ይህንኑ ለማስፈጸም የዘርፉ ዝርዝር ስትራቴጂ ወጥቶ ይተገበራል የከተማ ልማት ፖሊሲ የመሬት አቅርቦት ማመቻቸት የመሬት ፓሊሲ የመሬት ፓሊሲያችን በገጠርም ሆነ በከተማ መሬት የመንግሥት እና የሕዝብ ሆኖ የከተማ መሬትን ተከራይቶ ለተወሰነ ጊዜ የመጠቀም መብትን ያረጋግጣል በዚህ መሠረት መሬት የመንግሥትና የሕዝብ በመሆኑ ለሕዝብ ጥቅም ተፈላጊ የሆነውን መሬት መንግሥት በእጁ በማቆየት ጥቅም ላይ አንዲያውል በተጠቃሚዎች የተያዘ ከሆነም ለተጠቃሚዎች የንብረት ካሣ በመክፈልና በመረከብ የተሻለ ልማት እንዲሰራበት ያስችለዋል ከዚህም በተጨማሪም ፓሊሲው የመሬትንና የቤት ዋጋን ለማረጋጋት እንዲሁም በፍትሐዊ መንገድ ለሀብታሙና ለድሀው ለማዳረስ ይረዳል የከተማ መሬትን በተመጣጣኝ ዋጋና በረዥም ጊዜ ክፍያ ለተጠቃሚዎች ማከራየት ተጠቃሚው መሬት ለመግዛት በአንዴ ብዙ ገንዘብ ወጪ እንዳያደርግና በዚህ ሂደትም የሚያድነውን ገንዘብ ለሌላ ልማት ለማዋል እንዲችል ይረዳል ይህም ለፈጣን ልማታችን የጐላ አስተዋጽኦ ይኖረዋል የተረጋጋ የመሬት ዋጋና የንብረት ግብይትን ይፈጥራል መሬትን በቁጠባ ለተፈላጊ ልማት በማዋልና ፍትሐዊ የመሬትና የቤት ባለቤትነት በማረጋገጥ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚው ፈጣን ቀጣይና ፍትሐዊ እድገት እንዲያረያግጥ ያስችላል በሀገራችን የተጀመረው ፈጣን ተከታታይና ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርገው የኢኮኖሚ ልማት መሠረት እንዲኖረው ያደርጋል የተዓጓተተውን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት በፍጥነት ለማስፈጸም የመሬት በሕዝብና በመንግስት ባለቤትነት መቆየቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል በአጠቃላይ በአግባቡ የተጠናከረ ፈፃሚ አቅም በመፍጠርና ስለጠቀሜታውና አፈፃፀሙ ከሕዝብ ጋር ተገቢ መግባባት በማረጋገጥ ከተፈፀመ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፓሊሲ የከተማ ልማት ሥራችንን ማፋጠን ብቻ ሳይሆን ለነፃ ገበያ እድገትም መሣሪያ በመሆን ያገለግላል የመሬት አቅርቦት መርሆዎች የከተማ መሬት በጣም ቁልፍ ግን ውሱን ሀብት ስለሆነ በመሬት አጠቃቀም ፕላን መሠረትና በቁጠባ መጠቀም ይኖርብናል ስለሆነም የከተማ መሬትን በከተማ ኘላን መሠረት ለተፈላጊው አገልግሎት በቅደም ተከተል መጠቀም የመሬት አቅርቦት በቅድሚያ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ልማትን በሚያፋጥንና በተረጋጋ ዋጋ በቀጣይና ቀልጣፋ የአቅርቦት ሥርዓት መፈፀም የቤቶችና የመንደሮችን መተፋፈግ የሚያስወግድ አንዲሁም ለመኖሪያ ለሥራና ለመዝናኛ የሚሆን ቦታ አመጣጥኖና አቀናጅቶ ማቅረብ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በቂ መሬት ለመኖሪያና ለመስሪያ የሚሆን የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት የከተማ ልማት ፖሊሲ ባለሃብቶች የመኖሪያና የመሥሪያ ቤቶችን ሰርተው በኪራይም ይሁን በሽያጭ እንዲያቀርቡ መሬት በተቀላጠፈና ቀጣይነት ባለው መንገድ በጨረታ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት በሚያሰፍን መንገድ እንዲያገኙ ማድረግ የመሬትና የቤት አጠቃቀሙንም ጨምሮ ምዝገባ እንዲሁም የባለቤትነት ማረጋገጫና የንብረት ግብይት ሥርዓት መፍጠር ለመኖሪያና ለመሥሪያ ቦኖ የሚቀርብ መሬት በቅድሚያ በተቀናጀ መንገድ መሠረተ ልማት የተሟላለት እንዲሆን ማድረግ የመሬት አቅርቦት ቅደም ተከተል የከተማ መሬት ዓይነትና መጠን የሚገኝበት አካባቢ ለምን አገልግሎት እንደሚውል በጥናት በመለየት በአብዛኛው በጨረታ እንዲሁም በምደባ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለተጠቃሚዎች ሊሰጥ ይገባል የአጠቃቀሙና የአሰጣጡ ቅደም ተከተልም እንደሚተከለው መሆን ይኖርበኖል ለኢንዱስትሪ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለማምረቻና መሸጫ ለቁጠባ ቤቶች ቅድሚያ በመስጠት ለሌሎችም መኖሪያ ቤቶች ለማህበራዊ እና ለኢኮኖማያዊ አገልግሉቶች ለሌሎች የንግድ ተቋሞች እና ለመዝናኛ ቦታዎች ቅደም ተከተሉ ከላይ እንደተገለፀው ሆኖ በየቀበሌውና በክፍለከተማው ለነዚህ አገልግሎቶች ከኢንዱስትሪ በስተቀር የሚዘጋጀውን ቦታ በማሰባጠርና አመጣጥኖ በመደልደል መፈፀም ሲኖርበት ከከተማው ኘላንና የመሬት ድልድል ጋርም መጣጣም ይኖርበታል በተለይም የቁጠባ ቤቶችንና ሌሎች ቤቶችን እንዲሁም የመኖሪያና የሥራ ቦታን ያቀላቀለ በየአካባቢው በቂ አረንጓዴና መዝናኛ ለሕዝብ አገልግሉት የሚውል ቦታ እንዲኖር የሚያስችል መሆን አለበት የቤት ልማት የቤት ልማት ለከተማ ልማት ያለው ሚና በከተሞች ደረጃውን የጠበቀና ለሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የሚመጥን የቤት ልማት ሥራ ማከናወን የከተማ መተፋፈግንና እርጅናን በማሰወገድ የመጠለያ ችግርን በመቅረፍ የቁጠባ ባህልን በማዳበርና ሰፊ የስራ ዕድልን በመፍጠር እና የአብዛኛውን ሕዝብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ለከተሞች ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ስለሆነም በከተሞች ልማት ሥራችን ለዚሁ ተግባር ልዩ ትኩረት ይሰጣል የከተማ ልማት ፖሊሲ የቁጠባ ቤቶች ማስፋፋትን ማዕከሉ ያደረገ የቤት ልማት ሊኖረን ይገባል የቤት ልማት ሲባል ለመኖሪያና ለመሥሪያ የሚሆን ቤት ለሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ማለትም ለሀብታሙም ለድዛውም ማቅረብ ይሆናል ከዚህ አኳያ የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት የተለያየ አማራጭ የሚያቀርቡ የቁጠባ ቤቶችን ማስፋፋት ይሆናል የቁጠባ ቤቶች በገበያው በበቂ መጠንና በተመጣጠነ ዋጋ ሊቀርቡ ሰለማይችሉ የቁጠባ ቤቶችን በመገንባት ረገድ የመንግሥት ሚና የላቀ ይሆናል በዚህ መነሻ ፃሣሣብ መሠረት በመንግሥት ተሣትፎና አስተባባሪነት የሚካሄድ የቁጠባ ቤት ማሰፋፋት ሥራ የቤት ልማት ቁልፍ ሥራ መሆን አለበት የከተማው አስተዳደር ዋነኛ ትኩረት አብዛኛው ሕዝብ ተባብሮና ተደራጅቶ የቁጠባ ቤት እንዲሠራ ያረጀ ቤትና መንደር እንዲያሻሽል ብሎም እንዲያድስ ማገዝና ማስቻል ይሆናል ይህ እገዛም የለማ መሬት በማቅረብ አማራጭ ዲዛይንና የግንባኖ ቴክኖሎጂ በማቅረብ ወይም የሚያቀርቡትን በማበረታታት ነዋሪዎች ይዞታቸውን እንዲያለሙ በየቀበሌውና በየመንደሩም መሠረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሻሻል የበኩሉን ድርሻ በማበርከትና በመሳሰሉት ጉዳዮች ዙሪያ ሊሆን ይገባል ከዚህም በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሮችና የክልል መንግሥታት አቅም በፈቀደ መጠን ለቁጠባ ቤት ከባንክ በቦንድ አማካይነት በመበደር እና በቤት ልማት ሥራ ተሣታፊ በመሆን የቁጠባ ቤት ሠርተው ዝቅተኛ ገቢ ላለው ድሀ ሊያቀርቡ ይገባል የአቅማቸውን ያህል ሠርተው በማቅረብና ሕዝቡ ራሱ እየቆጠበና በማኅበር እየተደራጀ ቤት እንዲሠራነ በማገዝ የቁጠባ ቤት ማስፋፋትን ማዕከሉ ያደረገ የቤት ልማት ሥራ ማፋጠን ይጠበቅባቸዋል የቁጠባ ቤቶች ማስፋፋት አቅጣጫ የከተማ አስተዳደር ትልቁ ሚና ለቁጠባ ቤት የሚሆን መሬትና መሠረተ ልማት ማቅረብ አማራጭና ወጭ ቆጣቢ ዲዛይን ማቅረብ ያረጁ ቤቶችና መንደሮችን በባለንብረቶች እንዲሻሻሉና እንዲታደሱ የአካባቢውን መሠረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት የማሻሻል እገዛ መስጠት ይሆናል ይህ እገዛም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቁጠባ ቤት በሕዝቡ እንዲሠራና ያረጁ ቤቶችም እንዲታደሱ ያስችላል ከዚህ በተጨማሪ የከተማ አስተዳደርና የክልል መንግሥታት አቅም በፈቀደ መጠን ገንዘብ ተበድረው የቁጠባ ቤት ናየሠሩ ድዛፃውን የሕብረተሰብ ክፍል በረጅም ጊዜ ክፍያ የቤት ባለቤት ሊያደርጉት ይገባል እነዚህ በአስተዳደሩ የሚሠሩ ቤቶች መሬት ቆጣቢ የጋራ ሕንጻ እንዲሆኑ በወጪ ቆጣቢ ዲዛይንና የግንባታ ዕቃ እንዲሠሩ በአነስተኛ ከተሞች ደግሞ የተጠቃሚዎችን ጉልበት በተቻለ መጠን የሚያሣትፉና የሥራ ዕድል ፈጣሪም እንዲሆኑ በሚያስችል መንገድ መፈጸም ይኖርባቸዋል የእነዚህ የቁጠባ ቤቶች የፋይናንሰ ምንጭም ከባንክ የረዥም ጊዜ ብድር በመውሰድ ከተጠቃሚዎች ቁጠባና ከመሳሰሉት ሲሆን የቁጠባ ቤቶችም በአነስተኛ ቅድመ ክፍያ በዝቅተኛ ወለድና በረዥም ጊዜ ክፍያ ለድሆች የሚተላለፉ ይሆናሉ ክፍያውም ከዐ ዓመታት ባለው ጊዜ አንዲጠናቀቀ ማድረግ ይገባል የከተማ ልማት ፖሊሲ በከተማ አስተዳደርና በማህበራት የሚከናወን የቁጠባ ቤቶች ግንባኖ ያረጁ ቤቶችና መንደሮችን ናየተካ የሚያድስና ከተማን የሚያሻሸል መሆን አለበት ግንባታውም በዋናነት በከተማ ውስጥ ባሉ ክፍት ቦታዎችና ያረጁ ሰፈሮችን በማፍረሰ የሚሠራ ሊሆን ይገባል በሚፈርሱ ቤቶች የሚኖሩ ሰዎችም በአቅራቢያቸው ከሚገነባው የቁጠባ ቤት የመግዛት ቅድሚያ መብት ማግኘት ይኖርባቸዋል ከዚህ ጋር በተያያዘም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ተመጣጣኝ ቤት ሠርተው የሚያከራዩ ባለፃብቶች በመሬትና መሠረተ ልማት በዲዛይንና ግንባታ ዕቃ አቅርቦት ድጋፍ ሊያገኙ ይገባል የቀበሌና የአካባቢ ልማት ኘላን ሲሰራም ያረጁ አካባቢዎች እንዴት ሊሻሻሉና ሊታደሱ እንደሚችሉ ማመላከትና ማቀድ ይኖርበታል ይህም ሕዝቡ ሰፊ ምክክር አድርጐበትና ተጠቃሚነቱን በሚያረጋግጥ መንገድ በጋራ በወጣው መርፃግብር መሠረት የሚፈጸም መሆን አለበት አዳዲስ የቁጠባ ቤቶች በከተማ አስተዳደሩም ሆነ በማህበራት ሲሰሩ ደረጃቸውን ያልጠበቁና የከተማ ኘላን ያልተከተሉ እንዳይሆኑ ግለጽ ደረጃ ወጥቶላቸውና የአካባቢም ይሁን የሰፈር ኘላን ተሠርቶላቸው በዚሁ መሠረት ብቻ የሚሠሩ መሆን ይኖርባቸዋል ይህንንም አቅጣጫ ለሕዝቡ የማሣመንና በጋራ በወጣው መርፃግብር መሠረት የማስፈጸም ሥርዓት የማጠናከር ሥራ ሊተኮርበት ይገባል ይህ ፖሊሲ ከመውጣቱ በፊት የተሠሩ ሕገወጥና ሕጋዊ ቤቶች የከተማ ኘላንን የሚያዛቡና የሚጥሱ ወይም ያረጁ ከሆኑ የሚፈርሱበትን መንገድ በሕግ መደንገግና መተግበር ያስፈልጋል በዚህ መንገድ ቤቶቻቸው ለሚፈርስባቸው ነዋሪዎች ምትክ መሬት መስጠት ወይም የቁጠባ ቤት አንዲገዙ ቅድሚያ መስጠት ይገባል ከዚህ በተጨማሪም ሕጋዊ ቤት ለፈረሰባቸው ነዋሪዎች በንብረት ካሣ ሕግ መሠረት ተገቢውን ካሣ መሰጠት የግድ ይሆናል ከዚህ ውጭ የማይፈርሱና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሕገወጥና ሕጋዊ ቤቶች አካባቢያቸውን የሚያሻሽል መሠረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት በመዘርጋት ባለንብረቶች ቤታቸውን እንዲያሻሸሉ ማበረታታት ካልሆነም በሂደት በአዳዲስ የቁጠባ ቤቶች መተካት ያስፈልጋል ከዚህ ፖሊሲ መውጣት በኋላ ደረጃቸውን ያልጠበቁና ኘላን ያልተከተሉ እንዲሁም ፈቃድ ያላገኙ ቤቶች እንዳይሰሩ በጥብቅ መከላከልና የተጠያቂነት ሥርዓት በሕጉ መሠረት ማስፈን የከተማ አስተዳደር ኃላፊነት ይሆናል ይህን ተግባራዊ ለማድረግም ሰለ ሕገወጥ ግንባታ ስለ ቁጠባ ቤት ደረጃና ሰለ ግንባታ ፈቃድ አስፈላጊ ደንብና መመሪያ በክልሎችና ከተሞች ሊወጣ ይገባል በዚህ ጉዳይ ዙሪያም ከሕዝቡ ጋር በቂ መግባባት መፍጠር የሚኖርበት ከመሆኑም በተጨማሪ ሕዝቡ አምኖበት የሚያከብረውና የሚያስከብረው እንዲሆን መደረግ ይኖርበታል የቁጠባ ቤቶችና የመካከለኛም ይሁን ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶች ተቀላቅለው የሚሠሩበት የመሬትና የመሠረተ ልማት አቅርቦት እንዲሁም የአካባቢ ኘላን መዘጋጀት አለበት የቁጠባ ቤቶች በአንድ አካባቢ ተነጥለው የሚገነቡበት ወይም በከተማ ዳር የሚጣሉበት አሠራር መኖር የለበትም እንደዚሁም የቁጠባ ቤቶች ለመኖሪያ ብቻ ሣይሆን በከፊል ለንግድና ለመዝናኛ የሚሆኑ ክፍሎችና ክፍት የመዝናኛ ቦታዎች ሊኖሩዋቸው ይገባል የከተማ ልማት ፖሊሲ በተቻለ መጠን አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በግንባታው ሥራ የላቀ ሚና እንዲጫወቱ ይደረጋል ባለቁጠባ ቤቶች በሂደት የቤቱን ዋጋ ከፍለው ሲጨርሱ ሙሉ የባለቤትነት መብት እንዲኖራቸው ይደረጋል ቤት ገንብተው በሚሸጡና በሚገዙ ተጠቃሚዎች መካከል ስለሚኖር የኮንትራት አሰራር በአከራይና ተከራይ ስለሚኖር የመብትና ግዴታ ግንኙነት ስለ ቤት ጥራት ደረጃ ደንብና መመሪያ ማውጣት አለበት በባለሀብት የሚካሄድ የቤት ልማትን መደገፍ ባለሃብቱ ከፍተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎችና ድርጅቶች የሚሆን የመኖሪያና የመሥሪያ ቤት ሰርቶ የመሸጥና የማከራየት ትልቅ ሚና አለው ስለሆነም በቤት ልማት ሥራ የሚሰማሩ ልማኖዊ ባለዛብቶችን ለመደገፍ የከተማ አስተዳደሩ የለማ መሬት በማቅረብ የሰለጠነ የግንባታና ዲዛይን ሙያተኛ በማፍራት የንብረት መብት ዋስትናና የንብረት ግብይት ሥርዓትን በማጠናከር አንዲሁም ችግር ፈቺና ቀጣይነት ያለው የጋራ መድረክ በመፍጠር ሊያበረታታቸው ይገባል መሬት የሕዝብና የመንግስት በመሆኑ በቤት አቅርቦት ላይ የላቀ ሚና አንዲኖረው መንግስት መሬትና መሠረተ ልማት አያቀረበ የግል ባለሀብቱ ደግሞ ገንዘብና ቴክኖሎጂ አቅርቦ በሽርክና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት የሚፋጠንበት ምቹ ሁፄታ ይፈጠራል በተጨማሪም የአካባቢውን ማቴሪያል ተጠቅመው የግንባኖ ዕቃ አንዲያመርቱ በተቻለው አቅም ሁሉ መደገፍ አለበት ፈ የመሠረተ ልማት አቅርቦት የመሠረተ ልማት አቅርቦት ዋናው አቅጣጫ ፈጣን ልማትን ማረጋገጥ ሲሆን ይህም አዋጭነትን በተከተለ መንገድ ይፈፀማልፁ መሠረተ ልማት በከተሞች የሚዘረጋው ከተሞች ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ባላቸው ሚና አንፃር በቅደም ተከተል ይሆናል ይህን መሠረት ባደረገ መንገድ ለፈጣን ልማት ምቹ ሁፄታ ለመፍጠር ፍትሐዊ ሥርጭት እንዲኖረው ልዩ ትኩረት መደረግ አለበት በዚህ መነሻ አቅጣጫ መሠረትም መሠረተ ልማት የማስፋፋት ሥራን በመንግሥት በባለዛብቱና በሕዝብ ቅንጅት መፈፀም ያስፈልጋል ከሁሉም በላይ ቀድሞ መቅረብ ያለበትና ለሁሉም ከተሞች መዳረስ ያለበት የመጠጥ ውዛፃ ይሆናል የመጠጥ ውፃ አቅርቦቱም በክልል መንግሥታትና በከተሞች አስተዳደር የሚቀርብ ሆኖ ወጪን በመመለስ መርህ ዋጋ እየተከፈለበት የሚከፋፈል ይሆናል የግንባታ ሥራውም በዋነኛነት በመንግሥት በጀት የሚሰራ ሆኖ ሕዝቡም በገንዘብና በጉልበት በከፊል እንዲሳተፍ ማበረታታት ይገባል በውዛ አቅርቦት ትኩረት የሚያስፈልገው ነገር የጥራትና የቀጣይ ጥገና ሥርዓቱን ማጠናከር አገልግሎቱ ፈጣንና ፍትሐዊም ማድረግ ይሆናል ስለሆነም ይህንን የሚያረጋግጥ አቅም የመፍጠር እገዛ በክልልና ፌዴራል መንግሥታት ሊሰጥ ይገባል ከውሃ ቀጥሎ በከተሞች ትኩረት ማግኘት ያለበት የመንገድ ሥራ ነው። እእ የሃገራችን ከተሞች መሠረኖ ዊ ችግሮች የልማት ችግሮችኔ ከ አ እ እ ከከ ከ « የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የፖሊሲው አስፈላጊነት ከ ከ ከ ከ ከ ከ ን ሲሲሲ ከ ከ ን ን ን ን ንቄ ሄ አሄ ቴቴ ፊፊ ሄሄ ዓ » ክፍል ሁለት የፖሊሲው ራዕይ ዓላማ መነሻና መርሆዎች የፖሊሲው መነሻዎች ህ ከ ን እ እ እ ን ሊሲ ሲከ ት ከ ተ ተ ን ንዓ ንን ንቴ ን ሄሄ ን ቴቴ ሄን ንን» ፌዴራላዊ ሥርዓት እህ እእ እ ከ ን ሲሌ ሲሲ ን ን ን ን ሄሄ ሄሄ ሄሄ ቴቴ የልማት ስትራተጂያችን ሻ እ እ እ እ እ እ ከ ከ ከ ሲት ሲሲ ሲሊ ግ ግ ን ን እ ሄ እ ሄሄ ቴቴ ሄሄ ፊፊ መርሆዎች ከ ከ ከ እ ን ት ን ን ት ን ን ተ ተ ተ ን ን ን ን ቴቴ ን ን ን ፊቴ ና ን ን ። ክፍል ሦስት የከተሞች ሚና ለፃገራችን ልማትና ዲሞክራሲ ከ ከ ሲን ሲን እ ን ደ ንደ ንዘ ንን ሄሄ ቴቴ ሄሄ ሄን» የከተሞች ሚና ለፃገር ልማት ሀ ን ን ን ከ ከ እ ን ን ንን ን ንዘ ንቄ ንዘ ሄሄ ቴፔ ሄሄ ፔፔ ። እ ከተሞች የገጠር ልማትን የማፋጠን ምትክ የለሽ ሚና አላቸው ከተሞች የገበያ ማፅከል ይሆናሉ ሲተ ከ ሲን ተንቄ ንቄ ን ዘ ንቴ ንቴ ሄሄ ከተሞች የአገልግሎት ማዕከል ይሆናሉ ን « ቄ ከተሞች የኢንዱስትሪ ማዕከል ይሆናሉ ሑ ሀ ህህ የከተሞች ሚና በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባና ፊህ የከተሞች አድገት የሕዝቦች ትሥሥርን ያጠናክራል ከተሞች የዲሞክራሲ ተምሣሌት ይሆናሉ ፊህ ሀ ሀ ሀ ሀ ፊህ ዜህ ከተሞች ሲያድጉ ጠንካራ የዲሞክራሲና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ይፈጥራሉ ክፍል አራት ፈጣንና ፍትፃዊ ልማት በከተሞች እህ እ ን ከ ከ ን ከ ት ሲሲ ከ ን ን ንን ን ን ሄሄ ቴቴ ቴቴ ቴፔ ሄሄ ፔን» ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት « ፋባለቤትና አስተባባሪ ሆኖ ድጋፍና አመራር የሚሰጥ ጠንካራ የአስተዳደሩ ፈፃሚ ተቋም መፍጠር የገበያ ችግራቸውን መፍኖት የአመራርና የክህሎት ችግራቸውን መፍናኖ ት ካጻ ሔ ኩን ኩንጋ ኩጋ ው ው ው ላሎዴፎ ፎ ፎ መ የከተማ ልማት ፖሊሲ የፋይናንስ ችግራቸው እንዲፈቱ ማገዝ ህእ ከተ ሲተን ሲተን ንዓ ንንን ሄን ሄሄ ቴቴ ቴፔ ቴን ንንንዓ የማምረቻ ቦታና የመሠረተ ልማት ችግራቸውን መፍታት የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ክላስተር ማዕከላት ማደራጀት የመሬት አቅርቦት ማመቻቸት እ ከ እ እ ከ ከ እ ከ እ ን ን ከ ከ ዚዜ ሲሲ ሲን ን ን ግ ግ አሄ ሄሄ ሄ ሄሄ ፔን» የመሬት ፓሊ ከ ከ ከ ከ ከ ከ ሊት ሲሲ ት ከ ን ን አ ን ሄ ግ ዘ ሄሄ ሄሄ ሄእ ቴቴ የመሬት አቅርቦት መርሆዎች እ ከ ከ ተ ሲን ንን ንን ንን ን ሄን ን ዘ ሄሄ ቴቴ ዓ«ንቴቴ የመሬት አቅርቦት ቅደም ተከተል ፊፊ ሲሲ ሲተ ሊን ን ደ ን ንን ንዓ ንዘ ን ዓዓ ሄሄ ቴቴ » የቤት ልማ እ እ እ እ ከ እ ከ ከ ከ ከ ከ ከ ሲት አ አ ን ን ን ን ግ ግ ዘ ሄሄ ሄሄ ፔፔ ፉ« የቤት ልማት ለከተማ ልማት ያለው ሚና እ እ እ ከ ከ ከ ተ ተ ዚዜ ን ዘ ንን ንግ ንን ሄሄ ሄሄ ሄን» የቁጠባ ቤቶች ማስፋፋትን ማዕከሉ ያደረገ የቤት ልማት ሊኖረን ይገባል የቁጠባ ቤቶች ማስፋፋት አቅጣጫ ህህ እ እ ን ከ ከ ሲቲ ሲን ንደ ንን ን ን ሄሄ ሄሄ ሄን ዓ«ንአንንፊሄ በባለሀብት የሚካሄድ የቤት ልማትን መደገናኦ ከ ከ ሲን ከ ንን ንን ን ደ ንደ ኣቄ«« የመሠረተ ልማት አቅርቦት ህ ፊፊ ሀ ን ሲን ን ን ከ ከ ዚን ንን ንደ ን ሄሄ ሄሄ ሄሄ ቴፔ ፔፔ ፔሼ» ማህበራዊ አገልግሎቶችን ማስፋፋት ከን ሲን ከ ሲን ሲን ሲሲ ን ን ንን ን ን ን ሄን ሄሄ ሄሄ ቴቴ ፊፔሄ ንን ትምህርትና ሥልጠና በከተሞች ማስፋፋት ፊህ የጤና አገልግሎት ማስፋፋት ን እ ከ ከ ሲሲ ሲተ ከ ሲን ንን ንን ን ን ሄን ሄሄ ሄሄ ዓዓ«» የመዝናኛ ማእከላት ማስፋፋት ፊፊ ሲከ ተ ሲን ንን ንን ደ ን ንን ሄሄ ቴቴ ሄን የከተሞች ፈርጅ ኘላንና የአካባቢ ጥበቃ የከተሞች ፈርጅ ማውጣት የከተማ ኘላን ማስጠበቅ የአካባቢ ጥበቃ በከተሞች ማረጋገጥ ዜ ክፍል አምስት ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር በከተሞች ዲሞክራሲ በከተሞች መልካም አስተዳደር በከተሞች እን እ ን ሲን ን ከ ሲተ ዚን ንቄ ን ዘ ንቴ ንቴ ቴፔ አአ የተጠናከረ የከተሞች አቅም ግንባኖ ፊፊ ህ ሦ « ክፍል ስድስት የፖሊሲው አፈፃፀም ሱ ከ ከ እ እ ን ከ ን ን ት ን ት ት ተ ን ን ን ን ተ ተ ተ ሄሄ ንንን ፊ የፌዴራል መንግሥት ድርሻሸ እእ ከ ከ ከ ከ ከ ከ ከ ከ ሲት ተ ሊን ን ን ን ን ግ ንዘ ዘ ሄሄ ሄሄ ፔቬፔፊ የክልል መንግሥታት ድርሻህ ፊፊ ህእ ከ እ እ ከ ከ ሲት ሲሲ ከ ን ን ን ን ደ ን ንዘ ንዓ ሄሄ ቴቴ ፔፔ ፔፔሼፊ» የከተሞች ድርሻ ከ ከ እ እ ከ ከ ከ ት ት ት ከ ን ተን ን ንዓ ንቴ ሄሄ ቴቴ ፊቴ ፉ ክፍል ሰባት ማጠቃለያ አዓ ክክክ ክክክ አክብብ ከ ከ ከ አ ከ ከ ከከ ከከ ከ ህከ ከ ህህህህ ቭ ቭ የከተማ ልማት ፖሊሲ።